የክርስቲያን አገልግሎት

84/246

የሰማይ መዝገብ

ዓለም በቅድስና የሚመላለሱ፣ በየቤቱ አገልግሎት የሚሰጡ ወንጌላውያንን ትሻለች፡፡ የወንጌላዊ መንፈስ የሌለው ማንም ሰው እንደ ክርስቲያን በሰማይ መዝገብ ላይ ስሙ ሊሰፍር አይችልም፡፡— Review and Herald, Aug. 23, 1892. ChSAmh 119.3

የቤተ ክርስቲያን አባላት ይህን አገልግሎት በየግልላቸው ካልጀመሩ ከእግዚአብሔር ጋር ሕያው ግንኙነት እንደሌላቸው ያሳያሉ፡፡ በሰማይ መዝገብ ስማቸው ታካች አገልጋይ በሚል ይሰፍራል፡፡-Testimonies, vol. 5, pp. 462, 463. ChSAmh 119.4

ሥራው የእግዚአብሔር መሆኑን እያወቁ ራሳቸውን ከሥራው የሚነጥሉና እገዛ ለማድረግ እምቢተኝነታቸውን የሚያሳዩ ጥቂት ግለሰቦች በእያንዳንዱ ኃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ይስተዋላሉ፡፡ እነዚህ ድርጊታቸው አንዳችም ስህተት በማያወቀው በሰማያዊው መዝገብ ላይ መስፈሩንና በዚያ መዳኘታቸውን ቢያስታውሱ መልካም በሆነላቸው ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር አገልግሎት መስጠት የምንችልበትን እያንዳንዱን መልካም ዕድል ቸል ማለት በመጽሐፉ ላይ የሚሰፍር ሲሆን እንዲሁም እያንዳንዱ የእምነትና የፍቅር ድርጊት በዘላለማዊው መጽሐፍ ላይ ተመዝግቦ ይታወሳል፡፡-Prophets and Kings, p. 639. ChSAmh 119.5

በወርሃ ጥቅምት 23/1879 ስምንት ሰዓት ገደማ የጌታ መንፈስ አርፎብኝ ወደፊት በፍርድ ወቅት የሚሆነውን ትዕይንት ተመለከትኩ. . . አስር ሺ ጊዜ አስር ሺ የሚሆኑ በታላቁ ዙፋን ፊት ተሰብስበው የነበረ ሲሆን በዙፋኑ ላይ ንጉሣዊ ገጽታ የተላበሰ ሰው ተቀምጦ ነበር፡፡ ያሌ መጻሕፍት ከፊቱ ነበሩ፡፡ በእያንዳንዱ መጽሐፍ ሽፋን ላይ የሚንበለበል እሳት የሚመስሉ “የሰማይ መዝገቦች” የሚል ወርቃማ ቃላት ተጽፎባቸው ነበር፡፡ ከእነዚህ መጻሕፍት አንዱና—እውነትንእናምናለን የሚሉ ሰዎች ስም የሰፈረበት ተከፈተ፡፡ በቅጽበት በዙፋኑ አካባቢ የነበሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እጅግ ብዙዎች ከዓይኔ ተሰወሩና የብርሐንና የእውነት ልጆች መሆናቸው በይፋ የተነገረላቸው ብቻ ትኩረቴን ሳቡት…. ChSAmh 120.1

