የወንጌል አገልጋዮች
ምዕራፍ 6—ለበታች እረኛ
መልካም እረኛ
ለወንጌላዊያን ሁሉ ምሣሌ የሆነው ክርስቶስ ራሱን በአረኛ መስሎታል፡፡ «መልካሙ አረኛ እኔ ነኝ መልካም አረኛ ነፍሱን ስለበጎቹ ያኖራል፡፡ መልካም አረኛ እኔ ነኝ፣ አብን እንደማውቀው እርሱም እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም በጎቼን አውቃቸዋለሁ:: የራሴም በጎች ያውቁኛል፡፡ ነፍሴንም ስለበጎት አኖራለሁ፡፡› (ዮሐ 10፡15) GWAmh 112.1
ምድራዊ አረኛ በጎቹን እንደሚያውቅ ሁሉ ሰማያዊውም እረኛ በዓለም ዙሪያ ያሉትን በጎቹን ያውቃቸዋል፡፡ «እናንተም በጎቼ፤ የማሰማሪያዬም በጎች ናችሁ እኔም አምላካችሁ ነኝ ይሳል ጌታ እግዚአብሔር” GWAmh 112.2
በጠፋው በግ ምሣሌ አንድ በግ ቢጠፋም አረኛው ለፍለጋ መውጣቱን ይናገራል፡፡ አንድ በግ ሲጠፋ «ዘጠና ዘጠኝ በጎች: አንድ ቢጠፋ በጣም ስለማይጎዳ ግዴለም አይልም፡፡ ቢፈልግ ተመልሶ ሲመጣ የበጎቹን ጉረን እከፍትለታለሁ አይልም፡፡ በጉ ሲጠፋ ወዲያው አረኛው ያዝናል እንጂ ዝም አይልም፡፡ ዘጠና ዘጠኙን በሜዳ ትቶ የጠፋውን ይፈልጋል፡፡ GWAmh 112.3
ምንም ቢጨልም፤ መንገዱ አስጊ ቢሆንም፤ ፍለጋው አድካሚም ቢሆንም፣ የጠፋውን በግ ሳያገኝ አያርፍም፡፡ የደከመውን የበጉን ጩኸት ከሩቅ ሲሰማ በጣም ይደሰታል፡፡ የድምጹንም አቅጣጫ በመመልከት አንደ አንጨት ቀጥ ባለው ዳገት ለነፍሱ ሳይሰጋ ይወጣል፡፡ የሰለለው የበጉ ድምፅ በጉ ሊሞት መቃረቡን ያስረዳዋል፡፡ GWAmh 112.4
የጠፋውን ሲያገኝ እየጎተተ ያንገላታው ይሆን? ወይስ ከኋላ ሆኖ እየገፈተረ ያዳፋዋል? በእርሱ ምክንያት ስለደከመ ለመበቀል ይደበድበው ይሆን? የለም የደከመውን በግ በትከሻው ላይ ይሸከመዋል፡፡ ያለዋጋ ባለመቅረቱ በጣም ይደሰታል፡፡ ደስታውን በመዝሙርና በምሥጋና ይገልጣል፡፡ «ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን በአንድ ላይ ጠርቶ፤ ‹የጠፋውን በጌን አግኝቸዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል፡› (ሉቃስ 15 ፡ 6-7 ) GWAmh 112.5
አንድ የጠፋን ኃጢያተኛ መልካሙ እረኛ ከወደቀበት ሲያነሳው በሰማይና በምድር ታላቅ ደስታ ይሆናል:: «አንዲሁም ንስሐ ከሚያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢያተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል፡፡>> GWAmh 113.1
ታላቁ ጠባቂ ለጠቦቶቹ አንዲጠነቀቁ አደራ የጣለባቸው ምክትል ጠባቂዎች አሉት፡፡ ክርስቶስ ጴጥሮስን የሰጠው የመጀመሪያ አደራ ጠቦቶቹን እንዲመግብ (ዮሐ. 21፡15) ጴጥሮስ በዚህ ሥራ ላይ ብዙ ልምድ አልነበረውም፡፡ ትጋትና ትዕግሥት የሚያስፈልገው ከባድ ሥራ ነው:: GWAmh 113.2
