የክርስቲያን አገልግሎት

203/246

የአእምሮ ጽናት

እውነተኛ ክርስቲያን—መርኅን የተከተለ የሕይወት ሙሉ አገልግሎት ይሰጣል እንጂ በስሜት ተገፋፍቶ ለአንድ ቀን ወይም ለአንድ ወር የሚቆይ ሥራ ለእግዚአብሔር አይሠራም፡፡Counsels to Teachers, p. 518. ChSAmh 320.2

ደከመኝ፣ ሰለቸኝ የማይል ሠራተኛ የነበረው አዳኝ ሥራውን በሰዓታት ለክቶ አያውቅም፡፡ ጊዜውን፣ ልቡንና ጉልበቱን ለሰብዓዊው ፍጡር ጥቅም ያውል ነበር፡፡ ማንኛውንም የጠላት ማታለያ ዘዴ ተቋቁሞ ማለፍ ይችል ዘንድ ሙሉውን ቀን ለአገልግሎት ሰጥቶ የነበረው አዳኝ ሌሊቱን በጸሎት ተግቶ በማሳለፍ ሰብዓዊውን ፍጡር የማነጽና ወደ ቀድሞው ንጽህና የመመለስ ሥራ ለመሥራት የሚያስችለውን በቂ ዝግጅት ያደርግ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ከተግባሩ ፍንክች ሳይል ጊዜውን ሁሉ በሥራ ላይ ያውላል እንጂ አገልግሎቱን በስምንት የሥራ ሰዓታት አይለካም፡፡ መልካም ለማድረግ የሚያስችሉት ሁናቴዎች በተመቻቹለት ቁጥር መልካም ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም፡፡ በየትኛውም ስፍራም ሆነ በማንኛውም ጊዜ ለእግዚአብሔር መሥራት የሚችልበትን ዕድል አሻግሮ ይመለከታል፡፡ በሄደበት ሁሉ መልካም መዓዛ ያለው የአገልግሎት ሽቶ ከእርሱ አይለይም፡፡Testimonies, vol. 9, p. 45. ChSAmh 320.3

አምላካዊን ሥራ በንዝህላልነት ለተግሳጽ የሚያጋልጥ ወይም ለሥራ የተዘረጉ የባልደረቦቹን የአገልግሎት እጆች የሚያዳክም በገዛ ባህሪው ላይ በቀላሉ ሊወገድ የማይችል ዕድፍ ያኖራል፡፡ ወደፊት ጠቃሚ ተግባር ሊያበረክት ያስችለው በነበረ የአገልግሎት ጎዳና ላይ ብርቱ መሰናክል ይደነቅራል፡፡--Prophets and Kings, p. 659. ChSAmh 321.1

የሱስ “ቀንበሬን በጫንቃችሁ ተሸከሙ ብሎ ተናግሮአል፡፡ ቀንበር አገልግሎት መስጫ መሣሪያ ነው፡፡ ከብቶች ለሥራ በቀንበር ይጠመዳሉ፡፡ እነዚህ እንስሳት ሥራቸውን በትክክል ለመወጣት እንዲችሉ ለማድረግ ቀንበር አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ምሳሌ ክርስቶስ እስከ ህይወታችን ፍጻሜ ድረስ ለአገልግሎት የተጠራን መሆናችንን ያስተምረናል፡፡ የእርሱ የሥራ አጋሮች ለመሆን የእርሱን ቀንበር መሸከም አለብን፡፡--The Desire of Ages, p. 329. ChSAmh 321.2