የክርስቲያን አገልግሎት
ጠንክሮ የድርሻን ሥራት
እግዚአብሔር አምላካዊውን እውነት ወደ ፊት ለማራመድ ሲል ተአምራትን ተጠቅሞ አይሠራም፡፡ ገበሬው መሬቱን ለማረስ ችላ ካለ ሊከተል የሚችለውን ውጤት ለመከላከል ተአምራት ሊያደርግለት አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ይፋ የተደረጉልንን +ላላቅ መርኅዎች ተከትሎ የሚሠራ አምላክ እንደመሆኑ ብልህ ዕቅዶችን አውጥተን ባለን ነገር ወደ እንቅስቃሴ እየገባን የድርሻችንን ስንወጣአመርቂ ውጤት እንድናገኝ ይባርክልናል፡፡ ነገር ግን አንዳችም እንቅስቃሴ ወይም ወሳኝ ጥረት ሳያደርጉ መንፈስ ቅዱስ ወደ ተግባር የሚገቡበትን ግፊት እንዲያደርግላቸው የሚጠባበቁ በጨለማ ጠፍተው ይቀራሉ፡፡ በአምላካዊው ሥራ ተካፋይ በመሆን ፋንታ እጆችዎን አጣጥፈው ያለ እንቅስቃሴ መቀመጥ {ይችሉም፡፡--The Southern Watchman, Dec, l, 1903. ChSAmh 315.1
አንዳንድ የወንጌል አገልግሎት አካል የሆኑ ወገኖች ሃሞታቸው የፈሰሰ፣ ወኔ ቢሶች፣ መንