የክርስቲያን አገልግሎት
ለሐኬተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የቀረበ ተማጽኖ
አንድ መቶ ሠራተኞች በሥራው ላይ ሊማሩ ሲገባ ነገር ግን አንድ ብቻ የመገኘቱ ነገር እንቆቅልሽ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ተብለው በተጠሩ ዘንድ እየተስተዋለ ያለው ችላ ማለት፣ ግዴለሽነት፣ መቀዛቀዝና መፍዘዝ በመላው ሰማያዊ አካላት ላይ አድናቆት ፈጥሮአል፡፡ በእውነት ውስጥ ሕያው ኃይል አለ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 42. ChSAmh 122.2
ያለ ሥራ በስንፍና ተቀምጠን መዳን አንችልም፡፡ በእውነት የተለወጠ ሰው ከንቱና ጥቅመ ቢስ ሕይወት ይኖራል ተብሎ አይታመንም፡፡ እንደው እንደ ዋዛ እየተንሳፈፉ ሰማይ መግባት አይቻልም፡፡ ሰነፉ ወደዚያ ሊገባ አይችልም. . . በምድራዊው አገልግሎት ከእግዚአብሔር ጋር በአንድነት ለመሥራት ፈቃደኞች ያልሆኑ በሰማይም ከእርሱ ጋር ኅብረት ሊፈጥሩ አይችሉም፡፡ እነርሱን ወደ ሰማይ መውሰድ አስተማማኝ አይሆንም፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 280. ChSAmh 122.3
የቤተ ክርስቲያን አባላት በጨለማ ለሚገኙ ሕዝቦች አምላካዊውን መልእክት በማስተላለፉ ረገድ እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ መላው ሰማይ በአንክሮ እየተከታተለ ይገኛል፡፡Review and Herald, Feb. 27, 1894. ChSAmh 122.4
ግንኙነትዎ በመጫወቻ ሊያባብሉት ከሚችሉት ትንሽ ልጅ ጋር ሳይሆን ነገር ግን ከታላቁ አምላክ ጋር መሆኑን በአክብሮት ሊያጤኑ ይገባል፡፡ ደስ ሲሎት አገልግሎት የሚሰጡበት ደስ ሳይሎት ሲቀር ደግሞ የሚተዉት አይደለም --Testimonies, vol. 2, p. 221. ChSAmh 123.1
የሰማይ ኃይላት ከሰብዓዊ ወኪሎች ጋር አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን እድል ሲጠባበቁ ቢኖሩም የእነርሱን መገኘት ለይተን መመልከት አልቻልንም፡፡-Testimonies, vol. 6, p. 297. ChSAmh 123.2
ታላቁ ሥራ መሠራት ይችል ዘንድየሰማይ መላእክት ሰብዓዊ ወኪሎች የሆኑትን የቤተ ክርስቲያን አባላት ለረጅም ዘመናት ሲጠባበቁ ኖረዋል፡፡ እነሆ እርስዎን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡--Testimonies, vol. 9, pp. 46, 47. ChSAmh 123.3
እጅግ ብዙዎች ከኃላፊነት እየራቁና በመንፈሳዊው ሕይወት እየቀጨጩ አንዳችም ሳይሠሩ ወደ አምላካዊው የምጽአት ቀን እየተቃረቡ ይገኛሉ፡፡ ከአምላካዊው ሥራ ጋር በተያያዘ የሕይወት ታሪኮቻቸው ገጾች ከአሳዛኝ ክፍት ቦታ ውጪ አንዳች አልሰፈረባቸውም፡፡ በእግዚአብሔር የአትክልት ስፍራ የተተከሉ ዛፎች ቢሆኑም ነገር ግን በተንዠረገጉ ቅርንጫፎቻቸው ምድሩን እያጨለሙ፣ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎች ሊይዙት ይገባ የነበረውን መሬት የሚያጎሳቁሉ ናቸው፡፡-Review and Herald, May 22, 1888. ChSAmh 123.4
ለክርስቶስ አንዳችም ወይም ጥቂት ብቻ በሚሠሩ ላይ አደጋ ተጋርጦአል፡፡ ከፍ ያለ ምቹ ሁኔታና ዕድል ተፈጥሮላቸው እያለ በጸጥታ ከሚቀመጡ ነፍሳት ጋር አምላካዊው ጸጋ ለረጅም ዘመን አብሮ መዝለቅ አይችልም፡፡-Review and Herald, Aug. 22, 1899. ChSAmh 123.5
