መልዕክት ለወጣቶች

22/511

ውስጣዊ ጽድቅ

የውስጥ ጽድቅ በውጫዊ ጽድቅ ይገለፃል፡፡ በውስጡ ጻድቅ የሆነ ሰው ልበ ደንዳናና ርህራሄ የለሽ አይሆንም፡፡ ነገር ግን በየቀኑ ከብርታት ወደ ብርታት እየተሸጋገረ ወደ ክርስቶስ አምሳያነት እያደገ ይሄዳል፡፡ በእውነት እየተቀደሰ ያለ ሰው ራሱን የሚገዛ ይሆንና ፀጋ በክብር እስኪዋጥ ድረስ የክርስቶስን ዱካ ይከተላል፡፡ የጸደቅንበት ጽድቅ የተሰጠን ሲሆን የተቀደስንበት ጽድቅ ደግሞ በህይወት ልምምድ ያገኘነው ነው፡፡ የመጀመሪያው ሰማይ የማግኘት መብት እንዳለን የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለሰማይ ገጣሚ መሆናችንን የሚያሳይ ነው፡፡ Review and Herald, June 4, 1895. MYPAmh 30.2