የክርስቲያን አገልግሎት

113/246

ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው

የሱስ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ጠርቶ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ከተማውና መንደሩ ሁሉ እንዲሄዱ አዘዛቸው፡፡ ወንድም ከወንድሙ፣ ወዳጅ ከወዳጁ ጋር እየሆኑ ተላኩ እንጂ ብቻውን የሄደ አልነበረም፡፡ ይህ የሆነበት ምከንያት እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱና እንዲደፋፈሩ፣ እንዲመካከሩና አብረው እንዲጸልዩ፣ብሎም የአንዱ ብርታት የሌላው ድhመት ሟሟያ እንዲሆን ለማድረግ ነበር፡፡ ሌላ ጊዜ ሰባውን የላካቸው በዚሁ አኳኋን ነበር፡፡ የወንጌል መልእክተኞች የዚህ ዓይነት ግንኙነት እንዲኖራቸው የአዳኛችን ዕቅድ ነበር፡፡ እኛም ለዚህ ዘመን አገልግሎት ከዚህ ምሳሌ ጋር በቅርበት ብንራመድ የወንጌል ሥራ በእጅጉ የተሳካ ይሆናል፡፡--The Desire of Ages, p. 350. ChSAmh 176.2