የክርስቲያን አገልግሎት
የhርስቲያኑ ሕይወት ከተፈጥሮአዊው ትዕይንት አኳያ
የእግዚአብሔርን ቃል የሚቀበለው ልብ እንደሚያተን የውሃ ገንዳ ወይም በውስጡ የያዘውን ዋጋ ያለውን ፈሳሽ እንደሚያፈስ የውሃ ማጠራቀሚያ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከተራሮች ሥር እንደሚፈልቀው የማይነጥፍ ምንጭ በዐለቶች መሃል እየተንፎለፎለ የደከሙትን፣ የዛሉትንና ከባድ ሸክም የተጫናቸውን ሕይወት የሚያድስ ጅረት ነው፡፡ ይህ ሕይወት ሰጭ ውሃ በመላው ምድር እስከሚሰራጭ ድረስ ወደፊት የሚገሰግስ፣ ጥልቅ፣ ሰፊና ሳያቋርጥ የሚፈስ ወንዝ ይሆናል፡፡ ይህ ፈሳሽ አረንጓዴውን ቀለምና ፍሬያማነተ ወደ ኋላው እየተወ፣ መንፈስ የሚያድሰውን ድምጽ እያሰማ መንገዱን ይዞ ወደፊት ይገሰግሳል፡፡ የወንዙ ዳር በሚዘናፈል አረንጓዴ ሣር የተሸፈነ፣ ዛፎቹ በደማቅ ቀለም ያጌጡ፣ አበቦች እዚህም እዚያም ሞልተውና ተትረፍርፈፈው የሚታዩበት ይሆናል፡፡ ምድሪቱ በበጋው ሐሩር ጠውልጋ ገጽታዋ አፈርማ ሲመስል ወንዙ የሚያልፍበት ሸለቆ ግን አረጓዴውን ቀለም እንደያዘ ይዘልቃል፡፡ ChSAmh 145.3
ከላይ የቀረበው እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅን ማንነት ያሳያል፡፡ የሚያነቃቃና ሕያው መርኅ የሚከተለው የክርስቶስ ኃይማኖት ወደ ሌሎች የሚሰራጭ፣ በሥራ የተጠመደና በመንፈሳዊ ኃይል የተሞላ ነው፡፡ ሰብዓዊው ልብ ሰማያዊ ተጽእኖ ለሆኑት ፍቅርና እውነት ክፍት ሲሆን እነዚህ መርኅዎች በበረሃ እንደሚፈስ ወንዝ አሁን ደረቅ ሆኖ በሚታየው የምድር ገጽታ ፍሬያማነት አብቦ እንዲታይና ልምላሜ እንዲመጣ ያደርጋሉ፡፡--Prophets and Kings, pp. 233, 234. ChSAmh 146.1