መልዕክት ለወጣቶች
ተገቢ የሆነ የአእምሮ ምግብ
ልጆቻችን ምን ማንበብ አለባቸው? የሚለው ጥያቄ አሳሳቢ ጥያቄና ተገቢ መልስ የሚያሻው ነው። በክርስቲያን ቤተሰቦች ውስጥ በሰው አእምሮ ውስጥ ምንም የመልካም ነገር አሻራ የማያስቀምጡ ታሪኮችን የያዙ ጋዜጣዎችና መጽሐፍቶች በማየቴ ግራ ተጋብቻለሁ። የልብ-ወለድ ፍቅራቸው በደንብ የጎለበተ ሰዎችን አይቻለሁ። የእግዚአብሔርን ቃል እውነት የማዳመጥና ከእምነታችን ዋና ምክንያቶች ጋር የመተዋወቅ እድሉ ነበራቸው። ነገር ግን ያለ እውነተኛ የሕይወት ቅድስና ብዙ አመታትን አሳልፈዋል። MYPAmh 182.1
እነዚህ ውድ ወጣቶች በባህሪይ ግንባታቸው ውስጥ ከሁሉም የሚበልጠውን ነገር፣ እግዚአብሔርን መውደድን፣ መፍራትንና የክርስቶስን እውቀት መጨመር አለባቸው። ነገር ግን ብዙዎች በክርስቶስ ስላለው እውነት ትክክለኛ ማስተዋል የላቸውም። አእምሮ ስሜትን ቀስቃሽ በሆኑ ታሪኮች ግብዣ ተሞልቷል። ከእውነታ ውጪ ባለ ዓለም ውስጥ ስለሚኖሩ ለሕይወት ተግባራዊ ስራዎች ገጣሚ አይደሉም። MYPAmh 182.2