የክርስቲያን አገልግሎት

97/246

ዋጋ የተከፈለበት አገልግሎት

ጌታ ዳግም በሚገለጥበት ወቅት ለእያንዳዱ የሰጠውን መክሊት በጥንቃቄና በጥልቅ በመመርመር ለሰጠው አደራ ትርፉን ይጠይቃል፡፡ ክርስቶስ ውርደትና ሕማም ተቀብሎ፣ ፍዳ በበዛበት ምድራዊ ሕይወቱና አሳፋሪ ሞቱ ስሙን ወስደው የእርሱ አገልጋይ የተባሉትን ሁሉ እዳ ከፍሎአል፡፡ — Testimonies, vol. 9, p. 104. ChSAmh 150.2

ሁሉም ነፍሳትን ለእርሱ መማረክ ይችሉ ዘንድ መክሊቶቻቸውን ጥቅም ላይ እንዲያውሉና እንዲያጎለብቱ በሚጠይቅ ጥልቅ ግዴታ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ “እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም በዋጋ ተገዝታችኋልና” ስለዚv ወንዶችንና ሴቶችን ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ሊያሸንፍ በሚችል በአገልግሎት ሕይወት እግዚአብሔርን አክብሩ፡፡ እኛ ሁላችን በታማኝ አገልግሎት የገዛ ንብረቱን ወደ እግዚአብሔር እንድንመልስ በክርስቶስ ሕይወት ተገዝተናል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 104. ChSAmh 151.1

እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚሆን መልእክት ሰጥቶኛል፡፡ ከእንቅልፋቸው ነቅተው ድንኳኖቻቸውንና ድንበሮቻቸውን ሊያሰፉ የግድ ነው፡፡ ወንድሞቼና እህቶቼበዋጋ የተገዛችሁ እንደመሆናችሁ ራሳችሁን ጨምሮ እናንተ ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብርና ለባልንጀራችሁ ጥቅም ሊውል ይገባል፡፡ በኃጢአት እየጠፋ ያለውን ዓለም ለማዳን ሲል በመስቀል ላይ የሞተው ክርስቶስ በሥራው ተባባሪ እንድትሆኑ ይጠይቃችኋል፡፡ ለእርሱ እገዛ እንደሚያደርግ እንደ አንድ አካል፤ ጽኑ በሆነና በማይዋልል ጥረት የጠፉትን በመፈለጉ ሥራ ይሰማሩ፡፡ መስቀሉን አስፈላጊ ያደረገው የእርስዎ ኃጢአት መሆኑን አይዘንጉ፡፡Testimonies, vol. 7, p. 9. ChSAmh 151.2

የክርስቶስ ተከታዮች አገልግሎት እንዲሰጡ ተዋጅተዋል፡፡ ተጨባጩ የሕይወት ዓላማ አገልግሎት መሆኑን አዳኛችን አስተምሮአል፡፡ እርሱ ራሱ ሠራተኛ የነበረው ክርስቶስ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን የማገልገልን— የአገልግሎት ሕግ ለመላው ተከታዮቹ ይሰጣል. . . የአገልግሎት ሕግ እኛን ከእግዚአብሔር ብሎም ከባልንጀራችን ጋር የሚያስተሳስር ገመድ ለመሆን F:- Christ’s Object Lessons, p. 326. 110 ChSAmh 151.3