የክርስቲያን አገልግሎት
በወንጌል እንቅስቃሴ ላይ የተጋረጠው አደጋ
መሠራት ያለበትን ሥራ በመሥራቱ ረገድ እንቅስቃሴአችን ሲጨምርና ስኬታማነታችን ሲያይል በሰብዓዊው ዕቅድና ዘዴ መታመን አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አንርሳ፡፡ በቂ ጸሎት ያለመጸለይና የእምነት መጉደል አዝማሚያ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ ሲሆን ሥራችንን በብቸኝነት ውጤታማ ሊያደርግ በሚችለው በእግዚአብሔር ላይ የመተማመን ስሜት የማጣት አደጋ ይጋረጥብናል፡፡ ነገር ግን ይህ አዝማሚያ ቢሆንም እንኳ ሰብዓዊው መሣሪያ እጅግ አነስተኛ ብቻ የሥራ ድርሻ እንዳለው አድርገን አናስብ፡፡ በጭራሽ--አነስተኛ ሥራ መሥራት የለበትም፡፡ ይልቁንም ሰማያዊ ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን በመቀበል የላቀውን ተግባር ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡-Review and Herald, July 4, 1893. ChSAmh 135.1
ቤተ ክርስቲያን በመለኮታዊው ኃይል ተነሳስታ ጽኑ ተግባራት የም>ከናውንበትሕይወት ሰጪ ይል የሆነው መንፈስ ቅዱስ አባላቶቿ ነፍሳትን ለክርስቶስ እንዲማርኩ የሚያነሳሳበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ነገር ግን ይህ እንቅስቃሴ በሚስተዋልበት ወቅት አስተማማኝ ሁናቴ ላይ ሊገኙ የሚችሉት ባልተቆጠበ ጽኑ ጸሎት በእግዚአብሔር ላይ የሚተማመኑ ቅን ሠራተኞች ብቻ ናቸው፡፡ በሥራቸው ከመታበይ ወይም እንቅስቃሴአቸውን አዳኝ አድርገው ከመቁጠር ታቅበው በክርስቶስ ጸጋ እንዲድኑ ጽኑ ልመና ማድረግ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሥራውን የሚሠራው የእርሱ ኃይል መሆኑን መገንዘብ እንዲችሉ ያለማቋረጥ ወደ የሱስ መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሲሆን hብርን ሁሉ ለእግዚአብሔር መስጠት ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ ለማስፋፋት ወሳኝ ጥረት እንድናደርግ እንጠራለን፡፡ ከሰማዩ አባታችን ጋር በጸሎት መትጋት እጅግ አስፈላጊው ክፍል ይሆናል፡፡ ብቻችንን በስውር፣ ከቤተሰባችን ጋር እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን በጸሎት መትጋት አስፈላጊ ይሆናል፡፡-Review and Herald, July 4, 1893. ChSAmh 135.2
እንደ አይሁድ ምሑራን አስተሳሰብ ከሆነ የኃይማኖት ፍሬ ነገሩ የአገልግሎት ሽር ጉድ ነው፡፡ ከሌሎች የተሻሉ ኃይማኖተኛ መሆናቸውን ለማሳወቅ በውጪያዊ አገልግሎት ተማኑ፡፡ ስለዚህ ነፍሳቸውን ከእግዚአብሔር ለዩ፣ በራስ የመተማን ስሜት አደረባቸው፡፡ ይህ ዓይነት አደጋ አሁንም አለ፡፡ የሥራው ዓይነት እየጨመረ በሄደ መጠን ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚሠሩት ሥራ ስኬት ሲያገኝ በሰብዓዊ ዕቅድና ሥልት የመተማመን አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህም የጸሎትና የእምነት መቀነስ አዝማሚያ ይከሰታል፡፡ እኛም እንደ ደቀ መዛሙርቱ በእግዚአብሔር መተማመናችንን የመተውና ሥራችንን እንደ አዳኝ የመቁጠር አደጋ ያሰጋናል፡፡ ሥራውን የሚያሳካው የእርሱ ኃይል መሆኑን በመረዳት ሁል ጊዜ የሱስን መመልከት አለብን፡፡ ለጠፉት ነፍሳት ደኅንነት በቅንነት መሥራት ቢኖርብንም በእርጋታ ለማሰላሰል፣ ለመጸለይና የእግዚአብሔን ቃል ለማጥናት ጊዜ ሊኖረን ይገባል፡፡ በመጨረሻ ጥሩ ውጤት ለማስገኘት ብቃት የሚኖረው በብዙ ጸሎት የተከናወነና በክርስቶስ ጸጋ የተቀደሰ ሥራ ብቻ ነው፡፡The Desire of Ages, p. 362. ChSAmh 136.1