የክርስቲያን አገልግሎት

4/246

የhርስቲያን ኃይሎች ጥምረት

“እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” የተሰኘው ጥያቄ በhርስትና የእምነት ተጓዳኝ ወንድም እህቶች ልብ ውስጥ ይነሳ ይሆን? የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆኑ የሚያምኑ ከሆነ የወንድምዎ ጠባቂ ኖት፡፡ ጌታ ሌሎችን ለማዳን መንስኤ ለሆኑ ነፍሳት ኃላፊነት እንዲኖራት አድርጎ ቤተ ክርስቲያንን ደግፎ ይዞአል፡፡--Historical Sketches, p. 291. ChSAmh 16.2

አዳኙ በሥቃይ፣ በሐዘንና በፈተና ለሚገኙ ወገኖች ብቁ አገልግሎት መስጠት የምትችል ቤተ ክርስቲያን ለመመስረት ሲል የከበረ ሕይወቱን ሰጠ፡፡ የአማኞች ጉባዔምስኪን፣ ያልተማረና በብዙዎች የማይታወቅ ቢሆን፤ አማኞች በቤታቸው፣ በማኅበረሰባቸው ብሎም ከእነርሱ “ወዲያ ባለው አገር” በክርስቶስ ዘላለማዊ ውጤት ያለውን ሥራ ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡The Ministry of Healing, p. 106. ChSAmh 16.3

ምንም እንኳ ቤተ ክርስቲያን ደካማና ጉድለት ያላት ብትመስልም እግዚአብሔር በተለየ መልኩ ከፍ ባለ አንክሮ የሚመለከታት አካል ናት፡፡ ቤተ hርስቲያን እርሱ ደስ የሚሰኝበትን ልቦችን የመለወጥ ሥራ የሚገልጥባትና የአምላካዊው ጸጋ ትዕይንት የሚታይባት መድረክ ናተ፡፡--The Acts of the Apostles, p. 12. ChSAmh 16.4

እያንዳንዱ ሰው የክርስቶስን ተልዕኮ ማሳከትና እርሱ በዚህ ምድር የጀመረውን ይዞ መቀጠል የሚኖርበት ሲሆን ቤተ ክርስቲያንም ይኸው ልዩ መብትና ጥቅም ተሰጥቶአታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የተደራጀችው ይvን ዓላማ ለማሳካት ቢሆንም የቤተ ክርስቲያን አባላት ይህን ኃላፊነት ያልተቀበልንበት ምክንያቱ ምን ይሆን?--Testimonies, vol. 6, p. 295. ChSAmh 17.1

አባላት የተመደቡበትን ተግባር እንዲያከናውኑ፣ በግዛታቸው አምላካዊውን ትእዛዛት መሰረት ያደረገ እውነተኛ መነቃቃት እንዲያደርጉ፣ ተገቢ ሥልጠና የወሰዱና በሥራው ተሞክሮ ያላቸው ሠራተኞች በአዳዲስ የአገልግሎት መስኮች ላይ እንዲሰማሩ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን ጥሪውን ያቀርባል፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 292. ChSAmh 17.2

በቀረበላቸው እውነት ልቦቻቸው የተሸነፈው. . . በየቀኑ ነፍሳት ይጨመሩላቸው የነበሩት የተሰሎንቄ አማኞች እውነተኛ ወንጌላውያን ነበሩ፡፡The Acts of the Apostles, p. 256. ChSAmh 17.3

ክርስቶስ ካረገ በኋላ በምድር የጀመረውን ሥራ ለማስቀጠልና ቤተ ክርስቲያንን ለማደራጀት የመጀመሪያው ተቀዳሚ ተግባር አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለአገልግሎት መቀባት ነበር፡፡--The Acts of the Apos tles,P 18. ChSAmh 17.4

የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ችሮታ በተለያዩ ስጦታዎች የተሞላች የቅድስና ሕይወት ቅጥር ናት፡፡ አባላት በሚረዷቸውና በሚባርኳቸው ወገኖች ደስታ ሐሴት ያደርጋሉ፡፡ ጌታ በቤተ ክርስቲያኑ አማካይነት ለመሥራት ያቀደው ወደር የማይገኝለት ሥራ አምላካዊው ስም የሚከብርበት ነው፡፡--The Acts of the Apostles, pp. 12, 13. ChSAmh 17.5

የምነራው ሥራ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ቁልጭ ብሎ ሰፍሮአል፡፡hርስቲያኖች ከhርስቲያኖች ጋር ቤተ hርስቲያን ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሕብረት በመፍጠርና—ሰብዓዊው ፍጡር ከመለኮት ጋር በመተባበር ብሎም ጠቃሚ መሣሪያ በመሆንእያንዳንዱ ወኪል በመንፈስ ቅዱስ አመራር ስር ሆኖ መልካሙን የእግዚአብሔር ጸጋ በማብሰሩ ረገድ ኅብር መፍጠር ይኖርበታል፡፡—General Conference Bulletin, Feb. 28, 1893, p. 421. ChSAmh 18.1

ቤተ ክርስቲያኖቻችን ውሎ አድሮ የሚገኘውን መከር ተስፋ በማድረግ በመንፈሳዊው የእርሻ ሥራ መተባበር ይኖርባቸዋል. . . አፈሩ መንቻካ ቢሆንም ነገር ግን ያልታረሰው መሬት ሊታረስና የጽድቅ ዘር ሊዘራበት የግድ ነው፡፡ በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ መምህራን በሠራችሁ ቁጥር እያደገ የሚሄደውን ሥራ እስከ መጨረሻው ለመቀጠል ጥርጣሬ ገብቶአችሁ አታቁሙ::Testimonies, vol. 6, p. 420. ChSAmh 18.2

ቤተ ክርስቲያን ሰዎች ደኅንነት እንዲያገኙ እግዚአብሔር የሾማት ወኪሉ ናት፡፡ አገልግሎት እንድትሰጥ የተደራጀችው የቤተ ክርስቲያን ዓላማ ወንጌልን ለዓለም ማዳረስ _ ነው፡፡ _ አምላካዊውን ሙላትና መትረፍረፍ በቤተ ክርስቲያኑ አማካይነት መግለጥ ከመጀመሪያ የነበረ የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው፡፡ ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃን የጠራቸው የቤተ ክርስቲያን አባላት የእርሱን ክብር ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡The Acts of the Apostles, p. 9. ChSAmh 18.3

ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ጊዜ የሚሆን ታላቅ አገልግሎት ማበርከትና በሰዎች ላይ ተጽእኖ ማሳደር እጅግ ቀላል ተግባር አድርጋ አታስብ፡፡ ወንድሞች ሆይ ለአገልግሎት ውጡ፡፡ ከእግዚአብሔር የተለየ ሞገስ የምናገኘው በታላላቅ ጉባዔዎች ወይም በአንድነት የአምልኮ መርጎ ግብሮች በመካፈል ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም እጅግ በትህትና የተሞላ ከራስ ወዳድነት የራቀ የፍቅር ልግስና አምላካዊውን በረከት በመቀዳጀት ከእርሱ የተዘጋጀውን ሽልማት ይወስዳል፡፡ አቅምዎ የሚፈቅደውን ሲያደርጉ እግዚአብሔር ችሎታዎን ይጨምራል፡፡Review and Herald, March 13, 1888. ChSAmh 18.4