የክርስቲያን አገልግሎት
ደስታ—የምድር ሽልማታቸው Present Reward Happiness.---
ራሳቸውን ለክርስቶስ ዓይነት አገልግሎት የሰጡ የእውነተኛን ደስታ ትርጉም ያውቃሉ፡፡ ፍላጎታቸውም ሆነ ጸሎታችው ከእኔት ያለፈ ውጤት አለው፡፡ ሌሎችን ለመርዳት በሚያደርጉት ጥረት ራሳቸውን ያሳድጋሉ፡፡ ከግዙፎቹ ዕቅዶች ጋር ትውውቅ እየፈጠሩ፣ የሕያው እንቅስቃሴዎች አካል እየሆኑና ራሳቸውን በመለኮታዊው የብርሃን መስመርና በረከት እያኖሩ እንዴት አያድጉ? እንደነዚህ ያሉት ሰማያዊ ጥበብ ይቀበላሉ፡፡ ከክርስቶስ ዕቅዶች ጋር ይበልጥ የተዋወቁና የተሳሰሩ ስለሚሆኑ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንደ ታቆረ የኩሬ ውሃ ሊሆን የሚችልበት ዕድል አይኖርም፡፡— Testimonies, vol. 9, p. 42. ChSAmh 372.1
ሙሉ ለሙሉ በዚህ ሥራ ላይ የተሰማራች ቤተ ክርስቲያን በእርግጥም ደስተኛ ናት፡፡ በስvተት ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ነፍሳቸው በርኅራኄና በፍቅር ተሞልቶ ወደ ታላቁ እረኛ መንጋ ሊያመጧቸው የሚተጉእርሱም ሆነ እርሷ የተባረከው አገልግሎት አካል ሆነዋል፡፡ በበረት ካሉት ዘጠና ዘጠኙ ይልቅ አንድ ነፍስ ሲመለስ በሰማይ እንዴት ታላቅ ደስታ ይሆን! --Testimonies, vol. 2, p. 22. ChSAmh 372.2
ራሱን ለአምላካዊው ፈቃድ ላስገዛው ነፍስ ሊከብድ የሚችል አገልግሎት አይኖርም፡፡ ለጌታ እንደምናደርገው ቆርጠን በሙሉ ልባችን ስንሠራ እግዚአብሔር በሚሰጠን ሥራ ሁሉ መማረክ እንዳለብን እንገነዘባለን፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 150. ChSAmh 373.1
የhርስትና አገልግሎት ከሰማይ የተሰጠውን ሥራ ከባድና አድካሚ አድርጎ አይመለከትም፡፡ በዚህ ፋንታ ነፍሳት ከኃጢአት ባርነት ነጻ ወጥተው ሲመለከት የጌታው ደስታ አካል ይሆናል፡፡ ለእያንዳንዱ ራሱን ክዶ ለሰጠው አገልግሎት ይህ ያገኘው ደስታ ወሮታ ይሆነዋል፡፡-Southern Watchman, April 2, 1903. ChSAmh 373.2
ራስን ለመካድ ጥሪ የሚያቀርበውን ብርቱ ልፋት የሚጠይቀውን ሥራ በመልካም ሁኔታ እያከናወኑ በትዕግሥት መቀጠል—ሰማይን ደስ ያሰኛል፡፡-Testimonies, vol. 2, p. 24. ChSAmh 373.3
ሰይጣን አዋርዶ የጣላቸው ተስፋ የቆረጡ ነፍሳት ጋር በመድረስ የጸጋው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስንሠራ ክርስቶስ አብልጦ ደስ ይሰኛል፡፡ ሥራውን ከግብ ለማድረስ በእንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኙት ወኪሎቹና ልጆቹ በሚያገኙት ስኬት በሰማይ ብቻ ሳይሆን በዚህ ምድርም ሽልማታቸውን ይቀበላሉ፡፡— Testimonies, vol, 6, pp. 308, 309. ChSAmh 373.4
እያንዳንዱ ለክርስቶስ አገልግሎት የሚደረግ ጥረት ለአገልጋዩ በረከት ያስገኛል፡፡Christ’s Object Lessons, p. 354 ChSAmh 373.5
እያንዳንዱን ግዴታችንን ስንወጣና በየሱስ ስም ሥራው የሚጠይቀውን መሥዋዕትነት ስንከፍል መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ የሽልማት ባለቤቶች እንሆናለን፡፡ በሥራ ገበታ ላይ ሆነን እግዚአብሔር ይናገረናል፣ በረከቱንም ያፈስልናል፡፡— Testimonies, vol. 4, p. 145. ChSAmh 373.6
በዚህ ምድር የመኖራችን ዓላማ ነፍሳትን ለአዳኛችን ለማሸነፍ ሊሆን ይገባል፡፡ ሌሎችን ስናቆስል ራሳችንንም እናቆስላለን፡፡ ሌሎችን ስንባርh ራሳችንንም እንባርካለን፡፡ እያንዳንዱ በጎ ተግባር የሚያስከትለው ተጽእኖ 373በልባችን ውስጥ ይፈነጥቃል፡፡Testimonies, vol. 4, p. 72. ChSAmh 373.7
