መልዕክት ለወጣቶች
የመስዋዕትነት መንፈስ
በዓለም ውስጥ ምኞት፣ ከፍተኛ ስልጣንና ደሞዝ መሻት የተለመደ ነው። የጥንቱ ራስን የመካድና የመስዋዕትነት መንፈስ እጅግ አነስተኛ ነው። ነገር ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ተከታይ የሚያነሳሳው መንፈስ ይህ ብቻ ነው። እንዴት መስራት እንዳለብን መለኮታዊው ጌታችን ምሳሌ ሰጥቶናል። እርሱ “ተከተሉኝ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” ብሎ ለጠራቸው ሰዎች ለአገልግሎታቸው የሚከፍላቸውን የገንዘብ መጠን አልነገራቸውም ነበር። የተጠሩት ከእርሱ ጋር የእርሱን እራስን መካድና መስዋዕትነት ሊጋሩ ነበር ። MYPAmh 196.1
የሠራተኞች አለቃ ተከታዮች እንደሆኑ የሚናገሩና ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ሠራተኞች በመሆን በአገልግሎቱ ላይ የተሰማሩት ሁሉ የምድራዊ ቤተ መቅደስ በሚሰራበት ጊዜ የፍጽምና አምላክ የጠየቃቸውን ትክክለኛነትና ብልሃትን፣ ስልትንና ጥበብን ወደ ሥራቸው ማምጣት አለባቸው። ልክ እንደዚያ ክርስቶስ በምድር ላይ በአገልግሎት ላይ እንደነበረው ጊዜ ሁሉ ዛሬም ተቀባይነት ላለው አገልግሎት ለእግዚአብሔር ራስን ቀድሶ መስጠትና ራስን የመሰዋት መንፈስ እንደ መጀመሪያ መስፈርት ሆኖ መወሰድ አለበት። እግዚአብሔር በስራው ውስጥ የራስ ወዳድነት አንድ ክር እንኳን እንዲሸመን እቅድ የለውም። Herald, January 4, 1906. MYPAmh 196.2