የክርስቲያን አገልግሎት

208/246

heading missing

para .text missing የክርስቶስን ባህሪ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ማለት ነው፡፡ ይህ ከመለኮታዊው መምህር ብቻ የሚገኝ የጥበብ ውጤት እንጂ በሳይንስ አስተምህሮአቸው ከታወቁ ታላላቅ ተቋሞች አይሸመትም፡፡The Desire of Ages, pp. 249, 250. ChSAmh 325.3

የአንድ ሰው ከወትሮ _ የተለየ እንግዳ መንፈሳዊ ፍንደቃ ውስጥ መገኘት የግሰቡን ክርስቲያንነት የሚገልጽ ወሳኝና የተረጋገጠ መረጃ መሆን ይችልም፡፡ ቅድስና መነጠቅ ሳይሆን ነገር ግን ራስን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማስገዛት ነው፣ ከእግዚአብሔር አፍ በምትወጣው እያንዳንዷ ቃል መኖር ነው፣ የሰማያዊው አባታችንን ፈቃድ ማድረግ ነው፣ በፈተና--በብርሐንም ሆነ በጨለማ በእግዚብሔር መታመን ነው፣ በምናየው ሳይሆን በእምነት መራመድ ነው፣ እግዚአብሔርን በመታዘዝ በእርሱ መተማመንና በፍቅሩ ማረፍ ነው::--The Acts of the Apostles, p. 51. ChSAmh 326.1

በሙሉ ልብ መሆን የእግዚአብሔር ሕዝቦች እርሱን በሙላትና በሙሉ ልባቸው ለማገልገል የተለዩ ሕዝቦች መሆናቸውን በማስታወስ ለራሳቸው አንዳች ክብር ሳይወስዱ ጌታንና እርሱን ብቻ ለማገልገል ራሳቸውን እጅግ ከተከበረው ኪዳን ጋር ማስተሳሰር ይኖርባቸዋል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 17. ChSAmh 326.2

በዚv ዘመን ጸንተው መቆም የሚችሉት በሙሉ ልብ የሚመላለሱ ጽኑ ወንዶችና ሴቶች ናቸው፡፡ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያንን መሰረት ለመጣል አስራ አንድ ደቀ መዛሙርትና ሌሎች ጥቂት ታማኝ ሴቶች እስኪቀሩ ተከታዮቹን በተደጋጋሚ ያጠራ ነበር፡፡ መሸከም የሚኖርባቸው ቀንበር ሲመጣ ወደ ኋላ አፈግፍገው ቤተ ክርስቲያን እያንጸባረቀች መሄድ ስትጀምር እንደ ቀድሞው ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው የሚዘምሩትንና በደስታ ስሜት የሚሰምጡትን በጥንቃቄ ማየት ተገቢ ነው፡፡ መልካምና ምቹ የነበረው ሁናቴ ሲከስም ጥቂት ታማኝ ካሌቦች ብቻ ወደ ፊተኛው መስመር መጥተው ጽኑና ጥብቅ የሆነውን መርኅ ያውለበልባሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ጣዕማቸውን እንደያዙ የሚዘልቁ ጨው ናቸው፡፡ ሥራው ከብዙ ተግዳሮቶች ጋር እየተጋፈጠ ሲውተረተር ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ረዳቶችን እያጎለበተች ትሄዳለች፡ :-- Testimonies, vol. 5, p. 130. ChSAmh 326.3

ማንም በሙሉ ልቡ ወደ አገልግሎት በመግባት ምርጥና የከፍተኛ ችሎታ ባለቤት ሊያደርገው የሚችለውን የክርስቶስ ዕውቀት ለማግኘት በመጣር ፋንታ ውድቀቱን የሚያሰላስል ከሆነ በአምላካዊው ሥራ ስኬታማ መሆን አይችልም፡፡ ራሱን ሙሉ ለሙሉ መስጠት የማይችል ሰው የክርስቶስ ደቀ መዝሙርም ሆነ የሥራው አካል መሆን አይችልም፡፡The Desire of Ages, p. 273. ChSAmh 327.1

ጥናት ባልተረደገበት ግምታዊ ሥራም ሆነ ከማያምኑ ጋር በማንኛውም የንግድ ሽርክና ውስጥ መግባት እግዚአብሔር የሰጣቸውን አገልግሎት ያደናቅፋል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 19. ChSAmh 327.2

አዳኙ በተከፋፈለ ልብ የሚቀርበውን አገልግሎት አይቀበልም፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሠራ ሠራተኛ በየዕለቱ ራስን ለአገልግሎት አሳልፎ የመስጠትን ትርጉም ሊማር የግድ ነው፡: --Gospel Workers, p. 113. ChSAmh 327.3