የክርስቲያን አገልግሎት

76/246

ለዚህ ሰዓት አስፈላጊ ማስጠንቀቂያ

ሥራውን በዘዴና በብልሃት መሥራት የሚያስፈልግ ቢሆንም ነገር ግን አንዳንዶች ዕቅድ ሲያወጡና ሲነድፉ ረጅም ጊዜያቶችን በመውሰዳቸው ሰይጣን ዘር የሚዘራበትን አእምሮ በሚያነሆልሉ ተረቶች እየሞላ የሰዎችም ትኩረት በአታላዩ አሳች ተግባራት እየተመሰጠ ይገኛል፡፡-Review and Herald, March 13, 1888. ChSAmh 105.1

በሥርዓት የሚራ መዋቅራዊ አደረጃጀት እጅግ አስፈላz በሆነበት በዚህ ወቅት ሰይጣን ወደ እግዚአብሔር ሕዝቦች ሰርጎ ገብቶ የተጭበረበረውን የአመጻ ተግባሩን ለማከናወን ብርቱ ኃይል ሊሆነው የሚችለውን ይህን አደረጃጀት ማቃወስ ከቻለ ምን ያህል ይደሰት! በመዋቅራዊው አደረጃጀት ሥርዓትም ሆነ በማስተዋልና በጥንቃቄ በተገነቡት ላይ የመፈረካከስ አደጋ እንዳይደርስ ሚዛናችንን ጠብቀን መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡ በዚህ ሰዓት በእንቅስቃሴ የሚገኘውን ሥራ በቁጥጥራቸው ስር ለማዋል ምኞት ላላቸው--ከሥነ ሥርዓት ውጪ ለሆኑ አካሎች የሥራ ፈቃድ ሊሰጥ አይገባም::--Gospel Workers, p. 487. ChSAmh 105.2