መልዕክት ለወጣቶች

276/511

ከዘላለማዊው ጋር የቅርብ ግንኙነት መፍጠር

ፀሎት የነፍስ እስትንፋስ ነው፡፡ ፀሎት የመንፈሳዊ ኃይል ምስጢር ነው፡፡ የነፍስን ጤና ለመጠበቅ ማንኛቸውም ሌላ የፀጋ መንገዶች ሊተኩት አይችሉም፡፡ ፀሎት ልብን ከሕይወት ምንጭ ጋር በመገናኘት የመንፈሳዊ ልምምድን ጅማትና ጡንቻ ያጠነክራል፡፡ የፀሎት ልምምድን ችላ ካልክ፣ ወይም ጊዜን ባልጠበቀ ሁኔታ አመቺ መስሎ እንደታየህ አሁንም አሁንም ወደ ፀሎት ልምምድ የምትገባ ከሆነ በእግዚአብሔር ያለህን ጽናት ታጣለህ፡፡ መንፈሳዊ ኃይሎችህ ብርታታቸውን ያጣሉ፣ የሃይማኖት ልምምድህ ጤናና ብርታት ያጣል…፡፡ MYPAmh 163.3

በተሳከ ሁኔታ መፀለይ መቻላችንና የማይገባቸው ተሳሳች የሆኑ ኃጢአተኞች ጥያቄአቸውን ለእግዚአብሔር የማቅረብ ኃይል ያላቸው መሆኑ አስደናቂ ነው፡፡ ሰው ከዘላለም አምላክ ጋር ለመገናኘት ከሚያስችል ከዚህ ኃይል የበለጠ ሌላ ምን ኃይል ያሻል? ደካማና ኃጢአተኛ የሆነ ሰው ከፈጣሪው ጋር የመነጋገር እድል አለው፡፡ የዓላማት ገዥ ወደ ሆነው ዙፋን መድረስ የሚችሉ ቃላትን መናገር እንችላለን፡፡ በመንገድ ላይ እየሄድን ሳለ ከኢየሱስ ጋር መነጋገር እንችላለን፤ እርሱም እኔ የቀኝ እጃችሁ ነኝ ይለናል፡፡ MYPAmh 163.4