መልዕክት ለወጣቶች
ጤናን መጠበቅ
ጤና ያለውን ዋጋ ጥቂቶች ብቻ የሚያደንቁት በረከት ነው፡፡ ሆኖም የአእምሮአችንና የአካላችን ብቃት በአብዛኛው የሚደገፈው በጤንነት ላይ ነው፡፡ ትርታዎቻችንና ስሜቶቻችን መቀመጫቸው በአካል ውስጥ ስለሆነ አካላዊ ጤንነታችን በተሸለ ሁኔታና መክሊቶቻችንን እስከ መጨረሻ መጠቀም በምንችልበት በተሻለ መንፈሳዊ ተጽእኖ ሥር መጠበቅ አለባቸው፡፡ ማንኛውም የአካል ብርታትን የሚቀንስ ነገር አእምሮን ደካማ በማድረግ በትክክለኛና ትክክል ባልሆነ ነገር መካከል የመለየት አቅምን ይቀንሳል፡፡ MYPAmh 153.1
የአካል ኃይሎቻችንን ያለ አግባብ መጠቀም ሕይወታችን ለእግዚአብሔር ክብር የሚውልበትን ጊዜ ያሳጥርና እግዚአብሔር እንድንሰራለት የሰጠንን ሥራ ለመሥራት ገጣሚዎች እንዳንሆን ያደርገናል፡፡ ሌሊት እስከ ረፋድ በመቆየትና ጤናችንን እስከመሰዋት ድረስ ለምግብ ፍላጎት ራሳችንን በማስገዛት እኛነታችንን ለመጥፎ ልምዶች ተገዥ ስናደርግ የደካማነትን መሠረት እየጣልን ነን…፡፡ MYPAmh 153.2
ስለዚህ የተፈጥሮ ሕግን በመጣስ ሕይወታቸውን የሚያሳጥሩና ራሳቸውን ለአገልግሎት ገጣሚ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ ሰዎች እግዚአብሔርን በመቀማት ወንጀል ተጠያቂ ናቸው፡፡ እንዲሁም የእነርሱን መሰል ሰዎችንም እየቀሙ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር እንዲሰሩለት ወደ ዓለም የላካቸው ሌሎችን የመባረክ ዋና ሥራ በተከተሉት መጥፎ መንገድ በአጭሩ ተቀጭቷል፡፡ ባላቸው አጭር ጊዜ ውስጥ ሊፈጽሙት ለሚችሉት ሥራ እንኳን ራሳቸውን ገጣሚ አላደረጉም፡፡ ጎጂ በሆኑ ልምዶቻችን ምክንያት ዓለምን መልካም ነገር እንዳያገኝ ስንከለክል እግዚአብሔር በጥፋታችን ተጠያቂ ያደርገናል፡፡ MYPAmh 153.3