በከንቱ ጸጸት የምንሞላቀቅበትም ሆነ የምናንቀላፋበት ጊዜ ከዚህ በኋላ አይኖረንም፡፡ በዚህ ወቅት ለማንቀላፋት የሚደፍር መልካም መሥራትየሚችልበትን የከበረ _ ዕድል ያጣል፡፡ በታላቁ የመከር ወቅት ነዶ የምንሰበስብበት የተባረከና ምቹ ሁናቴ ተሰጥቶናል፡፡ እያንዳንዱ የዳነ ነፍስ ተወዳጁ የሱስ በሚጭንልን አክሊል ላይ የሚያንጸባርቅ ተጨማሪ ኮከብ ይሆናል፡፡ በተፋፋመው ውጊያ ወደፊት እየገፉ አዳዲስ ድሎችን ከማስመዝገብና ዘላለማዊ ምርኮዎችን ከመሰብሰብ ውጪ ሠይፉን በሰገባው ለማስቀመጥ ብርቱ ምኞት የሚያድርበት ይኖር ይሆን?-Review and Herald, Oct. 25, 1881. ChSAmh 124.1
የሰማይ መልእክተኞች ሥራቸውን በትክክል እየሠሩ ነው--እኛስ ምን እያደረግን እንገኛለን? _ ወንድሞችና እህቶች! ጊዜውን ትዋጁ ዘንድ እግዚአብሔር ጥሪ እያቀረበላችሁ ይገኛል፡፡ ወደ _ እርሱ ቅረቡ፡፡ የተሰጧችሁን መኪሊቶች ሥራ ላይ አውሉ፡፡ ከኃይማኖታዊ አስተምህሮዎቻችን ጋር የመተዋወቅ ዕድል ያገኙ ይህን ዕውቀት ለአምላካዊው ዓላማ ያውሉ፡፡Historical Sketches, p. 288. ChSAmh 124.2
“መንግሥትህ ትምጣ፣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” የሚለውን የጌታችንን ጸሎት የሚጸልዩ፤ የሚንቦገቦገውን የእውነትን ችቦ ወደ ሌሎች ለማዳረስ የበኩላቸውን እገዛ በማድረግ ፋንታ እንዴት ያለ አንዳች እንቅስቃሴ በየቤቶቻቸው ይቀመጣሉ? ሌሎችን ለመርዳት እያደረጉ ያለው እንቅስቃሴ እጅግ አነስተኛ ሆኖ እየታየ እግዚአብሔር እርስዎንና ቤተሰብዎን እንዲባርክ እጆችዎን በፊቱ ማንሳቱ አግባብ ይሆን?--Historical Sketches, p. 288. ChSAmh 124.3
አንዴ ቆም ብለው እንቅስቃሴ አልባውን አቋማቸውን መመልከት ቢችሉ እግዚአብሔር የሰጣቸውን መክሊቶች ጥቅም ላይ ባለማዋል የቸልተኝነት ኃጢአት እየሠሩ መሆናቸውን የሚያስተውሉ ወገኖች በመካከላችን አሉ፡፡ ወንድሞችና እህቶች! አዳኛችሁና ቅዱሳን መላእክት በልባችሁ መደንደን ክፉኛ ያዝናሉ፡፡ ክርስቶስ ነፍሳትን ለማዳን ሲል የገዛ ሕይወቱን ቢሰጥም ነገር ግን የእርሱን ፍቅር የቀመሱት እርስዎ የጸጋውን ባርኮት ወደ ሌሎች ለማስተላለፍ እያደረጉ ያለው ጥረት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ግዴለሽነትና ችላ ባይነት መላእክትን በእጅጉ ያስደንቃቸዋል፡፡ በፍርድ ቀን ቸልተኝነት ካሳዩአቸው ነፍሳት ጋር መጋፈጥዎ የግድ ይሆናል፡፡ በዚያ ታላቅ ቀን የገዛ ሕሊናዎ ጥፋተኛ ያደርጎታል፣ ይኮንኖታልም፡፡ አቤቱ ጌታ አሁኑኑ ወደ ንስሐ ይምራዎ፡፡ ጌታ በወይን ተክሉ ዙሪያ እንዲሠሩ የሰጣቸውን ሥራ ችላ ያሉትን ሕዝቦቹን ይቅር ይበል!--Testimonies, vol. 6, pp. 425, 426. ChSAmh 124.4
መክሊቶችን ጉድጓድ ቆፍሮ መቅበር ሳይሆን ነግዶ የማትረፍን አስፈላጊነት ሰነፉ የቤተ ክርስቲያን አባል ማስተዋል እንዲችል ምን ማለት እንችላለን? በሰማይ መንግሥት ውስጥ አንድም ሥራ ፈት ወይም አኬተኛ አይኖርም፡፡ እግዚአብሔር አስፈላጊ የሆኑትን ጉዳዮች በሙሉ ባንቀላፉት ቤተ ክርስቲያኖች ፊት ያኖራል! እነሆ ጽዮን ከእንቅልፏ ነቅታና ያማረውን ሸማ ለብሳ ታንጸባርቃለች! --Testimonies, vol. 6, p. 434. ChSAmh 125.1
