የወንጌል አገልጋዮች

4/217

ሐ. በታማኝነት ማገልገል

የእግዚአብሔር ተባባሪ የሆነው የወንጌል አገልጋይ የሥራውን ቅዱስነትና የኃላፊነቱን ከባድነት መገንዘብ አለበት:: ለራሱ ምቾት መጣር የለበትም፡፡ ራሱን ይክዳል፡፡ የጠፉትን በጐች ሲሻ ረሀብ ጥማትን፣ ብርድ ትኩሳትን፤ መውጣት መውረድን ከቁም ነገር አይቀቆጥረውም፡፡ ዋና ዓላማው የጠፉትን ማግኘት ነው፡፡ GWAmh 10.1

በደም ከተበከለው ከአማኑኤል አርማ ሥር የሚያገሰግለው የወንጌል ገበሬ ጅግንነትና ትዕግሥት ያሻዋል፡፡ የመስቀሉ አርበኛ በጦርነቱ ግንባር ሲሰለፍ አይደነግጥም፡፡ ጠላት ሲጋተረው ወደ ክርስቶስ ይማጸናል፡፡ ያን ጊዜ የብርታት ጋሻ ከላይ ይሰጠዋል፡፡ የተጐናጸፈው ድል ራሱን ከፍ ከፍ አንዲያደርግ አይገፋፋውም፡፡ ግን የእግዚአብሔር ኃያልነት ያስገነዝበዋል፡፡ በዚህ ኃይል ላይ ተደግፎ የመዳንን የምሥራች ለሌሎች ያዳርሳል፡፡ GWAmh 10.2

እግዚአብሔር አገልጋዮቹን የሚልካቸው «አጉል ዕምነት ወይም ሸንገላ›” አንዲያስተምሩ ሳይሆን «ለማዳን ኃይል ያለውን የክርስቶስን ወንጌል» እንዲያስተዋውቁ ነው:፡ 2ኛ ቆላሳይስ 2:8፣ ፲ኛ ጢሞቴ 6፡፡20፤ ርሜ 1:16 GWAmh 10.3

ጳውሉስ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ብሎ ይጽፍለታል፡፡ «በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፤ በመገለጡና በመንግሥቱ እመክርሃለሁ፡፡ ቃሉን ስበክ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፣ ፈጽመህ ታግሠህና አያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፣ ምከርም፡፡ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣል፤ ነገር ግን ጆሮአቸውን የሚያሳክክ ስለሆነ እንደገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ፡፡ ዕውነትም ከመስማት ይመለሳሉ፡፡ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ፡፡ አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ መከራን ተቀበል የወንጌልን ሰባኪነት ሥራ አድርግ፣ አገልግሎትህን ፈጽም፡፡” GWAmh 10.4

ይህን መሪ ቃል ሊፈጽም የሚችል አገልጋይ «አነሆ ከአናንት ጋር ነኝ አስክፍጻሜ ድረስ” የሚለውን የክርስቶስን ተስፋ ያመነበት ብቻ ነው፡፡ ከክርስቶስ ጋር ያላቸው ግንኙነት ከተቋረጠ ከተራ ሰዎች የበሰጠ አደጋ ያጋጥማቸዋል፡፡ ሌሎችን ወደ ስህተት መንገድ እንዲያዘነብሉ ምክኒያት ሊሆኑ ይችላሉ:: ሰይጣን ጉድለታቸውን አተኩሮ ይጠባበቃል፡፡ በስህተታቸው በኩል ጠጋ ብሎ እንዲወድቁ ይታገላቸዋል፡፡ ሊያሳስታቸው ከፍተኛ የድል አድራጊነት ስሜት ይሰማዋል፡፡ አንድ የክርስቶስ ወኪል ከወደቀ ሰይጣን ብዙ ነፍሳትን ለማሳት ይቀናዋል፡፡ GWAmh 10.5

ዕውነተኛው አገልጋይ ማዕረጉን የሚያጎሳቁል አጉል ተግባር አይፈጽምም፡፡ ሥራው ተከባሪና ሰውነቱም ተወዳጅ ይሆናል፡፡ ክርስቶስ ያክናወነውን መልካም ሥራ ይሠራል፡፡ የመዳንን የምሥራች ለማዳረስ ኃይሉን በሙሉ ይጠቀምበታል፡፡ በልቡ የክርስቶስ ጽድቅ ናፍቆት አለበት፡፡ ከሁሉ በፊት የክርስቶስን ፍቅር ለሌሎች በግልጽ አንዲያስተላልፍ ኃይል ከአምላኩ ይጠይቃል፡፡ 2ኛ ጢሞ. 4:15 ፣ ማቴ. 28:20:: GWAmh 11.1