የክርስቲያን አገልግሎት

108/246

የግል ተሞhሮዎችን መጥቀስ

ራሳቸውን በhርስቶስ ፈቃድ ስር ያኖሩ ደረጃ በደረጃ የተለማመዱትን የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ለይተው ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔርንና እርሱ የላከውን የየሱስ ክርስቶስን ዕውቀት መራብና መጠማታቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስን መርምረው ስላገኙት ውጤት፣ ስለ ጸሎታቸው፣ ስለ ነፍሳቸው መቃተትና ከርስቶስ “ኃጢአትv ይቅር ተብሎልሃል” በማለት ስለተናገራቸው ቃላት ብዙ መናገር ይችላሉ፡፡ እነዚህን ተሞhሮዎች ሳይናገሩና ሳይመሰክሩ በምስጢር መያዝ ለማንኛውም የእግዚአብሔር ልጅ ተፈጥሮአዊ ሊሆን አይችልም፡፡ በከርስቶስ ፍቅር የተሞሉ እንዲህ አያደርጉም፡፡ የአምላካዊው የተቀደሰ እውነት ማደሪያ ያደረጋቸው ሕዝቦቹ ሌሎችም ተመሳሳይ በረከት እንዲቀበሉ ምኞታቸው ይሆናል፡፡ የhበረውን የእግዚአብሔር ጸጋ ለሌሎች ገልጠው ባሳዩ ቁጥር የበለጠውና ከፍ ያለው የhርስቶስ ጸጋ ተካፋዮች ይሆናሉ፡፡Christ’s Object Lessons, p. 125. ChSAmh 171.1

እያንዳንዱን መንፈሳዊ ጉልበት ለተግባራዊ እንቅስቃሴ ማነሳሳት ይኖርብናል፡፡ የምድራዊው ነገር ማከተሚያ መቃረቡን ለምትጎበኗቸው ሁሉ ንገሯቸው፡፡ ጌታ የሱስ ክርስቶስ የልቦቻቸውን በር ከፍቶ በአእምሮአቸው የሚቀር አሻራ ይተዋል፡፡ ወንዶችና ሴቶችን ጠርንፎ ከያዘው መንፈሳዊ በድንነት ለመቀስቀስ ብርቱ ትግል አድርጉ፡፡ የሱስን እንዴት እንደተገናኙትና እርሱን ማገልገል ከጀመሩ ወዲህ ስላገኙት በረከት ተሞhሮዎን ለሌሎች ያካፍሉ፡፡ በየሱስ እግሮች ስር ተቀምጠው ከቃሉ የከበረውን ትምህርት መቅሰም ከጀመሩ አንስቶ ያገኗቸውን በረከቶች ይዘርዝሩ፡፡ በከርስትና ሕይወት ስላለው ሐሴትና ደስታ ያውሩ፡፡ ከአንደበትዎ የሚወጡት የሚያነቃቁና ልብ የሚነኩ ቃላት በእርግጥ ያን የከበረ ዋጋ ያለውን ሉል ለማግኘትዎ ማሳኛ ይሆናቸዋል፡፡ ፍልቅልቅ፣ ደስተኛና አበረታች ቃላቶችዎ ከፍ ያለውን አቅጣጫ ማግኘትዎን የሚያሳዩ ይሁኑ፡፡ ይህ ከልብ በመነጨ ስሜት የሚሠራው የወንጌል ሥራ በተጨባጭ ተግባር ላይ ሲውል ብዙዎች ከvልማቸው ይነቃሉ፡፡-- Testimonies, vol. 9, p. 38. ChSAmh 171.2

እግዚአብሔር መሣሪያዎቹ አድርጎ በአገልግሎቱ ላይ የሚመድባቸው ወገኖች ምናልባት በአንዳንዶች ብቃት የጎደላቸው ተደርገው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከጸለዩ፣ የሚወዱትን እውነት ግልጽና ሊስተዋል በሚችል ቀላል መንገድ ማውራት ከቻሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ ሕዝቡ መድረስ ይችላሉ፡፡ እውነትን በማያሻማ ልኩ ቀለል አድርገው ሲያቀርቡ፣ ከእግዚአብሔር ቃል ሲያነቡ ወይም ያለፉ ገጠመኞቻቸውን ሲያካፍሉ መንፈስ ቅዱስ የአድማጮቻቸውን አእምሮና ጸባይ ይነካል፡፡ ሳይስተዋል የቀረው እውነት ሕያው በሆነ መተማመን ወደ ልብ በመምጣት መንፈሳዊ ሃቅ መሆን ሲችል ለአምላካዊው ፈቃድ ተገዢ ይሆናሉ፡ ፡— Testimonies, vol, 6, p. 444። ChSAmh 172.1