የወንጌል አገልጋዮች
ምዕራፍ 5—ወንጌላዊው በአትሮኑስ (በኾልፒት) ላይ
«ቃሉን አስተምሩ»
«በእግዚአብሔር ፊት በሙታንና በሕይዋን ላይ ሊፈርድ ባለው፤ በጌታ በየሱስ ክርስቶስ ፊት በመገሰጡና በመንግሥቱም እነግርአለሁ፡- ቃሉን አስተምር፣ በጊዜውና አለጊዜቬውም ጽና፣ ፍጽመህ አየታገሥህና አያስተማርህ፣ ዝለዓና፡ና ገሥጽ ምክርም::» (2ኛ ጢሞ 4፡1-2) GWAmh 90.1
ከላይ በግልጽና በማያዳግም ቃላት የወንጌላዊ ተግባር ተገልዷል፡፡ «ቃሉን ማስተማር” አለበት፡፡ የሰዎችን ስሜት ለመሳብና ድጋፍ ለማግኘት ብቻ የሰዎችን ወግና ሥርዓት፣ የሚያስደስቱን ልበወለሰዶችና አፈ-ታሪኮች እንዲናገር አልታዘዘም፡፡ ራሱን ከፍ አድር ለማስገመት ሳይሆን በሕይው አምላክና በጠፊው አለም መካከል መቆሙሙን ማወጠቅ አለበት:፡-፡ ወንጌላዊ መጽሐፍ ቅዱስን ከልቡ ማስተማር አለበት አንጂ ቃል በመምረጥ፣ አነጋገር ብቻ በማሳመር በታሪክና በአፈ-ታሪክ በመቀመም ሰዎችን ማስደስት ዋና ዓላማው መሆን የለበትም:: ለአሁንም ለዘለዓለምም አዳማጮቹን የሚጠቅሙ ምክሮችን በቅዱስ ቃል አማካኝነት ማሰማት ተገቢ ነው:: GWAmh 90.2
ወንጌላዊያን ወንድሞቹ ሆይ፤ በሕዝብ ፊት ስተቆሙ ትምህርት አዘል ንግግር አሰሙ:: በኑሮ ሊገለጥ የሚችል ጠቃሚ ዕውነት ተናገሩ:: «የኃጢዓት ይቅርታ በሚሰጠን በክርስቶስ ስም» (ቀላ. 1፡14) አስተምሩ፡፡ የዕውነትን ኃይል አድማሙች አእንዲያስተውሉላችሁ ታገሉ፡፡ ወንጌላዊያን፣ የሰባተኛውን ቀን አክባሪ አድቬንቲስቶች አምነት በትንቢት ቃላት ላይ መመሥረቱን ማሳወቅ አለባቸው፡፡ GWAmh 90.3
የዳንኤልና የራዕይ ዮሐንስ ትንቢቶች በጥንቃቄ መጠናት አላባቸው፡፡ ከእነርሱም ጋር «እነሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢዓት የሚያስወግድ” (ዮሐ. 1፡29) የሚለው አነጋገር መለየት የለበትም:: GWAmh 91.1
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ሁልጊዜ ልናስብበት የሚገባን የወንጌል ክፍል መሆኑ ተደጋግሞ ተገልጦልኛል፡፡ የዚህ ምዕራፍ ትንቢቶች በሚፈጸመብት ጊዜ አንኖራለን፡፡ ወንጌላዊያንና መምህራን እነዚህን ትንቢቶች ያብራሩ፡፡ የማይረቡ ነገሮችን በመናገር ጊዜን ከማጥፋት ይልቅ ዘለዓለማዊ ውጤት የሚያስከትሉትን ነገሮች ለሕዝብ ያስተምሩ፡፡ GWAmh 91.2
የምንኖርበት ዘመን የማያቋርጥ ትጋትን ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ወንጌላዊያን ስለ ሰንበት ማስተማርን አይዘንገ-:: ክርስቶስ በኃይልና በክብር ታጅቦ በቅርቡ አንደሚገለጥ ሰዓለም ማስረዳት አለባቸውወ፡፡ የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ የእግዚአብሔር ሕግ አንዲሻር አምላክ የማይፈቅድ መሆኑን ለሰዎች የሚገልጥ መሆን አለበት፡፡ ማንም ሰው ሕግን ለመሻር ምንም ዓይነት ምክንያት ቢያቀርብ ተቀባይነት እንደማይኖረው መታወቅ አለበት፡፡ GWAmh 91.3
የሰንበትን ክቡርነት የሚገልጹ ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተውጣጥተው ለሕዝብ አንዲነበቡ ተናግሬአለሁ፡፡ ዕውነትን ያልተረዱ ሰዎች ከዕውነት ቢርቁ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” በሚል አንቀጽ ተይዘው አንደሚፈረድባቸው ይገንዘቡበ:: እግዚአብሔር ስሰሰንበተ «በእኔና በእሥራኤል ልጆች መካከል ምልክት ናት» : (ዘፀዐት 31:17) GWAmh 91.4