የወንጌል አገልጋዮች

68/217

ወደ ክርስቶስ የሚመራ ጉዳና

ከምንገምተው በላይ ብዙ ሰዎች ክርስቶስ የሚመራውን መንገድ : የመጨረሻውን የምህረት መልዕክት የሚያውጁ ሰዎች ክርስቶስ የኃጢዓተኞች መጠጊያ መሆኑን ማሳወቅ: አንዳንድ ወንጌላዊያን ስለመመለሰና ስለአምነት ማስተማር አያስፈልግም ይላሉ:: አዳማሙቻቸው ስለወንጌል በቂ ዕውቀት ያላቸው መሆኑን በመገመት አንዲያዳምጧቸው ሌላ ሌላ ነገር ያሰሟቸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ስለመዳን ታሪክ በጣም የተወሰነ ዕውቀት አላቸው፡፡ ስለሌላ ነገር ከሚማሩ ይልቅ ስለዚህ ተፈላጊ የምሥራች በበለጠ መማር አለባቸው፡፡ GWAmh 98.3

የመጽሐፍ ቅዱስ አውነቶች እንደሰንሰለት የተያያዙ መሆናቸውን ለማስረዳት የተብራራ ትምህርት ያስፈልጋል! ነገር ግን የክርስቶስ መስቀል የወንጌል መሠረት መሆኑ በሚገባ ካልተስተዋለ ሁሉም ጥረት ከንቱ ነው፡፡ ወንጌላዊያን ነፍሳትን ሊመልሱ የሚችሉት በሥራቸው የወንጌልን መልዕክት ሲገልጡ ነው:: በአዲስ ቦታ የወንጌልን ዘር ለመዝራት በሚደረገው ጥረት አብዛኛውን ጊዜ በአፍ ብቻ ንግግር ይደክማል፡፡ ሕዝቡ በሚሰሙት ነገር ይረበሻሉ፡፡ ብዙዎቹ እውነትን ያስተውሉና አረማመዳቸውን በእውነት መንገድ ለመምራት ይፈልጋሉ፡፡ የክርስቶስ ሃይማኖት በሕሊና ሊቀረጽ የሚችል ያንጊዜ ነው፡፡ ይህ ስብሰባ በሥራ የሚገለጽ ሃይማኖት ሳይታይበት ቢያበቃ ጥረቱ ሁሉ ገደል ገባ ማለት ነወ፡፡ GWAmh 98.4

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የተሰጠውን ማስረጃ በመቀበል ብቻ ከልባቸው ሳይመለሱ ማመናቸውን ይገልጣሉ፡፡ የልብን መለወጥ ተፈላጊነት ለአዳማጮች ካላስረዳ ወንጌላዊው በስራው አልቀናውም ማለት ነው፡፡ በማንኛውም አጋጣሚ ኃጢዓተኛው ኃጢዓቱን ረስቶ ወደ ክርስቶስ እንዲመለስ ሊነገር ይገባዋል፡፡ ዛሬ በዘመናችን በይፋ የሚፈጸሙት የኃጢዓት ዓይነቶች መነቀፍ አለባቸው፡፡ በሥራ የሚገለጥ ሃይማኖት ሊታይ ይገባዋል፡፡ ከአፉ የሚወጡትን ቃላት ጠቃሚነት በማመን፣ እውነተኛ ወንጌላዊ ለነፍሳት ያለበትን ኃላፊነት አይዘነጋም፡፡ GWAmh 99.1

ለወንጌላዊያን ልሰጥ የምፈልገውን ምክር ቅልብጭ ባለ አቀራረብ የሚቀርብበት በቂ ቋንቋ ቢኖረኝ እንዴት ደስ ባለኝ ወንድሞቹ ሆይ! የሕይወትን ቃል በአጃቸሁ: የመጨረሻውን የዕድገት ደረጃ ሊያገኙ ከሚችሱ ሰዎች ጋር ትሠራላችሁ፡፡ የተሰቀለው፤ የተነሣው፤ ያረገውና እንደገናም የሚመጣው ክርስቶስ የወንጌላዊውን ልብ በደስታ ሊሞላው ይገባል፡፡ ይኸው ስሜት ልቡን አለስልሶለት፣ አእምሮውን በአውቀት ሞልቶለት፤ በእውነተኛነትና በፍቅር ልብ ሰዎችን ማስተማር ይችላል፡፡ ከዚያ በኋላ የሰውየው ተፈላጊነት ይቀርና ክርስቶስ በጉልህ ይገለጣል፡፡ GWAmh 99.2

የሱስን ከፍ ከፍ አድርጉት፣ እናንት የሕዝብ መምህራን የሆናችሁ ክርስቶስን በመዝሙር፤ በጸሎት፤ በንግግር አመስግኑት፡፡ የጠፉትን፣፤ የተደናገራቸውንና ግራ የገባቸውን ነፍሳት ባለ ኃይላችሁ «ወደ እግዚአብሔር በግ» አመላክቷቸው፡፡ GWAmh 99.3

ለሚሰሙ ሁሉ « ወደ ወደደንና ራሱን ወደሰጠልን አዳኛችን ኑ” በሏቸው፡፡ የመዳን ትምህርት የስብከቱና የመዝሙሩ አርዕስት ይሁን:: በእያንዳንዱ የጸሎት ክፍለ-ጊዜ ይኸው ዋና ነገር አይረሳ፡፡ የእግዚአብሔርን ጥበብና ኃይል ወይም ክርስቶስን ለመተካት ሌላ አማራጭ ነገር አትጠቀሙ:: ለማንም ሰው ቢሆን ክርስቶስ ቋሚ ተስፋ መሆኑን አብሥሩ፡፡ ለተቸገሩት ነፍሳት የሰላምን ወንጌል: የመድኃኒታችንን ጸጋና ፍጽምና አስተምሩ፡፡ GWAmh 99.4

ከጨለማ አወጥቶ ወደ እግዚአብሔር የሚመራ አንድ መንገድ ብቻ አለ፡ ይኸውም የአምነት ጐዳና ነው:: ይህ መንገድ ጨለማና አጠራጣሪ አይደለም:: በሰብዓዊ የቀን ሠራተኞች የተደለደለ: በዚህ መንገድ ላይ ለመጓዝ የጉልበት ሥራ አያዋጣም:: GWAmh 99.5

እግዚአብሔር የጠረገልን መንገድ ከፍጽምናው የተነሣ የሰው ከፍተኛ ችሎታ ሊያሻሽለው አያስፈልግም፡፡ ከልቡ የተመለሰውን ኃጢዓተኛ ለማስጓዝ በቂ ስፋት አለው፡፡ ግን አንድም ቅንጣት ኃጢዓት ለማስገባት የማይበቃ ጠባብ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ለመጓዝ የሚችሉ በጌታ የዳኑት ናቸው፡፡ GWAmh 100.1