እርስዎ በጨለማ እያሉ የተሠራሎት ሥራ ዓይነት እውነትን ለማያውቁ ልንሠራ የሚገባን ሥራ አለ፡፡ ለማንቀላፋትም ሆነ ለስንፍና ጊዜ የለንም፡፡ የቤቱ ባለቤት እያንዳንዱ የሚሠራውን ሥራ ሰጥቶአል፡፡ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አናፈግፍግ፡፡ በየቀኑ አዳዲስ የተለወጡ ነፍሳት እንዲኖሩን እንሻለን፡፡ አያሌ ነፍሳትን ማዳኛ መሣሪያ መሆን እንችል ዘንድ የየሱስ ፍቅር የልብ ትርታችን እንዲሆን ምኞታችን ነው፡፡-Review and Herald, June 10, 1880. ChSAmh 125.2
የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆኑ የሚያምኑ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች እያንዳንዱ ነፍስ ከማንኛውም እርክስና መራቅ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የተትረፈረፈ የልግስና፣ ራስን የመካድና የሰብዓዊነት ሥራ ይሥራ፡፡ ጌታ ስለ አገልግሎታችን ሊያስጠነቅቁን እንዲችሉ አድርጎ የአእምሮአችንን ሕግጋትና አካሄዶች ከፊታችን አኑሮአል “ላለው ይጨመርለታልና፤ ከሌለው ሁሉ ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል”፡፡ የተሰጧቸውን መልካም ዕድሎች ጥቅም ላይ በማዋል የማያበለጽጓቸው፣ ጸጋውን የማይለማመዱና ይህን ለማድረግ አነስተኛ ዝንባሌ ያላቸው በስተመጨረሻ እንቅልፋምና ልፍስፍስ በመሆን በአንድ ወቅት የራሳቸው አድርገዋቸው የነበሩትን ሁሉ ያጣሉ፡፡ አስቸጋሪ ሁኔታና ፈተና ሲገጥማቸው ጸንተው ለመቆም የሚያስችላቸው እያደገ የሚሄድ መለኮታዊ ዕውቀት፣ ለወደፊት ብርታት የሚሆናቸው ከፍ ያለ ተሞክሮ ባለቤት እንዲሆኑ -ራሳቸውን አሳልፎ የመስጠት ሁኔታ አይስተዋልባቸውም፡፡ በዚህ ረድፍ የሚገኙ አማኞች ነፍሳቸውን ከዘላለማዊው ዐለት ጋር ባለማስተሳሰራቸውና የቆሙበትን መሰረት የተረጋገጠ የማድረጉን አስፈላጊነት መመልከት ባለመቻላቸው ስደትና ፈተና ሲመጣ ወኔም ሆነ እምነት ስለሚያጡ ከሥረ ከመሰረታቸው የተናጉ ይሆናሉ፡:Review and Herald, March 27, 1894. ChSAmh 125.3
የቤተሰብ አባሎቻችን፣ ምናልባትም የገዛ ልጆቻችን ወይም በአንድ ገበታ አብረን የበላንና የጠጣን ወገኖች ባለመዳናቸው ምክንያት በታላቁ የመጨረሻ ቀን ለዘላለም ሲለዩን መመልከት እንዴት አስደንጋጭና አስከፊ ይሆን! ከዚያም ራሳችንን እንዲህ ብለን እንጠይቃለን—የክርስቶስ ኃይማኖት ለእነርሱ ያልጣመበት ምክንያት ምን ነበርየእኔ ትዕግሥት ማጣት? የክርስቲያን ጸባይ ስላልነበረኝ? ወይስ እኔነትን በቁጥጥር ስር ማዋል አለመቻሌ? ChSAmh 126.1
የምንሠራበት ጊዜ እጅግ አነስተኛ እንደመሆኑ ዓለም በቅርቡ ስለሚገለጠው ጌታ የማስጠንቀቂያ መልእክት ሊሰጠው የግድ ነው፡፡ በቅድሚያ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቅ ለራሳችን በመሻት፤ በመቀጠል ያገኘነውን ብርሃን ለሌሎች እንድናጋራ ጥሪ ከቀረበልን ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ከፍተኛ የሥራ ድርሻ የተሰጣቸው፣ ታላቅ ብርሃን የተቀበና በእውነት ላይ የተመሰረቱ ሕዝቦቹ ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች እንዲሠሩ እግዚአብሔር አሁን ጥሪ እያቀረበላቸው ይገኛል፡፡ እያንዳንዱ ችሎታ፣ ጉልበተ፣ መክሊት እንዲሁም ለሌሎች መልካም እንድናደርግ የተሰጠን ብርሃን በጥቅም ላይ ይዋል፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንጂ ሰባኪዎች ለመሆን አንሞክር፡፡ Southern Watchman, June 20, 1905. ChSAmh 126.2