የክርስቲያን አገልግሎት
ሰማያዊውን ሸልማት በትዕግሥት ጠበቅ
የአዳኛችን መምጫ ሩቅ ቢመስል፣ በከባድ የሥራ ጫናና ልፋት ጀርባችን ቢጎብጥ፣ ተልዕኮአችንን ለመቋጨት ትዕግሥታችን የተሟጠጠ ቢመስልና ከውጊያው ግንባር በክብር ለመሰናበት ብንመኝ--አንድ ነገር በማስታወስ የማጉረምረማችንን መንስዔ እንፈትሽ፡፡ እግዚአብሔር እኛን በምድር ላይ የተወው እያንዳንዱን ወጀብና ግጭት እየተጋፈጥን የክርስትናን ሐይወት ወደ ፍጽምና እንድንመራ፣ ከእግዚአብሔር አብና ከታላቅ ወንድማችን ክርስቶስ ጋር የጠለቀ ትውውቅ እንድንፈጥር፣ ነፍሳትን ለክርስቶስ የማሸነፍ ሥራ ሠርተን “ደግ አድርገሃል አንተ መልካም ታማኝ አገልጋይ፤ ወደ ጌታv ደስታ ግባ፡፡ ” የሚሉትን የከበሩ አምላካዊ ቃላት በደስታና በሐሴት በተሞላ ልብ እንድንሰማ ነው፡፡Review and Herald, Oct. 25, 1881. ChSAmh 380.1
የክርስቲያን ወታደር ሆይበትዕግሥት ተጠባበቅ፡፡ ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ያ የሚመጣው ጌታ ዳግም ይገለጣል፡፡ በመጠባበቅና በትጋት የተሞላው አድካሚ ምሽትና ጠዋት እነሆ ወደ ማለቁ ነው፡፡ እያንዳንዱ የተዘጋጀለትን ሽልማት የሚቀበልበት ህያው ጧት በቅርቡ ይገለጣል፡፡ ከዚህ በኋላ የምናንቀላፋበትም ሆነ ጸጸት ብቻ በሚተርፈው እንደ ፈለጉ የመሆን ልል ስብዕና--የምንባክንበት ጊዜ የለም፡፡ በዚህ ወቅት የሚያንቀላፋ መልካም ማድረግ ይችልባቸው የነበሩትን የከበሩ ዕድሎች ያጣል፡፡ በታላቁ መከር ነዶ የምንሰበስብበት የተqረከ ልዩ መብትና ጥቅም ተሰጥቶናል፡፡ እያንዳንዱ ወደ እውነት የምናመጣው የሚድን ነፍስ ተወዳጁ አዳኛችን የሱስ በሚደፋልን አክሊል ላይ የሚያንጸባርቅ ተጨማሪ ኮከብ ይሆነናል፡፡ ለተጨማሪ ጥቂት ጊዜያት በውጊያው እየገፉና አዳዲስ ድሎችን እያስመዘገቡ ተጨማሪ ሽልማቶችን በመስበሰብ ፋንታ የጦር ልብሱን ለማውለቅ የሚቃጣው ይኖር ይሆን?-Review and Herald, Oct 25, 1881.... ChSAmh 380.2
የቤተሰብ አባሎቻችን፣ ምናልባትም የገዛ ልጆቻችን ወይም በአንድ ገበታ አብረን የበላንና የጠጣን ወገኖች ባለመዳናቸው ምክንያት በታላቁ የመጨረሻ ቀን ለዘላለም ሲለዩን መመልከት እንዴት አስደንጋጭና አስከፊ ይሆን! ከዚያም ራሳችንን እንዲህ ብለን እንጠይቃለን--የክርስቶስ ኃይማኖት ለእነርሱ ያልጣመበት ምክንያት ምን ነበር--የእኔ ትዕግሥት ማጣት? የክርስቲያን ጸባይ ስላልነበረኝ? ወይስ እኔነትን በቁጥጥር ስር ማዋል አለመቻሌ? ChSAmh 381.1
... የምንሠራበት ጊዜ እጅግ አነስተኛ እንደመሆኑ ዓለም በቅርቡ ስለሚገለጠው ጌታ የማስጠንቀቂያ መልእhት ሊሰጠው የግድ ነው ... እያንዳንዱ ችሎታ፣ ጉልበት፣ መክሊት እንዲሁም ለሌሎች መልካም እንድናደርግ የተሰጠን ብርሃን በጥቅም ላይ ይዋል፡፡ ChSAmh 381.2
ኢትዮጵያዊው በጥሩ አቋም ላይ ይገኝ የነበረና ሰፊ ተጽእኖ ማሳደር የቻለ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው ቢለወጥ ለወንጌል ድጋፍ የሚሆን ጠንካራ ተጽእኖ በማሳደር የተቀበለውን ብርሐን ለሌሎች እንደሚያሰራጭ እግዚአብሔር ተመልክቶ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መላእhት ብርሐን ለማግኘት ብርቱ ጥረት ያደርግ ከነበረው ከዚህ ሰው ጋር አብረው ነበሩ፡፡ ChSAmh 381.3
ኢትዮጵያዊው ወደ አዳኙ ተስቦ ነበር፡፡ ጌታም በመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት አማካይነት ወደ ብርሐን ሊመራው ወደ ሚችል ሰው አመጣው፡፡ ChSAmh 381.4
ከመጽሐፉ የተወሰደ ChSAmh 381.5