መልዕክት ለወጣቶች

304/511

የዛሬዎቹ የጥንቆላ መጻሕፍት

ኤፌሶናውያንን ተብትቦ ይዟቸው የነበረው ክፋት አለባችሁ አንልም፣ ወይም እናንተ እንደ እነርሱ አስማት እንደፈፀማችሁና የጥንቆላ ስራ እንደሰራችሁ አድርገን አንወነጅላችሁም። የጥንቆላ ምስጢሮችን ተከትላችኋል፣ ወይም ከክፉ መናፍስት ጋር ግንኙነት ፈጥራችኋል አንላችሁም። ነገር ግን የክፋት ሁሉ ደራሲ ከሆነውና እነዚህንና ሌሎች ገሃነማዊ ሥልቶችን ሁሉ ከሚያዘጋጅ ጋር ግንኙነት የላችሁምን? የዚህ ዓለም ገዥና በአየር ላይ የሚገዛ ኃይል ልዑል የሚሰጣችሁን ሃሳብ አታዳምጡምን? ለእርሱ ውሸት ራሳችሁን አሳልፋችሁ አልሰጣችሁምን? ከመለወጣችሁ በፊት ታደርጉ የነበረውን ዓይነት ስራ ለመስራት እራሳችሁን የሰይጣን ወኪሎች ለመሆን አሳልፋችሁ አልሰጣችሁምን? ሰፋ ባለ አገላለፅ ከወደቁ መላእክት ጋር ግንኙነት እየፈጠራችሁ የራሳችሁንና የሌሎች ሰዎችን ነፍስ የማታለል ጥበብን ከእነርሱ እየተማራችሁ አይደላችሁም? MYPAmh 180.3

የጥንቆላ መጽሐፍትን በተመለከተስ? ምን ታነቡ ነበር? ጊዜያችሁን እንዴት ጥቅም ላይ ታውሉ ነበር? የእግዚአብሔር ድምፅ ከቃሉ ውስጥ ሲናገራችሁ ለመስማት እንድትችሉ የተቀደሱ መጻሕፍትን ለማንበብ ትሹ ነበርን? ዓለም የጥራዝ-ነጠቅነትን፣ ታማኝነት የማጉደልን፣ የክህደትን ዘር በሚዘሩ መጻሕፍት ተታሏል። ይብዛም ይነስም እጂ እናንተም ከነዚህ መጻሕፍት ተምራችኋል! እነርሱ የጥንቆላ መጻሕፍት ናቸው። እግዚአብሔርን ከአእምሮ በማስወጣት ነፍስን ከእውነት እረኛ የሚለዩ መጻሕፍት ናቸው። MYPAmh 180.4