የክርስቲያን አገልግሎት

19/246

የስኬት ምስጢር

ወጣቶች ጌታን ለማወቅ ስትከተሉት “እንደ ንጋት ብርሃን በእርግጥ ይገለጣል”፡፡ ለውጥን በሕይወታችሁ ለማየት አብልጣችሁ ተመኙ፡፡ ከአዳኙ ጋር ድርሻ እንዲኖራችሁ በጽኑ ታገሉ፡፡ በክርስቶስ በእምነት ኑሩ፡፡ እርሱ የሠራውን ሥሩ፡፡ እርሱ ሕይወቱን አሳልፎ ለሰጠበትነፍሳትን ለማዳን ኑሩ፡፡ የተገናኛችኋቸውን ሁሉ በማናቸውም መንገድ ለመርዳት ሞክሩ.. . ስለ እያንዳንዱ አስተምህሮ፣ ርኅም ሆነ አነስተኛ ነገር-ዕውቀታችሁን ፍጹም ከሚያደርገው ታላቅ ወንድማችሁ ከሆነው ከእርሱ ጋር ተነጋገሩ፡፡ እየጠፋ ያለውን ዓለም ለማዳን ራሱን መሥዋዕት ካደረገው ከእርሱ ጋር የቀረበ ግንኙነት መፍጠራችሁ ተቀባይነት ያላቸው ሠራተኞች ያደርጋችኋል፡፡Testimonies, vol 6, p. 416. ChSAmh 44.4