የክርስቲያን አገልግሎት
ለመዘግየት ጊዜ የለም
“ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል” (ሶፎ. 1፡4)፡፡ የወንጌልን ጫማ ተጫምተንና የወቅቱን ሁናቴ አስተውለን ወደፊት ለማምራት እንዘጋጅ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 48. ChSAmh 107.2
የቤተ ክርስቲያን አባላት. . . የጌታን ትእዛዛት እየጠበቁ ተስፈንጥረው ወደ ተግባር ለመግባት ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ለመሠራት ተራ እየጠበቀ ያለውን ሥራ ስንመለከት ዐይኖቻችንን በየሱስ ላይ እንደተከልን እንሥራው. . . እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል በብርቱ እንቅስቃሴ ላይ ቢሆን ኖሮ ወንጌል ለመላው አገራት፣ ሕዝቦች፣ ብሔሮችና ቋንቋዎች በፍጥነት ተሰብኮ ባበቃ ነበር፡፡Testimonies, vol. 9, p. 32. ChSAmh 107.3
የምድር ታሪክ መደምደሚያ ወደሆነው ወቅት እየተቃረብን እንገኛለን፡፡ ለኃጢአትኛው ዓለም የሚሰጥ የሥራው መደምደሚያ የሆነው የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ መልእክት ታላቅ ሥራ ከፊት ለፊታችን ይጠብቀናል፡፡ ከግብርና፣ ከወይን ተhል ስፍራና ከሌሎች አያሌ የሥራ ቅርንጫፎች ተወስደው ይህን መልእክት ለዓለም እንዲሰጡ በጌታ የሚላኩ ሰዎች አሉ፡፡Testimonies, vol. 7, p. 270. ChSAmh 108.1
የማስጠንቀቂያው ደወል በመላው የምድር ክፍል ይደመጣል፡፡ የጌታ ቀን እጅግ መቃረቡ ለሕዝቦች ሁሉ ይነገራል፡፡ ማንም ማስጠንቀቂያውን ሳይሰማ አይቅር፡፡ ምናልባት በስህተት ውስጥ ከወደቁ ምስኪን ነፍሳት ወይም ኋላ ቀር አረመኔአዊ ተግባራትን ይፈጽሙ ከነበሩ ጨካኞች አንዱ ነበርን፡፡ አምላካዊው እውነት እንደሚነግረን እኛ ከሁሉም የላቀውን በመቀበላችን ለሌሎች ማስተላለፍ የሚገባን ባለዕዳዎች ነን፡፡ Testimonies, vol. 6, p. 22. ChSAmh 108.2
ወንድሞቼና እህቶቼ! ጊዜአችሁንና ጉልበታችሁን ለግል ጥቅማችሁ ለማዋል እጅግ ረፍዶአል፡፡ የመጨረሻው ቀን የከበረው ሰማያዊው ስጦታ የሌላችሁና የተራቁታችሁ ሆናችሁ አንዳያገኛችሁ፡፡ የመስቀሉን ድል ይዛችሁ ወደፊት ስትገሰግሱ፣ ለነፍሳት ለመንገር ጥረት ስታደርጉና ለባልንጀራችሁ ደኅንነት ስትሠሩ--አገልግሎታችሁ በእሳት ተፈትኖ ያለፈ ይሆናል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 56. ChSAmh 108.3
ይህን አስተምህሮ፣ መልእክት፣ መርኅና ደንብ አንድም ሳይቀር በፍጥነት ልናሰራጭ ይገባል፡፡ ሰዎች በቅርቡ ታላላቅ ውሳኔዎችን ለመወሰን ይገደዳሉ፡፡ በማስተዋል በትክክለኛው አቅጣጫ መቆማቸውንና እውነትን የሚገነዘቡባቸውን ዕድሎች ማግኘታቸውን መፈተሽ የእኛ ተግባር ይሆናል፡፡ የምህረት ጊዜ ሳያበቃ ሕዝቡ በጽናትና በጥበብ እንዲሠራ ጌታ ጥሪውን ያቀርባል፡፡Testimonies, vol. 9, pp. 126, 127. ChSAmh 108.4
አንድም የምናባክነው ጊዜ የለንም፡፡ መጨረሻው ተቃርቦአል፡፡ እውነት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው የሚተላለፍበትና የሚሰራጭበት መንገድ በግራም ሆነ በቀኝ በቅርቡ በአደጋ የታጠረ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ነገር የጌታ መልእክተኞች አሁን መሥራት የሚችሉትን ነገር እንዳይሠሩ መንገዱን የሚዘጋ ይሆናል፡፡ ከፊት ለፊታችን ያለውን ሥራ ቅንና ሚዛናዊ በሆነ ዓይን እየተመለከትን በተቻለን ፍጥነት በውጊያ ወደፊት መገስገስ ይኖርብናል፡፡ የጨለማው ኃይላት በማያባራ ብርታት እየሠሩ መሆናቸውንና ሰይጣን በአደን ላይ እንዳለ ተኩላ አንቀላፍተው ወደሚገኙ በዝግታ እያመራ መሆኑን ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ብርሃን ተመልክቻለሁ፡፡ ትንሽ ቆየት ብሎ ማሰብ ከምንችለው በላይ አዳጋች ሊሆኑ የሚችሉ አሁን ለሌሎች ማስተላለፍ ያለብን ማስጠንቀቂያዎችና ልንሠራቸው የሚገቡ ሥራዎች ተሰጥተውናል፡፡ ዓይኖቻችንን በመሪያችን የሱስ ላይ ተክለን ዓላማችንን ለማሳካት ተግተን በትዕግሥት በመሥራት በድል አድራጊነት ወደፊት እንድንገፋና ብርሃናችንን እንድናበራ እግዚአብሔር ይረዳናል፡፡- Testimonies, vol. 6, p. 22. ChSAmh 109.1
መዘግየት ብርቱ አደጋ ያስከትላል፡፡ ያ አግኝተኸው የነበረ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የከፈትhለት ሰው ልትደርስበት ከምትችለው ርቀት ባሻገር አልፎ ሊሄድ ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ባላንጣ የሆነው ሰይጣን ያዘጋጀውን መሰናhል ነገ በዚህ ሰው እግሮች ስር ለማኖር ሊንቀሳቀስ ይችላል፡፡ ወዲያውኑ ወደ ሥራ መሰማራት እንጂ አንድ ቀንስ ቢሆን ለምን እንዘገያለን?--Testimonies, vol. 6, p. 443. ChSAmh 109.2
በሁሉም ዘመን ያሉ የክርስቶስ ተከታዮች ንቃትና እምነት እንዲኖራቸው ይጠየቃሉ፡፡ ዛሬ እውነትን፣ የላቀውን ብርሃንና በእጅጉ አስፈላጊ የሆነ ሥራ ይዘን በምድር መጨረሻ ላይ የምንገኝ እንደመሆኑ ታማኝነታችንን በእጥፍ ሳደግ ይጠበቅብናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ችሎታው የሚፈቅደውን የላቀ ሥራ መሥራት ይኖርበታል፡፡ ወንድሜ ሆይ! አሁን ወደ ኋላ የምታፈገፍግ ከሆነ የገዛ ደኅንነትህን አደጋ ላይ ትጥላለህ፡፡ እግዚአብሔር የመደበልህን ሥራ ከመሥራት የምትሰናከል ከሆነ ተጠያቂ ተሆንበታለህ፡፡--Testimonies, vol. 5, pp. 460, 461. ChSAmh 109.3
ብርቱ ጥያቄዎች እነሆዘላለማዊ ሕይወት ከፊታችን ተዘጋጅቶ መጋረጃው ሊገለጥ ተቃርቦአል፡፡ በዙሪያችን ያሉ ነፍሳት እየጠፉ እኛ ግን ከራስ ወዳዱ ከንቱ ምቾት ጋር እንዴት ተጣብቀን መኖር እንዳለብን እያሰብን ይሆን? ለሆኑ ልባችን ፍጹም ርኅራኄ የለሽ እየሆነ ነው? ስለ ሌሎች ደኅንነት የምንሠራው ሥራ እንዳለን ማየትና ማስተዋል ተስኖናል? ወንድሞቼና እህቶቼ—ዓይን እያላቸው ከማያዩና ጆሮ እያላቸው ከማይሰሙ _ መካከል _ እንሆን? እግዚአብሔር ፈቃዱን የሚያስተውሉበት ዕውቀት የሰጥዎ በከንቱ ነውን? መጨረሻው ስለ መቃረብ አስመልክቶ በማስጠንቀቂያ ላይ ማስጠንቀቂያን አhሎ የሰጠዎት በከንቱ ነው? በምድር ላይ እየመጣ ስላለው ነገር በቃሉ ይፋ ያደረጋቸውን ድንጋጌዎች ያምናሉ? አምላካዊው ፍርድ በምድር ነዋሪዎች ላይ እየተሰጠ መሆኑን ያምናሉ? ታዲያ ቸልተኛና ግዴለሽ ሆነው እንዴት ያለ ሥራ ይቀመጣሉ? Testimonies, vol. 9, pp. 26, 27. ChSAmh 110.1