የወንጌል አገልጋዮች

54/217

ፍሬ መሰብሰብ (በሕልም)

መስከረም 29 ቀን 1886 ዓ.ም. በሕልሜ ከብዙ ሰዎች ጋር ቆሜ አንድ የፍሬ ዛፍ ወደ ላይ እመለከት ነበር፡፡ ፍሬውን ለመልቀም ብዙ ወጣቶች ነበሩ፡፡ በከተማ ውስጥ: ግን በከተማው በአካባቢው ለምለም ቦታ፣ መስክ፣ መናፈሻ ያለ ይመስለኛል፡፡ GWAmh 83.1

ልዩ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች የያዘልን መጓጓዣ በፊታችን ይጓዝ ነበር፡፡ ድንገት ያ ተሽከርካሪ ሲገለበጥ ሁሉም ፍሬ ለመፈለግ በየቦታው ተበታተነ፡፡ በተሽከርካሪው በፍሬ የዘመሙ የሚያምሩ ትናንሽ ቁጥቋጦዎች ነበሩ፡፡ ግን ሕዝቡ አርቆ ይፈልግ ኖሮ ቁጥቋጦዎቹን አላያቸውም፡፡ እኔ ግን ፍሬ መለቃቀም ጀመርሁ:: ያልበሰለውን ከበሰለው ጋር እንዳላደባልቅ በጥንቃቄ ነበር GWAmh 83.2

አንዳንዶቹ የሚያምሩ ፍራፍሬዎች ግማሽ ጎናቸው በወፍና በትል ተጐርጉረው ነበር «አየ ፍሬ ለቀማው ቀደም ብሎ ተጀምሮ ቢሆን ኖሮ እነዚህ ፍሬዎች ባልተበላሹም አሁን ግን ዘግይተናል፡፡ ቢሆንም ፍሬዎቹን እየለቃቀምሁ ያልተበላሸ ፍሬ አንዳለ አያለሁ፡፡ ሁሉ ቢበላሹ አንኳ ለወንድሞቼ ባይዘገዩ ኖር ብዙ ፍሬዎች ሊለቅሙ ይችሉ እንደነበር ላሳያቸው” አልሁ፡፡ GWAmh 83.3

ከዚያ በኋላ ከሰዎቹ ሁለት ሶስቱ ወደ እኔ ያወኩ ነበር:: ጓደኝነታቸው ያረካቸው ይመስላል፡፡ ወደእኔ አየተመለከቱ «ፍሬ ፈልገን ምንም አላገኘንም» አሉ፡፡ ወደ ሰበሰብሁት ፍሬ አየተመለክቱ ተደነቁ፡፡ «ከእነዚህ ቁጥቋጦች ብዙ የሚለቀሙ ፍሬዎች አሉ:::› አልኋቸው፡፡ መልቀም «ይህን ቦታ አንች ስለያዝሽው ከዚህ መልቀም የለብንም” ብለው መልቀሙን ተውት፡፡ እኔም «ምንም አይደል የትም ቢሆን ልቀሙ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር አርሻ ነው! ፍሬዎቹም የእርሱ ናቸው› አልኋቸው፡፡ ግን ወዲያው ብቻየን ሆንሁ በተሽከርካሪው ዙሪያ ሳቅና ጨዋታ አሰማለሁ፡፡ «ምንድነው?” ብየ ብጠይቅ ብንፈልግ ፍሬ አጣን አሁን ስለራበንና ስለጠማን ምግብና መጠጥ ለማግኘት በተሽከርካሪው አጠገብ እንገኛለን» አሉኝ፡፡ GWAmh 83.4

ትንሸ ካረፉ በኋላ ሥራቸውን አንደሚቀጥሉ ነገሩኝ:: «ምንም አልሰበሰባችሁም፣፤ የሰበሰብነውን ትበላላችሁ፡፡ አሁን አልችልም፤ ገና የሚለቀም ብዙ ፍሬ አለ፡፡ ፍሬ ያላገኛችሁ በደንብ ስላልፈለጋችሁ ነው፡፡ ፍሬው በውጭ ዘምሞ አይገኝም፡፡ ፈልጉ፤ አርግጥ አንደልባችሁ በሙሉ አጃችሁ አትዘርፉም ይሆናል፡፡ ግን ቀስ በቀስ ምርጥ ፍሬዎች ልታገኙ ትችላላችሁ» አልኋቸው፡፡ GWAmh 83.5

ከረጢቴ ወዲያው በፍሬዎች ሞላችና ተሽከርካሪዎች ይዤ ሄድሁ፡፡ ‹እናንተ ሩቅ ቦታ ሄዳችሁ አጉል ስትደክሙ እኔ ከአሁን ቀደም ሰብስቤ የማላውቀውን ምርጥ ፍሬ ሰበሰብሁ” አልኋቸው፡፡ ሁሉም ፍሬዎቼን ሊያዩ ተሰበሰቡ፡፡ GWAmh 84.1

