የክርስቲያን አገልግሎት

227/246

እግዚአብሔር መንፈሱን ሊሰጠን ፈቃደኛ ነው!

ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም ስጦታ ከሚሰጡት በበለጠ ጌታ ለሚያገለግሉት መንፈሱን ለመስጠት ፈቃደኛ ነው፡፡- The Acts of the Apostles, p. 50. ChSAmh 348.3

በማንኛውም ጊዜና ቦታ፣ በማንኛውም _ ሐዘንና ችግር ወቅት፣ ማንኛውም ነገር የጨለመና መጪውም ጊዜ ግራ የሚያጋባ ሲመስለን፣ አቅመ ቢስነትና ብቸኝነት ሲሰማን በእምነት ለምናቀርበው የጸሎት መልስ አጽናኙ ይላክልናል፡፡ አንዳንድ ሁኔታዎች ከምድራዊ ወዳጆቻችን ይለዩን ይሆናል፤ ነገር ግን ምንም ዓይነት ሁኔታ ወይም የቦታ ርቀት ከሰማያዊው አጽናኛችን ሊለየን አይችልም፡፡ ባለንበት ቦታና በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኛን ለመደገፍ፣ ለማበረታታትና ለማጽናናት ሁል ጊዜ በአጠገባችን ይገኛል፡፡The Desire of Ages, pp. 669,670. ChSAmh 349.1

የወንጌል የምስራች አብሳሪዎች በጌታ ስር ተንበርhከው ራሳቸውን ለእርሱ ቀድሰው ለመስጠት የገቡትን ቃል ሲያድሱ ዳግመኛ ሕይወት የሚዘራውንና የሚቀድሰውን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይሰጣቸዋል፡፡ የየዕለት ተግባሮቻቸውን ለማከናወን ሲወጡ በሰብዓዊው ዐይን የማይታየው መንፈስ ቅዱስ “ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች” እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡-The Acts of the Apostles, p. 56. ChSAmh 349.2

እኛ የምንኖርበት ይህ ዘመን መንፈስ ቅዱስ በሙላት የሚሠራበት ነው:፡ መንፈስ ቅዱስ ራሱን በሰብዓዊው ማንነት ውስጥ በማኖርና በማሰራጨት ተጽእኖን በዓለም ለማስፋፋት ምኞቱ ነው፡፡Southern Watchman, Nov. 3, 1903 ChSAmh 349.3