የክርስቲያን አገልግሎት

101/246

ለአንድ ነፍስ መመስከር

የክርስቶስ ሥራ ግለሰብን መሰረት አድርጎ የተዋቀረ እንደመሆኑ ለአንድ ነፍስ በታማኝነት፣ በግል ስለ መመስከር ብርቱ አጽንኦት ይሰጣል፡፡ በዚያ አንድ ነፍስ ተቀባይነት ያገኘ ምስክርነት ወደ ሺዎች ይዛመታል፡፡ Testimonies, vol. 6, p. 115. ChSAmh 161.2

የሱስ ዝሎና ደክሞ የነበረ ቢሆንም-ኃጢእት በይፋ ትሠራ የነበረችውን ይህችን ዕንግዳና ለእስራል ባዕድ ሴት ለማነጋገር ያጋጠመውን ዕድል ችላ አላለም፡፡ The Desire of Ages, p. 194. ChSAmh 161.3

አዳኛችን ብዙ ሰዎች እስኪሰበሰቡ አልጠበቀም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በዙሪያው ለተሰበሰቡት ጥቂት ሰዎች ማስተማር ይጀምራል፡፡ ሆኖም አልፎ ሂያጆች አንድ በአንድ እየቆሙ ያዳምጣሉ፡፡ በዚህ አኳኋን ብዙ ሰዎች ይሰበሰቡና የእግዚአብሔርን ቃል በአድናቆትና በፍርሐት ከሰማይ ከተላከው መምህር ይሰማሉ፡፡ የክርስቶስ ሠራተኛም ለብዙ ሰዎች ለመናገር በሚችለው አኳኋን ለጥቂት ሰዎች መናገር አልችልም የሚል ስሜት ሊኖረው አይገባም፡፡ መልእhቱን የሚሰማው አንድ ሰው ብቻ ሊሆን ቢችል እንኳ ነገር ግን ምን ያህል ተስፋፍቶ እንደሚሰራጭ ማን ያውቃል? አዳኛችን ከአንዲት ሳምራዊት ሴት ጋር ጊዜውን ማሳለፉ ደቀ መዛርቱ ዋጋ ያለው አልመሰላቸውም ነበር፡፡ ነገር ግን የሱስ ከነገሥታት፣ ከአማካሪዎችና ከሊቀ ካኅናት ጋር ቢነጋገር ኖሮ ይጠቀምበት ከነበረው አመክንዮና አንደበተ ርቱd አቀራረብ በበለጠ ከሴትየዋ ጋር ተወያየ፡፡ ለዚያች ሴት የሰጣት ትምህርት በተደጋጋሚ እስከ ዓለም ዳርቻ መቅረብ ችሎአል፡ ፡--The Desire of Ages, p. 194. ChSAmh 161.4