መልዕክት ለወጣቶች

296/511

በእግዚአብሔር ቤት ሊኖር የሚገባ ባህሪይ

በዚህ ዘመን ላሉ ወጣቶች አክብሮት እጅግ ያስፈልጋል። የኃይማኖት ቤተሰብ የሆኑ ልጆች በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ሊኖር ለሚገባው ሥርዓትና ተገቢ ባህሪይ ግድየለሽ ሆነው በማየቴ ተገርሜያለሁ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ለሕዝቡ የሕይወትን ቃል ሲያቀርቡ ሳለ አንዳንዶቹ ያነባሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ያፍዋጫሉ፣ ይስቃሉም:: በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ በመሳብ ዓይኖቻቸው ኃጢአት እየሰሩ ናቸው። ይህ ባህሪይ ቁጥጥር ካልተደረገበት እያደገ ይሄድና በሌሎች ላይ ተፅእኖ ያሳድራል። MYPAmh 174.3

እግዚአብሔር በሚመለክባቸው ስብሰባ ቦታዎች ውስጥ ቸልተኛና ግድ የለሽ መሆን በፍፁም ሊኮሩበት የሚገባ ባሕሪይ እንደሆነ ሊሰማቸው አይገባም። እግዚአብሔር እያንዳንዱን አክብሮት የጎደለውን አስተሳሰብ ወይም ተግባር ይመለከታል። ይህም በሰማይ መጽሐፍት ተመዝግቧል። እርሱ “ሥራህን አውቃለሁ” ይለናል። ሁሉን ከሚመረምር ዓይኑ የተሰወረ ምንም ነገር የለም:: በማንኛውም ደረጃ ቢሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ትኩረት የማጣትንና የግድለሽነትን ባህሪይ መስርተህ ከሆነ ይህንን መጥፎ ባህሪይ ለማረም ያሉህን ኃይሎች ተጠቀምና ለራስህ አክብሮት እንዳለህ አሳይ። አክብሮት የሕይወትህ ክፍል እስኪሆን ድረስ ተለማመደው። MYPAmh 174.4

በስብከት ጊዜ እርስ በርሳችሁ እስከመነጋገር ድረስ ለእግዚአብሔር ቤት አምልኮ ዝቅተኛ የሆነ አክብሮት አይኑራችሁ። እንደዚህ ዓይነት ስህተት እየፈፀሙ ያሉ ሰዎች እየተመለከቱአቸውና ድርጊታቸውን እየመዘገቡ ያሉ መላእክትን ማየት ቢችሉ ኖሮ በራሳቸው ያፍሩና ራሳቸውን ይጠሉ ነበር።እግዚአብሔር በደንብ አድማጮችን ይፈልጋል፡፡ ጣላት እንክርዳድ የዘራው ሰዎች ተኝተው ሳሉ ነበር። MYPAmh 174.5

ማንኛውም የተቀደሰ ነገር፣ ማንኛውም ከእግዚአብሔር አምልኮ ጋር ግንኙነት ያለው ነገር በግድየለሽነትና በቸልተኝነት መታየት የለበትም። የሕይወት ቃል በሚነገርበት ጊዜ በእግዚአብሔር በተመረጠው አገልጋይ አማካይነት የእግዚአብሔርን ድምፅ እየሰማችሁ መሆናችሁን ማስታወስ አላበችሁ:: እነዚህን ቃላት ትኩረት ባለመስጠት ማጣት የለባችሁም። በደንብ ጆሮአችሁን ከሰጣችሁ እነዚህ ቃላት እግሮቻችሁ በስህተት መንገድ እንዳይሄድ ይጠብቃሉ። MYPAmh 174.6

ሐይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያለ ሞኝነት

ብዙ ሐይማኖተኛ እንደሆኑ የሚናገሩ ወጣቶች ስለ ልብ መለወጥ ምንም እውቀት እንደሌላቸው በማየቴ በጣም አዝናለሁ። የባህሪይ ለውጥ የለም። ክርስቲያን እንደሆኑ መናገር የተቀደሰ (የከበረ) ነገር መሆኑን አይገነዘቡም። ሕይወታቸው ከሐይማኖታዊ አእምሮ ማዕቀፍ ጋር ሙሉ በሙሉ የማይስማማ ነው። እነርሱ በርግጠኝነት የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ከሚባሉት ቁጥር ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ በከንቱነት፣ የማይረባ ደስታን በመፈለግና በሞኝነት አይሞሉም ነበር። እንደዚሁም የሌሎች የሞኝነት አስተያየቶችና ጠባይ በእነርሱ ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት አይቀሰቅስም ነበር። ሽልማትን በማግኘትና ሰማይን በማግኘት ላይ ያነጣጠረ አእምሮ ሐይማኖታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚመጡ ቀልዶችንና ፌዞችን በአላማ ፅናት ጠንክሮ ይቃወማል። MYPAmh 174.7

በዚህ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ የሆነ የቸልተኝነት አደጋ አለ። እንደ ሐሳብ የለሽነትና ከንቱነት ያለ ክፉ ሞኝነት የለም። በሁሉም አቅጣጫ ከንቱ ባህሪይ ያላቸውን ወጣቶች እናያለን። በዚህ ምድብ ውስጥ ያሉ ወጣቶች በሙሉ አደገኛ ስለሆኑ ከእነርሱ መራቅ ያስፈልጋል። ክርስቲያን ነን በሚል ሽፋን ስር ያሉት ደግሞ የበለጠ ልንፈራቸው የሚገቡ ናቸው። አእምሮአቸው ዝቅ ባለ ቅርፅ የተቀረፀ ነው። እናንተ እነርሱን ከፍ ወዳሉና ወደ ከበሩ አስተሳሰቦችና ወደ ትክክለኛ የተግባር መስመር ከማምጣት ይልቅ እነርሱ እናንተን ወደ እነርሱ ደረጃ ማውረድ እጅግ ቀላል ይሆናል። ጓደኞቻችሁ በቃልና በሕይወታቸው ትክክለኛውን ባህሪይ የሚያሳዩ ይሁኑ። MYPAmh 175.1

የእግዚአብሔርን ክብር ለማሳየት ማድረግ የምትችሉትን ማድረግ እንድትችሉ ከሌሎች ጋር የሚኖራችሁ ግንኙነት የተቀደሰውን ነገር ተራ ከሆነ ነገር ለይታችሁ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮችሁን የሚጠብቅ መሆን አለበት። ሰፊ አመለካከት፣ የከበሩ አስተሳሰቦችና ግቦች እንዲኖሩአችሁ ከፈለጋችሁ ትክክለኛ መርህን የሚያጠናክሩ ጓደኞችን ምረጡ። እያንዳንዱ አስተሳሰብና የእያንዳንዱ ተግባራችሁ ዓላማ የወደ ፊት ሕይወትን ከዘላለማዊ ደስታ ጋር ወደ ማግኘት ያዘነበለ ይሁን። The Youth’s Instructor, October 8, 1896. MYPAmh 175.2