የወንጌል አገልጋዮች
ምዕራፍ 9—ዘዴዎች (አቅዶች) በከተማ ውስጥ መሥራት
መልፅክቱን በታላላቅ ከተማዎች ውስጥ ለማዳረስ ልዩ ልዩ ሥጦታና ችሎታ ባላቸው ሰዎች ለከናወኑ የሚገባቸው ብዙ ዓይነት ሥራዎች አሉ፡፡ ጥቁቶች በአንድ በኩል ሲሰለፉ፣ ሴሎች በሴሳላው በኩል ይሰለፋሉ፡፡ በክተማ ውስጥ የሚክናወነት ሥራዎች ልዩ ልዩ ሥጦታ ባላቸው የተለያዩ ሰዎች ህብረት አንዲካሄዱ እግዚአብሔር : የእግዚአብሔር ሠራተኞች እርስ በርሳቸው መግባባት አለባቸው፡ መመካክርና የልብ ህብረት ሊኖር ይገባል፡ ቢሆንም ሁሉም ከሰው መምሪያ ክመጠባበቅ ይልቅ እግዚአብሔር ጥበብ አንዲሰጣቸው መጠየቅ አለባቸው፡፡ GWAmh 225.1
እግዚአብሔር ለአንዳንድ ወንጌላዊያን ታላቅ ጉባዔ የመምራት ችሎታ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን ሻሉታ ለማዳበር ልምድ ያሳል፡፡ ልዩ ልዩ የሚያባብሉና የሚያስጎመጁ ነገሮች በሞሉባቸው ከተማዎች ተራ ጥረት አይበቃም፡፡ የሕዝብን ሀሳብ ለመማረክ ወንጌላዊያን ልዩ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ ሕዝብ ከተሰበሰበ በሏላ ለአድማጩ ማስጠንቀቂያና ትምህርት የሚሆን የተጠና መልዕክት መሰጠት አለበት፡፡ ዕውነትን ቅልብጭ አድርጎ በግልጽ ለማቅረብ የተቻለውን ያህል ማንኛውንም አጋጣሚ መጠቀም ነው፡፡ ለአሁኑ ዘመን ተፈላጊነት ያለው መልዕክት የሰዎችን ሀሳብ አነሳስቶ መጽሐፍ ቅዱስን አንዲመረምሩ የሚያደርጋቸው ነው፡፡ GWAmh 225.2
በከተማ ውስጥ ሰጌታ የሚሠሩ ሰዎች ሕዝቡን ለማስተማር የማያቋርጥ የልብ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ የሕዝብን ስሜት ለመሳብ ሲሉ በሚያደርጉት ጥረት በስሜታቸው ተመርተው ክዕውነት መስመር አንዳይወጡ መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ በአሁኑ በብልጭልጭ ዘመን፤፣ ሰው በውጭ መስሎ በመታየት በሚከናወንለት በአሁኑ ጊዜ፤ የእግዚአብሔር መልዕክትኛች ሰዎችን ለመሳብ ብለው ከመጠን በላይ የገንዘብ ወጭ ማድረግ የለባቸውም፡፡ በግልጽ፣ በትህትና፣ በክበር ሰዎችን ለማስደሰት መስለው ባለመታየተት ካስተማሩ ውጤቱ ዘላቂ ይሆናል፡፡ GWAmh 225.3
ማስታወቂያ ለማዳረስ፤ ሥራውን ለማካሄድ ገንዘብ ወጭ ማድረግ አይካድም፡፡ ግን እያንዳንዱ ሠራተኛ ብርታት የሚያገኘው አንደ እነቢህ ካሱት ጥቃቅን ድርጊቶች ሳይሆን በጸሎትና ቃሉን በመታዘዝ ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆነ መዘንጋት የለበትም፡፡ GWAmh 226.1
ተጨማሪ ጸሉት፣፤ የክርስትና ሕይዎት፣ ፈቃድ መታዘዝ በጌታ ሥራ ላይ መዋል አለበት፡፡ ታይታና ገንዘብ ማባከን ሊፈጸም የሚገባውን ሥራ አያከናውንም፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ ወደፊት በኃይል መግፋት አለበት፡፡ እግዚአብሔር በክብር ላይ ክብር የሚደርብላቸው ዓለምን ለማስጠንቀቅ ያለ ችሎታቸውን በሙሉ ከልብ ለሚሰሩበት ሰዎች መሆኑን አናስተውል፡፡ በዓለም ያለው ሰው ሁሉ በሙሉ ሕገወጥና ኃጢዓተኛ አይደለም፡፡ ጉልበታቸውን ለብዔል ያላንበረከኩ በብዙ ሽህ የሚቀጠሩ ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ጠንዶችና ሴቶት አሉ፡ እንዲህ ባይሆን ኖሮ «ወደቀች ወደቀች ታላቂቱ አገር ባቢሎን ሕዝቤ ሆይ ከእርሷ ው» (ዘራዕ.18፡2-4)4 የሚለው መልዕክት ባልተሰጠን ነበር፡፡ ከልባቸው ታማኝ የሆኑ ብዙ ስዎች ከሰማይ ሕይወት ይፈልጋሉ፡፡ ወንጌል በግልጽ ሲሰጣቸው ያስተውሉታል፡፡ GWAmh 226.2