የወንጌል አገልጋዮች

48/217

የጳውሎስ የትምህርት ሚዛን

አንድ ወንጌላዊ ላላመኑ ሰዎች በአንድ ጊዜ ዕውነትን ለማስጨበጥ መሞከር የለበትም፡፡ የሚናገርበትን ጊዜና ምን ተናግሮ ምን አለመናገር እንደሚገባው መወሰን አለበት:: ይህ አንደ መደበቅ ወይም አንደማታለል ሊቆጠር አይገባውም፡፡ ጳውሎስ ስለዚህ ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡ «ከሰው ሁለ አርነት የወጣሁ ስሆን የሚበልጡትን አረባ ዘንድ አንደ ባሪያ ለሁሉ ራሴን አስገዛለሁ: አይሁድንም አጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር አንደ አይሁዳዊ ሆንሁ:: ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለ ሆንሁ::- ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ ያለ እግዚአብሔር ሕግ ሳልኖር ነገር ግን ከክርስቶስ ሕግ በታች ሳለሁ ሕግ ለሌላቸው ሕግ አንደሌለኝ ሆንሁ:: ደካማዎችን እጠቅም ዘንድ ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንሁ:: በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ::› (፤ቆሮ. 9፡19-22) GWAmh 72.1

ጳውሎስ አይሁዶችን ሲቀርብ የመለየት ስሜታቸውን አንዳይቀሰቅስ ተጠንቅቆ ነው:: ቶሎ ብሎ ሳያዋዛ በናዝሬቱ በየሱስ ክርስቶስ ማመን ኣለባችሁ አላላቸውም፡፡ ግን ስለ ክርስቶስ የተነገሩትን ትንቢቶችና ክርስቶስ የሠራውን ይነግራቸው ነበር፡፡ ቀስ በቀስ አድማሙቹን የአግዚአብሐርን ሕግ የማክበርን ተፈላጊነት አስገነዘባቸው፡፡ ሕገ- ኦሪትንና የአይሁዶችን ሥነ ሥርዓት ያቋቋመ መሆኑን በማስገንዘብ ደንባቸውን አላንኳዓሰሰባቸውም፡፡- ከዚያ በኋላ ስለ ክርስቶስ ሲያስተምር የመሥዋዕት ሥነ ሥርዓት በክርስቶስ ስቅለት መደምደሙን አስረዳቸው፡፡ GWAmh 72.2

ለአሕዛብ ደግሞ ክርስቶስን ካስተዋወቀ በኋላ የሕግን ተፈሳጊነት አስረዳቸዉ- የቀራኒዮ መስቀል ለአይሁድ ደንብና ሥርዓት የሚሰጠውን ውበትና ድምቀት በዝርዝር አስረዳ:: GWAmh 72.3

ስለዚህ ሐዋርያው አንደ ቦታው፤ እንደ ጊዜው የመልዕክቱን አቀራረብ ይቀያይር ነበር፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ በመሠረቱ ቢከናወንለትም ለማመን ሳይፈቅዱ የቀሩ ብዙዎች ነበሩ፡፡ ዛሬም በምንም ዘዴ ቢሆን ላለመቀበል የቆረጡ አሉ፡፡ ቢሆንም የወንጌል ገበሬ ልዩነትንና ጠላትነትን በማያነሣሣ መንገድ ለማስተማር መሞከር አለበት:: ብዙዎቹ የሚሳሳቱት አዚህ ላይ ነው፡፡ እንዳገኙ በመጋፈጥ በተጠና ዘዴ ቤሞከር የሚከፈት በር ዘግተዋል፡፡ GWAmh 73.1

የእግዚአብሔር ሠራተኞች አርቀው ሲመለከቱ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚመለከቱ፣ በራሳቸው አካባቢ የተዘጉ መሆን የለባቸውም፡፡ የትምህርት አቀራረባቸው እንደ የሰውና አንደ የቦታው መለያየት እንዳለበት መዘንጋት የለባቸውም፡፡ GWAmh 73.2

ተቃውሞ፣ አለመግባባትና ክርክር ሲገጥመው የወንጌላዊ ሥራ በበለጠ ይከብዳል፡፡ ከሌሉቹ ይልቅ «ንጽህት፣፤ ታራቂ፣፤ ገር፤ እሺ ባይ ምህረትና በጐ ፍሬ የሞላበት፣ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለበት ጥበብ” ያስፈልገዋል፡፡ ጠልና ዝናብ ለጠወለጉ አትክልቶች አንደሚጠቅም እርሱም ለጀማሪዎች የቃሉን ጠል በለዘብታ ማርከፍከፍ አለበት፡፡ ነፍሳትን ማቅረብ እንጂ ማራቅ የለበትም፡፡ በቀላል ዘዴ ለመቅረብ ዘዴኛ መሆን አለበት፡፡ GWAmh 73.3

ዘዴና አስተዋይነት የሥራን ውጤት በመቶ አጥፍ ያሳድጉታል፡፡ ተፈላጊውን አነጋገር በገጣሚው ጊዜ ተናግሮ የቀና መንፈስ የሚያሳይ ሊረዳው የሚሞክረውን ሰው ልብ ወደ እርሱ ይስበዋል፡፡ GWAmh 73.4