ሌላ መጽሐፍ ተከፈተ፡፡ በዚህኛው ውስጥ እውነትን እናምናለን የሚሉ ሰዎች ኃጢአት ተጽፎ ነበር፡፡ ራስ ወዳድነት ከሁሉ የበላይ ሆኖ የሰፈረ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ኃጢአት ተከታትሎ ቀረቦ ነበር፡፡ አንደኛው የኅብረተሰብ ክፍል ሸክም የተጫነው ሆኖ ተመዝግቦ ነበር፡፡ ወደ ውስጥ ጠልቆ የሚገባ የሚመስለው የፈራጁ ዐይን በእነዚህ ላይ ባረፈ ጊዜ የቸልተኝነት ኃጢአቶቻቸው በጉልህ ተገለጡ፡፡ ፊታቸው ገርጥቶና ከንፈሮቻቸው እየተንቀጠቀጡ በተሰጣቸው የተቀደሰ መታመን ላይ ክህደተ መፈጸማቸውን አመኑ፡፡ ማስጠንቀቂያዎችና መልካም ዕድሎች ተሰጠተዋቸው የነበረ ቢሆንም አክብረው አልተቀበሏቸውም ወይም አላሻሻሉም፡፡ አሁን የእግዚአብሔርን ምኅረት ምን ያህል አልፈው እንደሄዱ መመልከት ችለዋል፡፡ ይዘውት ከኖሩት የላሸቀ ሞራል አኳያ እንዲv ያለውን ኑዛዜ ከዚህ ቀደም አድርገው አለማወቃቸው እውነት ቢሆንም ፍሬ ባለማፍራታቸውና የተሰጣቸውን መክሊት ጥቅም ላይ ባለማዋላቸው እንደ በለሷ ዛፍ ርግማን ደረሰባቸው፡፡ ይሄኛው የኅበረተሰብ ክፍል ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግ ለግል ጥቅሙ ብቻ የሠራ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ፊት የከበሩ ወይም አምላካዊውን ነገሮች ለራሳቸው ያደረጉ አልነበሩም፡፡ ምንም እንኳ ራሳቸውን የክርስቶስ አገልጋይ ብለው ቢጠሩም ነገር ግን አንድ እንኳ ነፍስ አልመለሱም፡፡ ከእግዚአብሔር የተበደሯቸውን ነገሮች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መያዝ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ጭምር በመግታታቸው አምላካዊው ሥራ በእነርሱ ጥረት ብቻ የተወሰነ ቢሆን ኖሮ በጠወለገ ነበር. የራሳቸውን በስስት የተሞላ ጊዜያዊ ፍላጎት ለሟሟላት ወዲያና ወዲህ እየተራወጡ ሌሎች በጌታ የወይን ተክል ዙሪያ ተሰማርተው ከባዱን የኃላፊነት ሸክም እንዲሸከሙ ፈቅደው ነበር. ChSAmh 120.2

ፍርድ ሰጪው ዳኛ “ሁሉም ሰው በሥራው ይፈረድበታል፤ በእምነቱ ግን ይጸድቃል” ሲል ተናገረ፡፡ እያንዳንዱ ሰው አምላካዊውን ሥራ እንዲያበረታታና ለባልንጀራው ደኅንነት እንዲሠራ ለሁሉም ስምሙ ሆኖ በተሰጠው በዚህ በጥበብ የተሞላ አገልግሎት ላይ የታየው ቸልተኝነት እጅግ ግልጽ ሆኖ ቀርቦአል፡፡ እያንዳንዱ አማኝ ለደኻው፣ ለተጎዳውና ለተጠቃው ደግነትንና የድጋፍ ስሜትን እያሳየ በወንጌል አገልግሎት እንዲሳተፍ፣ አምላካዊውን ሥራ በገንዘቡ እየደገፈ ለቤተሰቡና ለጎረቤቱ ሕያው አገልግሎት እንዲሰጥ ተጠርቶአል፡፡ ነገር ግን የተጣለባቸውን ኃላፊነት ባተወጡት ላይ እንደ ሜሮዝ ሁሉ አምላዊው እርግማን በእነርሱ ላይ ያርፋል፡፡ በምድራዊው ህይወት ታላቅ ትርፍ የሚያስገኘውን ሥራ በመውደዳቸውበሰማያዊው መዝገብ፣ በስማቸው ተቃራኒ ሊሰፍር በሚገባው መልካም ሥራ ላይ አሳዛኝ ባዶ ቦታ ነበር፡፡--Testimonies, vol. 4, pp. 384-386. ChSAmh 121.1