የወንጌል አገልጋዮች
የወንጌላዊ ኃላፊነት፡፡
«በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በመገለጡና በመንግሥቱ አመክርሀአለሁ፡፡ ቃሉን አስተምር በጊዜውና ያለጊዜውም ጽና ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገስጽ፣ ምከርም፡፡» ኢሣይያስ - 60:1- 5፣6.:ዘ፤፣ገላትያ 6:14 ፤2ኛ ጢሞቴዎስ 4፤፤2 GWAmh 18.3
እንደ ጢሞቴዎስ ላለ ለብርቱ መንፈሳዊ እንዲህ ያለ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ የሥራውን ከባድነት ያመለክታል። ጳውሎስ ጢሞቴዎሰን የሰዎችን ወግ ሳይሆን ቃለ-እግዚአብሔርን አንዲያስተምር፣ ለወዳጅም ለጠሳትም፤ ለብዙዎችም ለጥቂቶችም በችግርና በመከራም ጊዜ ደከመኝ ታክተኝ ሳይል አንዲያስተምር በጥብቅ ያስጠነቅቀዋል፡፡ የጢሞቴዎስን ደግነት በማስተዋል ጳጡሎሉሎስ ክፉ የሚሠሩንና አውቆ አጥፊዎችን በግልጽ አንዲገሰጻቸው ይመክረዋል፡፡ ግን «በትዕግሥትና በማስተማር» እንዲገሥጽ በጭማሪ አስገንዝቦታል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት የክርስቶስን ፍቅርና ትዕግስት ማሳወቅ ነበረበት፡፡ GWAmh 18.4
ኃጢዓትን ጠልቶና ገስጾ ለኃጢዓተኛው ፍቅርና ርህራሄ ማሳየት በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው:: ራሳችን አንደተቀደሰን መጠን በክርስቶስ እርዳታ ኃጢዓታችንን አንጠላዋለን፡፡ ኃጢዓተኛውን እንዳንጠላ መጠንቀቅ አለብን፡፡ በዚያውም ላይ ኃጢዓትን ችላ እንዳንል ትጉህ መሆን ይገባናል፡፡ ለተሳሳተ ሰው የክርስትና ትዕግሥት ማሳየት ተገቢ ነው:: ግን ኃጢአተኛው አበጀህ የተባለ መስሎት በስህተቱ እንዳይገፋበተ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ GWAmh 18.5