የክርስቲያን አገልግሎት

205/246

ያልተወሳሰበ መልእhት

ክርስቶስ የሚያምኑትን ሁሉ በስሙ በቤተ hርስቲያን እንዲሰበስ ለደቀ መዛሙርቱ መናገሩ ወንጌልን ሳያወሳስቡ የማቅረብን አስፈላጊነት ያሳያል፡፡ አምላካዊው መልእክት በቀላሉ መስተዋል በቻለ ቁጥር በሰዎች ላይ የሚኖው አርአያነት ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ደቀ መዛሙርት ክርስቶስ የተጠቀመውን ቀላል ዘዴ ተጠቅመው ወንጌልን መንገር ነበረባቸው፡፡-The Acts of the Apostles, p. 28. ChSAmh 322.2

እጅግ ግልጽና ትሁት አቀራረቦችን ተጠቅመን በሺ ወደ ሚቆጠሩ ሕዝቦች መድረስ እንችላለን፡፡ ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር የተነሳ ስለ አምላካዊው ደግነት መናገር ተፈጥሮው ከሆነ ነፍስ እንደ ዋዛ የሚሰነዘሩ ቀላል ቃላት በዓለም ላይ ታላቅ ስጦታ ያላቸው ተጽእኖ ፈጣሪ ወንዶችና ሴቶች ልብ ውስጥ መነቃቃት ማምጣት ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ በሚገባ ተዘጋጅተንና አጥንተን የምንናገራቸው ቃላት ተጽእኖ ያን ያህል አመርቂ አይሆንም፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች አንደበት የሚወጡ ተፈጥሮአዊዎቹ እውነተኛና ታማኝ ያልተወሳሰቡ አገላለጾች በክርስቶስና አስገራሚ ፍቅሩ ላይ ለረጅም ዘመናት ተከርችመው የነበሩ የልብ መግቢያ በሮችን ወለል አድርጎ የመክፈት ኃይልአላቸው:፡Christs Object Lessons p. 232. ChSAmh 322.3