የክርስቲያን አገልግሎት

41/246

ማራኪው ሕልም

በወርሐ መስከረም 29/1886 በተሰጠኝ ሕልም ከአያሌ ሐዝቦች ጋር ሆኜ የእንጆሪ ፍሬዎችን ለመልቀም ፍለጋ ላይ ነበርን፡፡ ይህን ፍራፍሬ ለመልቀም የሚያግዙ ብዙ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ነበሩ፡፡ የምንገኘው በከተማ ውስጥ ሲሆን እኛን ማስተናገድ የሚችል በቂ ስፍራ ያለ አይመስልም፡፡ መስኮች፣ ውብ ጫካዎችና በሚገባ የተያዙ የአትክልት ስፍራዎች በከተማዋ የቅርብ ዳርቻዎች ነበሩ፡፡ ለእኛ የሚሆን ስንቅ የተጫነ አንድ ተለቅ ያለ ጋሪ ከፊታችን ይሄዳል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ጋሪው በመቆሙ ሕዝቡ ፍራፍሬውን ፍለጋ በየአቅጣጫው ተበታተነ፡፡ ጋሪው በቆመበት ዙሪያ በሚገኙ ትናንሽና ዘለግ ያሉ ቁጥቋጦዎች ላይ ማራኪ ፍሬዎች ተንዠርገው ይታዩ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሕዝቡ በመጓዙ ፍሬዎቹን መመልከት የሚችልበት ርቀት ላይ አልነበረም፡፡ አጠገቤ የነበሩትን ፍሬዎች መልቀም ብጀምርም የበሰሉት ፍሬዎች ካልበሰሉት ጋር በመጣመራቸው የበሰለውን ነጥዬ ለመቅጠፍ በእጅጉ መጠንቀቅ ነበረብኝ፡፡ ስለዚህ ከአንዱ ዘለላ መልቀም የቻልኩት አንድ ወይም ሁለት ፍሬዎችን ብቻ ነበር፡፡ ChSAmh 62.2

አንዳንዶቹ ፍሬዎች እጅግ ከመብሰላቸው የተነሳ መሬቱ ላይ ተንጠባጥበው ግማሽ የሚያህለው ክፍል በትናንሽ ነፍሳትና ትሎች ተበልቶ ነበር፡፡ “ቀደም ተብሎ ወደዚህ የእርሻ ቦታ ቢገባ ኖሮ እነዚህ ሁሉ የከበሩ ፍሬዎች መትረፍ በቻሉ ነበር! አሁን ግን ጊዜው አልፎአል፡፡ ይህም ቢሆን ምናልባት ከመካከላቸው ያልተበላሹ ፍሬዎችን ማግኘት ብችል ብለቅማቸውበእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል የሚስተዋሉ ሁናቴዎች ይሻላል፡፡ ሁሉም ፍሬዎች ቢበሰብሱ እንኳ ወንድሞች በጣም ባይዘገዩ ኖሮ ሊያገኙ ይችሉ የነበረውን አሳያቸዋለሁ፡፡” ብዬ አሰብኩ፡፡ በዚህን ጊዜ ከሕዝቡ ጋር የነበሩ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች እየተንሸራሸሩ እኔ የነበርኩበት ስፍራ _ ደረሱ፡፡ _ እርስ በርሳቸው በሚያወሩት ነገርና በአብሮነታቸው አብልጠው የተጠመዱ ይመስሉ ነበር፡፡ እኔን እየተመለከቱ “በየቦታው ፍለጋ ብናደርግም አንድም ፍሬ ማግኘት አልቻልንም” አሉኝ፡፡ ወዲያው የሰበሰብኳቸውን ፍሬዎች ብዛት በአድናቆት ተመለከቱ፡፡ እኔም “ከእነዚህ ቁጥቋጦዎች መሰብሰብ የሚችሉ ብዙ ፍሬዎች አሉ” አልኳቸው፡፡ ፍሬዎቹን ልቀም ጀመሩና ብዙም ሳይቆዩ በማቆም “ይህን ስፍራ ያገኘሽው አንቺ ስለሆንሽ ከዚv ቦታ መልቀማችን አግባብ አይደለም” አሉ፡፡ እኔም “ይህ የሚያመጣው ልዩነት የለም፡፡ እርሻውም ሆነ ፍሬዎቹ የእግዚአብሔር እንደመሆናቸው መልቀማችሁ ከእርሱ የተሰጣችሁ ልዩ መብትና ጥቅም ነው፡፡ ፍሬ ማግኘት ከምትችሉበት ቦታ ሁሉ ልቀሙ” በማለት መለስኩላቸው፡፡ ChSAmh 62.3

ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ እንደገና ብቻዬን እንደሆንኩ ተሰማኝ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ጋሪው ባለበት አቅጣጫ ሰዎች ሲነገሩና ሲስቁ ስለ ሰማሁ “ምን እያደረጋችሁ ነው?” ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡ “እስካሁን አንድም የእንጆሪ ፍሬ ማግኘት አልቻልንም:፡ ፍለጋው ስላደከመንና ረሃብ ስለተሰማን ምሳ ለመብላት ወደ ጋሪው መጥተን ነው፡፡ ለጊዜው አረፍ ካልን በኋላ እንደገና ለፍለጋ እንወጣለን” በማለት መለሱልኝ፡፡ “እስካሁን አንድ እንኳ ፍሬ ሳትለቅሙና ምንም ሳትሰጡን የያዝናትን ስንቅ ምንም ሳታስቀሩ እየበላችሁብን ነው፡፡ ብዙ የሚለቀሙ ፍሬዎች ስላሉ እኔ እንኳ አሁን መብላት አልችልም፡፡ ፍሬዎቹን ማግኘት ያልቻላችሁት አትኩራችሁ ባለመመልከታችሁ ነው፡፡ ከቁጥቋጦዎቹ በውጭኛው hፍል ስለማይገኙ በሚገባ ልታስሱ ይገባል፡፡ በአንድ ጊዜ እፍኝ የሚሞሉ ፍሬዎችን መልቀም አለመቻላችሁ እሙን ቢሆንም ካልበሰሉት ፍሬዎች መካከል በጥንቃቄከተመለከታችሁ ልትመርጧቸው የምትችሏቸውን ፍሬዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡” ብዙም ሳይቆይ ትንሽዋ ቅርጫቴ በእንጆሪ ፍሬዎች ተሞላች፡፡ ፍሬዎቹን ይዤ ወደ ጋሪው በማምራት “እነዚህ ውብ ፍሬዎች—እናንተ ርቃችሁ በመጓዝ ውጤት የሌለው ፍለጋ በማድረግ ራሳችሁን ታደክሙ በነበረበት ወቅት ከቅርብ የለቀምኳቸው ናቸው” አልኳቸው፡፡ ChSAmh 63.1

ከዚያም የያዝኩትን ፍሬ ለመመልከት ሁሉም በመምጣት “እነዚህ ዘለግ ካሉ ቁጥቋጦዎች የተለቀሙ ፍሬዎች ጥብቅና መልካም ናቸው፡፡ ዘለግ ካሉት ቁጥቋጦዎች አንድ እንኳ ፍሬ እናገኛለን ብለን ስላላሰብን ትኩረታችን ጥቂት ተመሳሳይ ጥብቅ ፍሬዎችን ባገኘንባቸው አጫጭሮቹ ላይ ብቻ ነበር፡፡” ChSAmh 64.1

“እነዚህን የለቀምኳቸውን ተረክባችሁ ሌሎች ተጨማሪ ፍሬዎችን ዘለግ ካሉት ቁጥቋጦዎች ለመሰብሰብ አብራችሁኝ ትወጣላችሁ?” ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡ ሆኖም ለተለቀሙት ፍሬዎች ጥንቃቄ ለማድረግ የሚያስችላቸው ዝግጅት አልነበራቸውም፡፡ ምንም እንኳ ብዛት ያላቸው ለመያዣነት የሚያገለግሉ ሰሃኖችና ሌሎች ቁሳቁሶች ቢኖሩም ነገር ግን ሁሉም ለምግብ መያዣነተ ውለው _ ነበር፡፡ መጠበቁ ስለሰለቸኝ “የመጣችሁት ፍሬዎችን ለመሰብሰብ አይደለም? ለተሰበሰቡት ፍሬዎች እንዴት ማስቀመጫ አላዘጋጃችሁም?” በማለት ለጠየቅኳቸው ጥያቄ አንድ ሰው እንዲህ ሲል መለስ ሰጠኝ “ሲስተር ኋይት በእርግጥ እንዲህ ብዙ ቤቶች ባሉበትና አያሌ ነገሮች በሚስተዋሉበት ሁኔታ አንድም ፍሬ እናገኛለን ብለን አልጠበቅንም፡፡ Uኖም አንቺ ፍሬ ለመስበሰብ ያለሽን ከፍተኛ ጉጉት ስንመለከት አብረንሽ ለመምጣት ወሰንን፡፡ ፍሬ መሰብሰቡ ካልሆነልን በቆይታችን ዘና ማለት እንድንችል በቂ ምግብ መያዝ እንዳለብን አስበን ነበር” እኔም እንዲህ በማለት መልስ ሰጠሁ “እንዲህ ያለ ሥራ ሊገባኝ አይችልም፡፡ በድጋሚ ወደ ቁጥቋጦው እሄዳለሁ፡፡ ቀኑ እያለቀምንም ፍሬ መልቀም የማንችልበት ምሽቱ ሊመጣ ተቃርቦአል፡፡” አንዳንዶች አብረውኝ ሲሄዱ ሌሎች ግን ለመመገብ ወደ ጋሪው አመሩ፡፡ ጥቂት ሰዎች በአንድ ቦታ እጅብ ብለው ትኩረታቸውን የሳበ በሚመስል ጉዳይ ዙሪያ ወግ ይዘዋል፡፡ _ ቀረብ _ ብዬ ስመለከት ትኩረታቸውን የወሰደው በእናቱ እቅፍ ያለ ትንሽ ልጅ መሆኑን ሳስተውል “ጥቂት ጊዜ ብቻ ስላላችሁ መሥራት በምትችሉበት በዚv ወቅት ብትሠሩ መልካም ነው” አልኳቸው፡፡ ChSAmh 64.2

