መልዕክት ለወጣቶች

261/511

ጤንነት ባሕርይን ከመገንባት ጋር ያለው ግንኙነት

ሰው የማንነቱን ሕግ እንዲጥስ እግዚአብሔር አይፈቅድለትም፡፡ ነገር ግን ሰው መሻቱን ካለመግዛት የተነሣ ለሰይጣን ፈተናዎች በመሸነፍ የከበሩ የአካል ክፍሎቹን ለእንስሳዊ የምግብ ፍላጎቶችና ስሜቶች ተገዢ ያደርጋል፡፡ እነዚህ ፍላጎቶችና ስሜቶች የበላይነትን ሲያገኙ ለከፍተኛ እድገት መብቃት የሚችሉ የአካል ክፍሎች ያሉት ከመላእክት ትንሽ ዝቅ ብሎ የተፈጠረው ሰው ለሰይጣን ቁጥጥር ራሱን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሰይጣን በምግብ ፍላጎት ግዞት ውስጥ ያሉትን በቀላሉ ያገኛቸዋል፡፡መሻታቸውን ካለመግዛታቸው የተነሣ ከአካል፣ ከአእምሮና ከሞራል ኃይሎቻቸው አንዳንዶች ግማሹን ሌሎች ደግሞ ሁለት ሦሥተኛውን በመሰዋት የሰይጣን አሸንጉሊቶች ይሆናሉ፡፡ MYPAmh 154.2

የሰይጣንን ወጥመዶች ለይቶ ለማወቅ የጠራ አእምሮ እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ሰዎች የምግብ ፍላጎታቸው በአእምሮና በህሊና ቁጥጥር ስር መሆን አለበት፡፡ የክርስቲያን ባሕርይን ፍጹም ለማድረግ የግብረገብና ከፍ ያሉ የአእምሮ ኃይሎች ብርቱ ውሳኔ አስፈላጊ ነው፡፡ የአእምሮ ብርታት ወይም ደካማነት በዚህ ዓለም በሚኖረን ጠቃሚነታችንም ሆነ ለመጨረሻ ድነታችን የሚያደርገው እጅግ ብዙ አስተዋጽዖ አለው፡፡ በአካላዊ ተፈጥሮአችን ውስጥ ላለው የእግዚአብሔር ሕግ እየታየ ያለው ድንቁርና (ግንዛቤ ማጣት) የሚያስቆጭ ነው፡፡ ማንኛውም ዓይነት መሻትን አለመግዛት የአካልን (የጤናን) ሕግ መተላለፍ ነው፡፡ የአእምሮ ደደብነት በአስፈሪ ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡ ኃጢአት ሰይጣን በላዩ ከሚያሳርፈው የብርሃን ሽፋን የተነሣ ማራኪ ሆኗል፡፡ ሰይጣን የክርስቲያን ዓለምን እንደ አህዛብ በባህል ተጽእኖ ስር አድርጎ በየዕለቱ ልምምዶቻቸው መያዝ ሲችልና የምግብ ፍላጎት እንዲገዛቸው ሲያደርግ በደንብ ይደሰታል፡፡ MYPAmh 154.3