ጴጥሮስ ወጣቶችንና ልጆችን፣ በአምነታቸው ያልጎለመሱትን፣ የማያውቁትን እንዲያስተምር ወደ ወንጌል ብርሃን አንዲመራቸው፤ ክርስቶስን ማገልገል ዋጋ አንዳለው አንዲያስረዳ ተጠራ፡፡ ያን ጊዜ ጴጥሮስ ይህን ለመፈጸም ቀርቶ ሊያስተውለውም አልቻለም፡፡ ክርስቶስ ጴጥሮስን የጠየቀው ጥያቄ በጣም ትርጉም ያለው ነበር፡፡ ለአገልግሎትና ለደቀመዝሙርነት የሚረዳ አንድ ግዳጅ ጠየቀው:: «ትወደኛለህ ወይ?” አለው፡፡ ተፈላጊው ምልክት ይህ ነበር:: ጴጥሮስ ሌላውን ሁሉ አሳክቶ ፍቅር ብቻ ቢጎድለው ለአገልግሎቱ ብቁ ባልሆነም ነበር:: ዕውቀት፣ ፈቃደኝነት፣ የንግግር ችሎታ፣ አመስጋኝነት፣ ትጋት ለመልካም ሠራተኛነት በጣም ይረዳሉ፡፡ ነገር ግን የክርስቶስ ፍቅር በልቡ ያላደረበት ወንጌላዊ አይሳካለትም፡፡ GWAmh 113.3
የሱስ በገሊላ ባሕር ዳር ያስተማረውን ትምህርት ጴጥሮስ ሳይረሳው በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ለቤተ ክርስቲያን ሲፅፍ እንዲህ አለ «እኔ እንግዲህ ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞ ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፤ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ አንጂ በግድ ሳይሆን ፈቃድ አንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጎብኙት፤ ለመንጎች ምሣሌ ሁኑ እንጂ ማህበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ::› (፲ኛ ጴጥሮስ 5: 1-4) GWAmh 113.4
ከመንጋው ተለይቶ የባዘነ በግ ከሁሉ የባሰ ብዙን ነው:: ፈላጊ ካልሄደለት በቀር ከመንጋው ሊጨመር አይችልም፡፡ ከአምላኳ የተለየች ነፍስም አንደዚያው ተቅበዝባዥ ናት፡፡ መለኮታዊ ዕርዳታ ካልደረሰላት በቀር ጠፍታ ትቀራለች፡፡ ታዲያ እያንዳንዱ ምክትል ጠባቂ በትጋት፤ በፍቅር፣ በርህራሄ የጠፉትን ነፍሳት መፈለግ ይገባዋል፡፡ GWAmh 114.1
በዋናጡ ጠባቂ መሪነት ነፍሳትን የሚፈልጉ ብዙ ጠባቂዎች ይፈለጋሉ፡፡ ይህን ሲያደርጉ ሥጋዊ ምኛትና ዓለማዊ መንፈላሰስ አለመገኘቱን መረዳት መልካም ነው:፡ የተሳሳተውን በፍቅር ዓይን መመልከት፣ትዕግሥትና አለመሰልቸት ያስፈልጋል፡፡ በችግርና በስቃይ ምክንያት የምትጮኸውን ነፍስ ለማዳመጥ ፈቃደኛ መሆን አስፈላጊ ነው:: GWAmh 114.2
እውነተኛ ጠባቂ ለራሴ አይልም፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ራሱን ችላ ይላል፡፡ ቃለ-እግዚአብሔርን ሲያስተምርና የክርስቲያን ኑሮ ሲኖር የሰዎችን ፍላጎት፣ ፈተናና ችግር ይገነዘባል፡፡ ከታላቁ ጠባቂ ጋር በመተባበር ያዘነ ልባቸውን ያፅናናል፣ ችግራቸውን ይካፈላል፣ የተራበ ነፍሳቸውን ያጠግባል፣ ልባቸውን ወደ እግዚአብሔር ይመልሳል፡፡ በዚህ ሥራ ወንጌላዊውን መልአክት ይረዱታል፣ ለመዳን በሚያዘጋጀው እውነት እርሱም ይባረካል፡፡ GWAmh 114.3
ግላዊ ጥረት ለስራችን መሳካት ከሚጠበቀው በላይ ጠቃሚ ነው:: ይህ በመታጣቱ ብዙ ነፍሳት ይጠፋሉ፡፡ የአንድን ሰው ተፈላጊነት የቀራኒዮ መስቀል ይመሰክራል፡፡ GWAmh 114.4
አንድ የዳነ ነፍስ ለሌሎች ነፍሳትን ለመመለስ ዋና መሳሪያ: የመዳንና የበረከት መጨመሪያ ይሆናል፡፡ GWAmh 114.5