የክርስቲያን አገልግሎት
እንደ ወረርሽኝ በሽታ እየተዛመተ ያለው ወንጀል
በየቦታው የሚገኙ አስተዋይና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎችን የሚያሸብርወንጀል እንደ ወረርሽኝ በሽታ ከአንዱ ወደ ሌላው የሚዛመትበት ዘመን መሃል እንገኛለን፡፡ ዓለምን በቁጥጥሩ ስር ያዋለው ሙስና ያካበተው ኃይል ሰብዓዊው ብዕር ሊገልጸው ከሚችለው በላይ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቀን ከየራሱ አዳዲስ የፖለቲካዊ ሴራ፣ በጥቅም መደለልና ማጭበርበር ጋር ይîለጣል፡፡ እያንዳንዱ ቀን ቀድሞ የተመዘገበውን አኻዝ የሚሰብር የአመጻ ተግባር ይፈጸምበታል፡፡ ሕገወጥነት፣ ለሰብዓዊው ሥቃይ ርኅራኄ የለሽ መሆን፣ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የሰብዓዊውን ሕይወት መቅጠፍ፣ የአእምሮ መታወክና ራስን ማጥፋት የየዕለት ክስተቶች ሆነዋል፡፡ ሰብዓዊውን አእምሮ ለማዛባት፣ ብልሹ ለማድረግ፣ ለማርከስና አካልን ለማውደም የሰይጣን ወኪሎች ከመቼውም ጊዜ በላቀ ከሰዎች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን ሊጠራጠር የሚችል ይኖር ይሆን? Ministry of Healing, pp. 142, 143. ChSAmh 73.1
የሕገ-አልበኝነት መንፈስ በመላው አገራት እየተንሰራፋ ይገኛል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ በዓለም ላይ እንደ ወረርሽኝ እየተዛመቱ ያሉ፤ እንዲህ ተብለው ሊገለጹ የማይችሉ፤ የፍትዎት እሳትና ሕገ-አልበኝነት፤ አንዴ ከቁጥጥር ውጪ ከወጡ ምድርን በወዮታና በውድመት ይሞሏታል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ስለ ጥንቱ ዓለም የቀረበው ሥዕላዊ መግለጫ የዛሬው ዘመናዊ ማኅበረሰብ በፍጥነት እያመራበት ያለውን አቅጣጫ በተጨባጭ ያሳያል፡፡ ዛሬ በዚህ ዘመን እንኳ ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው በሚጠሩ ማኅበረሰቦች ምድር ላይ የጥንቱ ዓለም ኃጢአተኞች የጠፉበት ዓይነት አስከፊ ወንጀሎች ይፈጸማሉ፡፡ እግዚአብሔር የጥፋት ውሃን ከማምጣቱ አስቀድሞ ዓለም ከኃጢአት መንገድ ተመልሶ ንስሐ እንዲገባና ከመጣው ቁጣ እንዲያመልጥ ለማስጠንቀቅ ኖኅን ላከ፡፡ በተመሳሳይ ክርስቶስ ዳግም የሚገለጽበት ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ ህዝቡ ለዚያ ታላቅ ክስተት ይዘጋጅ ዘንድ ጌታ አገልጋዮቹን ከማስጠንቀቂያ መልእክት ጋር ይልካቸዋል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህዝቦች የእግዚአብሔርን ሕግ ሲተላለፉ ኖረዋል፡፡ አሁን ግን ቅዱሱን ትእዛዝ ይጠብቁ ዘንድ ጌታ በምህረት ውስጥ ሆኖ ጥሪ ያደርግላቸዋል፡፡ የኃጢአት መንገዳቸውን ትተው በክርስቶስ በሚኖራቸው እምነት ወደ እግዚብሔር ፊት በመቅረብ ለመተላለፋቸው ንስሐ የሚገቡ ሁሉ ይቅርታ ያገኛሉ፡፡ የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት ገጽ፡ 105-106: ChSAmh 73.2
ነገሮች የሚገኙበት ሁናቴ ከፊት ለፊታችን የተጋረጡትን አስቸጋሪ ጊዜያቶች ያሳዩናል፡፡ በየቀኑ እየታተሙ የሚወጡ ጋዜጦችና የመገናኛ ብዙሃን በቅርቡ አስከፊ ውዝግብ ሊፈነዳ እንደሚችል ሰፊ ሽፋን እየሰጡ ናቸው፡፡ ዐይን ያወጡ የዝርፊያ ተግባራት በተደጋጋሚ ሲከሰቱ እየተመለከትን ነው፡፡ ድብድብ የተለመደ ተግባር ሆኖአል፡፡ ስርቆትና ግድያ በብዙዎች እጅ እየተፈጸመ ነው፡፡ በአጋንንት የተያዙ ሰዎች የወንዶችን፣ የሴቶችንና የለጋ ህፃናትን ህይወት እየቀጠፉ ነው፡፡ ሰዎች በመጥፎ ድርጊቶች እየነሆለሉና በእያንዳንዱ ክፉ ዝርያ እየተሸነፉ ነው፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 11. ChSAmh 74.1