ወደ ጋሪው ለመድረስ የሚሮጡ የአንድ ወጣት ወንድና ሴት ሁናቴ የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ነበር፡፡ ወጣቶቹ ወደ ጋሪው ሲደርሱ ከላይ ወጥተው በመቀመጥ ከድካማቸው ፋታ ያገኙ የነበረ ሲሆን ሌሎችም መስኩ ላይ እየተንጋለሉ እረፍት ያደርጉ ነበር፡፡ ChSAmh 65.1

በዚህ መልኩ ጥቂት ብቻ ተሠርቶ ቀኑ ተገባደደ፡፡ እኔም እንዲህ አልኳቸው “ወንድሞች-ይvን ዘመቻ ውጤታማ ያልሆነ ብላችሁ ትጠሩታላችሁ፡፡ የምትሠሩት እንዲህ ከሆነ ስኬታማ አለመሆናችሁ አያስገርመኝም፡፡ ስኬታችሁም ሆነ ውድቀታችሁ ለሥራው በሚኖራችሁ አያያዝና እንክብካቤ ይወሰናል፡፡ በዚv ቦታ ያኘኋቸው እንጆሪዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቻችሁ ቁመታቸው አጫጭር ከሆኑት የእንጆሪ ተክሎች ፍሬ ለማግኘት በከንቱ ስትለፉ ሌሎች ደግሞ ጥቂት እንጆሪዎችን አግኝተዋል፡፡ ነገር ግን ቁመታቸው ዘለግ ካለው የእንጆሪ ተhሎች ላይ ተገቢው አሰሳ ሳይደረግ በከንቱ ታልፈዋል፡፡ ይህ የሆነው ፍሬ ልናገኝባቸው አንችልም ብላችሁ በማሰባችሁ ብቻ ነው፡፡ እንደምትመለከቱት የሰበሰብኳቸው ፍሬዎች ትላልቅና የበሰሉ ናቸው፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሌሎችም እንጆሪዎች ስለሚበስሉ በድጋሚ አብረን ወደ ተክሎቹ ማምራት እንችላለን፡፡ እኔ ፍሬዎችን መሰብሰብ የተማርኩት በዚህ መልኩ ነው፡፡ ምናልባትም ከጋሪው አጠገብ ፍለጋ ብታደርጉ ኖሮ እናንተም እንደኔ ፍራፍሬዎችን ባገኛችሁ ነበር፡፡ ChSAmh 65.2

“ይህ ትምህርት በዚህ ወቅት የቀረበበት ምክንያት እንዲህ ያለውን ሥራ እንዴት መሥራት እንዳለባቸው እየተማሩ ያሉ ወገኖች አሠራሩን ቀስመው በቀጥታ ተግባር ላይ እንዲያውሉት ነው፡፡ ጌታ እነዚህን ፍሬ የተሸከሙ ተክሎች ፈልጋችሁ እንደምታገኟቸው ተስፋ በማድረግ ጥቅጥቅ ካለው ቁጥቋጦ መሃል ቢያኖራቸውም እናንተ ግን በአንድ ላይ ሆናችሁ በመብላትና ራሳችሁን በማዝናናት ከመጠመድ ውጪ ቅን እና ቆራጥ አቋም ይዛችሁ ፍሬዎቹን ለመሰብሰብ አልመጣችሁም:፡ ChSAmh 66.1

“ከዚህ በኋላ ከቀድሞው የተለየ ዓላማና ግብ አንግባችሁ በከፍተኛ ጉጉት፣ በላቀ ቅንነትና ታማኝነት ካልሠራችሁ hንውን አታገኙም፡፡ ለሥራው ቅድሚያ ሰጥታችሁ በትhክለኛው መንገድ ስትሠሩ ለመብላትና ለመዝናናት ሊሰጥ የሚገባው ቦታ እጅግ አናሳ እንደሆነ በማሳየት ለወጣት ሠራተኞች ተገቢውን ትምህርት ትተዋላችሁ፡፡ ምግብ የተጫነባቸውን ጋሪዎች ወደ ተፈለገው ስፍራ ማምጣት ከባድ ሥራ ቢሆንም አብልጣችሁ ትጨነቁ የነበረው የአገልግሎት ውጤታችሁ የሆኑትን ፍሬዎች ይዛችሁ ስለ መግባታችሁ ሳይሆን ስለ ምግቡ ነበር፡፡ በመጀመሪያ በአካባቢያችሁ የሚኙትን ፍሬዎች ለመልቀም ትጉ ከሆናችሁ በቀጣይ ራቅ _ ብለው የሚገኙትን ልታስሱ ትችላላችሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ቦታችሁ ተመልሳችሁ በአቅራቢያችሁ ስትሠሩ ክንዋኔ ታገኛላችሁ፡፡--Gospel Workers, pp. 136-139. ChSAmh 66.2