«እነዚህ ዓይነት ፍሬዎች ናቸው፡፡ እኛ ስንፈልግ የነበር የእነዚህን ዓይነት አይደለም አሉኝ፡፡ «እነቢህን ፍሬዎች ለመጠበቅና ተጨማሪ ፍሬዎች ለመልቀም ፈቃደኞች ናችሁን?” አልኋቸው፡፡ ግን ለፍሬዎቹ ለመጠንቀቅ አልተዘጋጁም ነበር:: ብዙ ዕቃዎች ነበሩ ግን አገልግሎታቸው በምግብ ማስቀመጫነት ብቻ ተወስኖ መጠበቅ ደከመኝና «ፍሬ ለመልቀም ስትዘጋጁ ለተገኙት ፍሬዎች ለምን አትጠነቀቁም?» አልኋቸው፡፡ GWAmh 84.2

ከመካከላቸው አንዱ «ሲስተር ዋይት፣ ብቡ ቤቶች ባሉበት አካባቢ ፍሬ እናገኛለን ብለን አልተጠባበቅንም ነበር፡፡ ግን አንችን ተከትለን ወጣን፡፡ ፍሬም ባናገኝ ስንቃችን ይዘን ሄደን በጉዞው ለመደሰት አሰብን» አለ፡፡ ጥቂቶች አብረውኝ ሲሄዱ ሌሎች ግን በተሽከርካሪው አጠገብ ምግብ እየበሉ ቀሩ፡፡ እኔም «ይህ ዓይነት ሥራ አይስተዋለኝም፡፡ ጀምበር ጠልቃ ጨለማ ሳይተካ ብዙ የሚሠራ ሥራ አለ» ብየ ወደ ሥራዬ ሄድሁ፡፡ GWAmh 84.3

አብረውኝ ከወጡት ሰዎች መካከል በአንድ ላይ ተሰብስበው የወጡበትን ሥራ ረስተው አናቱ ያቀፈችውን ሕጻን አየተመለከቱ በጋለ ስሜት ይነጋገሩ ነበር፡፡ ‹ጊዜአችሁ ሊያልቅ ስለተቃረበ በርትታችሁ ብትሠሩ ይሻላል» አልኋቸው፡፡ GWAmh 84.4

ሌሎቹ ደግሞ ወደተሽከርካሪው ለመድረስ የሚሯሯጡን አንድ ወጣትና አንዲት ኮረዳ ቆመው ይመሰከቱ ነበር፡፡ እነዚህ ወጣቶች ካሰቡበት ቦታ ሲደርሱ ደከሙና ትንሽ ማረፍ ሆነባቸው፡፡ ሌሎች ደግሞ በመስኩ ላይ ተዝናንተው ተቀምጠው ነበር፡፡ ቀኑ በክንቱ አለፈ አንጅ ብዙ የተከናወነ ነገር አልነበረም፡፡ GWAmh 84.5

በመጨረሻ እንዲህ አልሁ «አሁን ይህን ያልተቃና ዘመቻ ትሉት ይሆናል፡፡ የሥራ ይዞታችሁ እንደዚህ ከሆነ ባይሳካላችሁም አልደነቅም:: የሚከናወንላችሁ ወይም የማይቀናችሁ በሥራችሁ ይዞታ መጠን : ፍሬ የትም አለ፣ እኔ ብዙ ሰብስቤአለሁ፡፡ አንዳንዶቹ ባልተገቡት ቁጥቋጦዎች ስትፈልጉ ወደ ረዣዥሞቹ ቁጥቋጦች ቀና ብላችሁ ስላልተመለከታችሁ ባዶ አጃችሁን ተመለሳችሁ፣ የሰበሰብሁት ፍሬ ትልቅና የበሰለ ነው፡፡ አንደገና ወደቁጥቋጦቹ ብንመለስ ያልበሰሉ ፍሬዎች ስለነበሩ አሁን በስለው እናገኛቸዋለን:፡ ፍሬ እንዴት አንደሚሰበሰብ የተማርሁት በዚህ መንገድ ነበር፡፡ በተሸከርካረው አጠገብ ተግታችሁ ፈልጋችሁ ቢሆን ኖሮ እኔ እንዳገኘሁት ታገኙ ነበር፡፡ ዛሬ የያዛችሁት የሥራ ዘዴ በተከታዮቻችሁ ይወረሳል፡፡ ሥራችሁ ወደኋላ የተጐተተው በመብላትና በመዝናናት አብዛኛውን ጊዜአችሁን ስለምታጠፉት ነው፡፡ GWAmh 84.6

«ለሥራው የተሰለፋችሁ ዕውነትም ፍሬ የመሰብሰብ ፍላጐት አድሮባችሁ አይደለም፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ዘዴአችሁን አሻሸላችሁ በበለጠ ትጋት መሥራት አለባቸሁ፡፡ ግን በዚህ ይዞታ ከቀጠላችሁ እስከመቸውም አይቀናችሁም፣ በትክክለኛው መንገድ በመሥራት ተከታዮቻችሁን መብላትና መዝናናት ተፈላጊነቱ ዝቅተኛ መሆኑን ልታስረዷቸው ትችላላችሁ፡፡ የምግቡን ማጓጓዣ መሸከም ፍሬዎቹን ከመልቀም የበለጠ ከባድ ሥራ ነበር:: ግን እናንተ ተቀዳሚነት የሠጣችሁት የምግቡን ሳጥን መሸከመሙን ነበር:: መጀመሪያ በአቅራቢያችሁ ያሉትን ፍሬዎች ሰብስባችሁ ከዚህ በኋላ ወደ ሩቅ ቦታ ብትዘምቱ ይከናወንላችኋል፡፡› አልኋቸወ፡፡ GWAmh 85.1