የክርስቲያን አገልግሎት

99/246

መሳጩ ትዕይንት

ምሽት ላይ በተመለከትኩት ራእይ ብርቱ ትዕይንት በፊቴ አልፎ ነበር፡፡ አንድ ግዙፍ የእሳት ኳስ በጣም በሚያምሩ ጥቂት ቤቶች ላይ ወድቆ ወዲያውኑ ዶግ አመድ ያደርጋቸዋል፡፡ “የእግዚአብሔር ፍርድ በምድር ላይ እንደሚመጣ እናውቅ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን እንዲህ በፍጥነት ይደርሳል ብለን አልጠበቅንም” በማለት አንድ ሰው ሲናገር ሰማሁ፡፡ ሌሎች ደግሞ እጅግ ሕም ባላቸው ድምጾች “ይህን ታውቁ ነበር! ታድያ ለምን አልነገራችሁንም? እኛ ግን አላወቅንም! በማለት ይናገሩና በያንዳንዱ አቅጣጫ ተመሳሳይ የትችት ቃላት እሰማ ነበር፡፡ ChSAmh 154.2

በታላቅ ሕመምና ሥቃይ ውስጥ ሆኜ ከነቃሁ በኋላ መልሶ እንቅልፍ አሸለበኝ፡፡ በአንድ ትልቅ ስብሰባ ውስጥ ያለሁ ይመስለኛል፡፡ ለተሰብሳቢው ሕዝብ ንግግር እያደረገ ከነበረው ከኃላፊዎቹ አንዱ ፊት የዓለም ካርታ ተገልጦ ነበር፡፡ ካርታው ሊለማ ስለሚገባው የእግዚአብሔር የወይን ተhል እንደሚያሳይ ተናገረ፡፡ በብዙ ቦታዎች ላይ ብርሃን ይበራ የነበረ ሲሆን ከእነዚህ ብርሃኖች ላይ እየተነሱ ሌሎች ብርሃኖችም ይቀጣጠሉ ነበር፡፡ ChSAmh 154.3

የሚከተሉት ቃላት በድጋሚ ሲነገሩ ሰማሁ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጣዕሙን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጪ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም፡፡ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤ ሰዎችም መብራት አብርተው ከእንቅብ በታች አያስቀምጡትም፤ በቤት ውስጥ ሁሉ ላሉት እንዲያበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ፡፡ እንዲሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለው አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ፡፡” (ማቴ. 5፡13—16)፡፡ ChSAmh 155.1

ከከተሞችና ከመንደሮች፣ ከፍ ካለ መልክአ ምድርና ከረባዳማ ስፍራዎች እንደ ጀት የሚተኮሱ አንጸባራቂ የብርሃን አምዶችን ተመለከትኩ፡፡ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ታዝዘው፤አምላካዊውም እውነት በመላው ምድር ታውጆ ነበር፡፡Testimonies, vol. 9, pp. 28, 29. ChSAmh 155.2