የክርስቲያን አገልግሎት
እርግጠኛው መፍትሔ
ተስፋ ለቆረጡት እርግጠኛ መፍትሔ ያለ ሲሆን ይኸውም እምነት፣ ጸሎትና ሥራ ናቸው፡፡ እምነትና ሥራ በየቀኑ እያደገና አየጨመረ የሚሄድ የዋስትና ስሜትና እርካታ ያስገኛሉ፡፡ ለስጋት፣ መጪውን ሁናቴ ለመፍራት፣ ተስፋ ለመቁረጥና ፈራ ተባ ለማለት መንገድ እንዲከፍቱ ተፈትነው ይሆን? ቀኑ በጨለማ የተዋጠና የሚታየው ሁሉ አስፈሪ ቢመስል እንኳ አይፍሩ፡፡ ለእርስዎ የሚያስፈልገውን ሁሉ በሚያውቀው በእግዚአብሔር ላይ እምነት ይኑርዎት፡፡ ኃይል ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ዘላለማዊ ፍቅሩም ሆነ ርኅራኄው ፈጽሞ አይታhትም፡፡ የገባውን ቃል ሳይፈጽም ይቀራል የሚል ፍርሐት አይግባዎት፡፡ እርሱ ዘላለማዊ እውነት ነው፡፡ እርሱን ከሚወዱት ጋር የገባውን ኪዳን ፈጽሞ አያፈርስም፡፡ ታማኝ አገልጋዮቹ የሚያሻቸውን ያvል ብቃት ይለግሳቸዋል፡፡Prophets and Kings, pp. 164, 165. ChSAmh 147.2
ለመንፈሳዊው ስንፍና የሚበጅ አንድ ፍቱን ፈውስ ያለ ሲሆን ይኸውም ሥራ ነው--የእርስዎን እርዳታ ለሚሹ ነፍሳት መሥራት፡፡ Testimonies, vol. 4, p. 236. ChSAmh 148.1
ይህ እንግዲህ ልባቸው በፍርሐት ለሚርድ፣ ለተጠራጣሪዎችና ለሚርበተበቱ ነፍሳት በክርስቶስ የተሰጠ መድኃኒት ማዘዣ ነው፡፡ በጌታ ፊት በብርቱ ሐዘን የሚያልፉ፣ የተከፉ ነፍሳት ብድግ ብለው እርዳታ ለሚያሻው አገልግሎት ይስጡ፡ ፡— Testimonies, vol. 6, p. 266. በጽናት፣ በቅንአት፣ በብርቱ ስሜትና በፍቅር ያለማቋረጥ እያደጉ ያሉ ክርስቲያኖች ፈጽሞ ወደ ኋላ አይመለሱም፡፡Review and Herald, June 7, 1887. ChSAmh 148.2
በእንዲህ ያለው ከራስ ወዳድነት መንፈስ የጸዳ አገልግሎት ተካፋይ ያልሆኑ ከጥርጣሬ፣ ከማጉረምረም፣ ከጢአትና ከንስሐ ጋር በሚፈጥሩት ግብግብ ህመም ባለው ተሞክሮ ውስጥ የወደቁና ትክክለኛው ኃይማኖት መያዝ የሚገባው ነገር ትርጉሙ እስኪጠፋቸው ድረስ ሁሉንም ስሜቶች ያጡ ይሆናሉ፡፡ ወደ ዓለም ተመልሰው መሄድ እንደማይችሉ ስለሚሰማቸው በጽዮን ጫፍ ላይ የተንጠላጠሉ፣ በጠባብ አስተሳሰብ፣ በቅናት፣ በተስፋ መቁረጥና በጸጸት ስሜት ውስጥ የወደቁ ይሆናሉ፡፡ የሰዎችን ስህተት ፈላጊና የወንድሞቻቸውን ጉድለቶች አሳባቂ በመሆናቸው፤ የመንፈሳዊ ሕይወታቸው ተስፋ የጨለመ፣ እምነተ ቢስና የብርሐን ጸዳል የሌላቸው ይሆናሉ፡፡--Review and Herald, Sept. 2, 1890. ChSAmh 148.3