የክርስቲያን አገልግሎት

50/246

የዓለም በጦርነት መንፈስ መታወክ

ይህች ዓለም በጦርነት መንፈስ እየታወከች ትገኛለች፡፡ የዳንኤል መጽሐፍ አስራ አንደኛው ምዕራፍ ፍጻሜ ወደ ማግኘቱ እየተቃረበ ነው፡፡ በትንቢቱ የተነገሩት የመከራ ትዕይንቶች በቅርቡ እውን ይሆናሉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 14. ChSAmh 75.2

በከፍተኛ ውዥንብር ውስጥ የሚገኙትን የምድር ነዋሪዎች ስመለከት ጦርነት፣ ደም መፋሰስ፣ መደኽየት፣እጦት፣ረሐብና ቸነፈር በምድር ተንሰራፍቶ ነበር. . . ከዚያም ትኩረቴ ወደ ሌላ ትዕይንት እንዲዞር ተደረገ፡፡ ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ ሰላም የሰፈነበት ወቅት የሚኖር ይመስላል፡፡ የምድርን ነዋሪዎች ዳግኛ ተመለከትኳቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ሁሉም ነገር መልሶ ብርቱ ውዥንብር ውስጥ ወደቀ፡፡ ሁከት፣ ጦርነት፣ ደም መፋሰስ፣ ረሐብና መቅሰፍት በየቦታው ይታይ ነበር፡፡ ሌሎች ሕዝቦችም የዚህ ውጊያና ግራ መጋባት ተካፋይ ሆነዋል፡፡ ጦርነት የረሐብ መንስኤ ሲሆን--እጦትና ደም መፋሰስ ደግሞ የመቅሰፍት ምክንያት ሆነው ነበር፡፡ ከዚያም የሰዎች ልብ በፍርሐት በመራዱ “በዓለም ላይ ምን ይመጣ ይሆን እያሉ በመጠባበቅ ይዝላሉ”- Testimonies, vol. 1, p. 268. ChSAmh 75.3