የክርስቲያን አገልግሎት

72/246

መልካም ምሳሌ መሆን

ሐዋርያው ጳውሎስ በወንጌል ሥራ ወደ ጌታ ያመጣቸው ወገኖች መንፈሳዊ ደኅንነት ብርቱ ሸክም ሆኖ ይሰማው ነበር፡፡ እነዚህ ሕዝቦች እርሱን በላከው ብቸኛና እውነተኛ አምላክ—በየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት እንዲያድጉ ምኞቱ ነበር፡፡ ጳውሎስ አነስተኛ አባላት ከነበሯቸው የሱስን ከሚወዱ ወንዶችና ሴቶች ጋር አብልጦ እየተገናኘ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሕያው ግኝኙነት እንዲመሰርትና ፈቃዱን እንዲያስተምራቸው በተደጋጋሚ አብሮአቸው ይጸልይ ነበር፡፡ የወንጌልን ብርሃን ለሌሎች በሚፈነጥቁበት መንገድ ዙሪያ የሚመክርባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ነበሩ፡፡ ሐዋርያው አገልግሎት ከሰጣቸው ከእነዚህ ወገኖች ተለይቶ በሚሄድ ጊዜ እግዚአብሔር ከክፉ እንዲጠብቃቸው፣ በጽናት እንዲያቆማቸውና ንቁ ወንጌላውያን መሆን እንዲችሉ ይለምንላቸው ነበር፡፡The Acts of the Apostles, p. 262. ChSAmh 99.1