መልዕክት ለወጣቶች
ራስን መካድ
በጊዜና በገንዘብ አጠቃቀም ላይ ጥሩ ውሳኔ የሌላቸው ሰዎች ልምድ ካላቸው ሰዎች ጋር መመካከር አለባቸው። እኔና እህቴ ከንግዳችን ከአገኘነው ገንዘብ ለራሳችን ልብስ እንገዛ ነበር። ገንዘቡን ለእናታችን እንሰጣትና “ግዢ፣ ለልብሳችን ከከፈልን በኋላ ለሚስዮናዊ ሥራ የሚሆን የሆነ ነገር ይቀራል” እንላት ነበር። እናታችንም በውስጣችን ሚስዮናዊ መንፈስን እያደፋፈረች ያልናትን ታደርግ ነበር። MYPAmh 194.5
ራስን የመካድ ፍሬ የሆነው መስጠት ለሰጪው አስደናቂ እገዛ ነው። በሰዎች መካከል መልካም እየሰራ፣ የታመሙትን እየፈወሰ፣ ለችግረኞች የሚያስፈልጋቸውን እያደረገ የተመላለሰውን የበለጠ ማስተዋል እንድንችል የሚያስችለንን ትምህርት ይሰጠናል:: አዳኙ የኖረው ራሱን በማስደሰት አልነበረም:: በእርሱ ሕይወት ውስጥ የራስ ወዳድነት ምልክት የለበትም። ምንም እንኳን ራሱ በፈጠረው ዓለም ውስጥ ቢሆንም አንዲቷን ቦታ እንኳን የእኔ ቤት ነው አላለም:: “ለቀበሮች ጉድጓድ ለወፎችም ጎጆ አላቸው፣ ነገር ግን የሰው ልጅ ራሱን የሚያስጠጋበት ቦታ የለውም::” ነበር ያለው። MYPAmh 194.6