በሌሎች ላይ የሚያበራ እያንዳንዱ የብርሃን ጨረር በእኛም ልብ ውስጥ ያንጸባርቃል፡፡ በሐዘን ውስጥ ላለው የምንሰነዝረው እያንዳንዱ የድጋፍ ቃል፣ የተጨቆኑትን ቀንበር የሚያላላ እያንዳንዱ ድርጊት፣ ለባልጀራችን የምንዘረጋው ማንኛውም የችሮታ እጅየእግዚአብሔርን ሞገስ እንድናገኝና አምላካዊውን በረከት እንድንቀበል መንስዔ ይሆነናል፡፡ በዚህ መልኩ ሰማያዊውን ሕግ እየጠበቁ አገልግሎት የሚሰጡ አምላካዊውን አዎንታና ተቀባይነት ያገኛሉ፡፡--Testimonies, vol. 4, p. 56. ChSAmh 374.1
ክርስቶስ ዳግም ሲገለጥ ታላቁና የመጨረሻው ሽልማት የሚጠብቀን ቢሆንም እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚሻ እውተኛ ልብ በዚህም ምድር ተገቢውን ወሮታ ያገኛል፡፡ አገልጋዩ መሰናክሎች፣ ተቃውሞ፣ ምሬትና ልብ የሚሰብሩ ተስፋ አስቆራጭ ሁናቴዎች ይገጥታል፡፡ ምናልባት የድካሙን ፍሬ ላያይ ቢችል እንኳ—ነገ ግን ከዚህ ሁሉ ጀርባ ለአገልግሎቱ ተገቢው ሽልማት ተዘጋጅቶለታል፡፡ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጥተው ራስ ወዳድ ባልሆነ ለጋስ አገልግሎት ለሰብዓዊው ፍጡር የሚሠሩ ሁሉ ከhብር ጌታ ጋር ልዩ ትስስር ይፈጥራሉ፡፡ ይህን ማሰባቸው ምንም ቢመጣአድካሚው ሥራ ጣፋጭ እንዲሆንላቸውና በአምላካዊው ፈቃድ ላይ እንዲደገፉ ያስችላቸዋል፡፡Testimonies, vol. 6, pp. 305, 306. ChSAmh 374.2
ጤናመልካም የሆነውን ሥራ መሥራት ፍቱን የበሽታ መድ>ኒት ነው፡፡ በሥራው የተሰማሩ እግዚአብሔርን እንዲጠሩአምላካዊውንም ምላሽ እንዲቀበሉ ማደፋፈሪያና ማረጋገጫ ተሰጥቶአቸዋል፡፡ ነፍሳቸው ይጠግባል፣ ዳግመኛ እንደማይጠማ የለመለመ - መስክም ይሆናሉ፡፡ Testimonies, vol. 2, p. 29. ChSAmh 374.3
የእግዚአብሔር ተባባሪዎች ሆነን ከክርስቶስና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ስንሠራ ሰማያዊው አብሮነት ለአካላችን ጤንነት፣ ለአእምሮአችን ብርታትና ለነፍሳችን ደስታ ያጎናጽፋል፡፡Testimonies, vol. 6, p. 306. ChSAmh 374.4
ለሌሎች መልካም በማድረግ በነርቭ ውስጥ ብልጭታ የሚፈጥረው ደማቅ የደስታ ስሜት ፈጣን የደም ዑደት በማስከተል በአእምሮና በአካል ላይ የጤንነት ስሜተ እንዲሰርጽ ያደርጋል፡፡Testimonies, vol. 4, p. 56. ChSAmh 375.1
ጥንካሬ፡ ጠንካራው ሰው ራሱን ከሥራ ቢያርቅ ውሎ አድሮ ደካማና ልፍስፍስ ይሆናል፡፡ የሌሎችን ሸከም ከመሸከም ራሷን ያገለለች ቤተ ክርስቲያንም ሆነች ግለሰቦች--በዙም ሳይቆዩ የደካማ መንፈስ ሰለባዎች ይሆናሉ፡፡ ጠንካራውን ሰው ጠንካራ አድርጎ የሚጠብቀው የየዕለት እንቅስቃሴውና ተግባሩ እንደመሆኑመንፈሳዊ አገልግሎተ፣ ብርቱ ልፋትና የሌሎችን ሸክም መሸከም--የክርስቶስ ቤተ hርስቲያን የብርታት ምስጢር ነው፡፡Testimonies, vol, 2, p. 22. ChSAmh 375.2
ሰላም፦ ታላቅ ወሮታ ያለው ለሌሎች መሥራት፣ የተትረፈረፈ የውስጥ ሰላም ከማሰገኘት አልፎ ጣፋጭ እርካታ ያጎናጽፋል፡፡ ለሌሎች መልካም የማድረጉ ሃሳብ ከፍ ባለውና በተከበረው ከልብ የመነጨ ምኞት ሲነሳሳ ሰዎች እውነተኛ ደስታ ያገኛሉ፡፡ በመላእክት ዕይታ ውስጥ ያለውና በህይወት መዝገብ ላይ የሚያበራው እያንዳንዱ ታማኝና ራስ ወዳድ ያልሆነ ተግባር ከምድራዊው ወሮታ የላቀ ዋጋ ይጠብቀዋል፡፡ Testimonies, vol. 2, p. 132. ChSAmh 375.3