የክርስቲያን አገልግሎት

33/246

አገልግሎት ተቀባዮች እንጂ ሰጪዎች አይደሉም

የክርስቶስ ተከታዮች በሰማያዊው ፍርድ ፊት ሲቀርቡ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ያሳዩት በራድ ቅንአትና ደካማ ጥረት ታማኝነት የጎደላቸው ያስብላቸዋል፡፡ አሁን እየሠሩ ያለው ሥራ ምርጥና አቅማቸው የሚፈቅደውን ያህል ቢሆን ኖሮ ነቀፌታ ባልደረሰባቸው ልቦቻቸው ለሥራው ቢመለመሉ ከዚህ የላቀውን ማድረግ በቻሉ ነበር፡፡ ራስን የመካድና መስቀሉን የመሸከም መንፈስ በከፍተኛ ደረጃ ማጣታቸውን ራሳቸውም ሆኑ ይህ ዓለም ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ በሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ከተጻፈው በተቃራኒ ከሚገኙት መሃል አብላጫዎቹ አገልግሎት ተቀባይ እንጂ የማይሰጡ ይሆናሉ፡፡ የክርስቶስን ስም በተሸከሙ በአብዛኞቹ ውስጥ ክብሩ ተሰውሮአል፣ ውበቱ ተጋርዶአል እንዲሁም ለእርሱ ሊቸር የሚገባ አክብሮት ከመገለጽ ተገትቶአል፡፡ ብዙዎች ስማቸው በቤተ ክርስቲያን የአባልነት ባሕር መዝገብ ላይ ሰፈረ እንጂ በክርስቶስ አገዛዝ ስር አይደሉም፡፡ ትእዛዙን አክብረው እየተቀበሉ ወይም ሥራውን እየሠሩ አይገኙም፡፡ በዚህ የተነሳ በጠላት ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ እነዚህ ነፍሳት አንድም አዎንታዊ ተግባር እያከናወኑ ካለመሆናቸው አኳያ--መጠን የሌለው ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ በሰዎች ላይ እያሳደሩ ያለው ተጽእኖ በሞት ላይ ሞት የሚያስከትል እንጂ በሕይወት ላይ ሕይወት የሚያተርፍ አይደለም፡፡-Christ’s Object Lessons, pp. 303, 304. ChSAmh 58.2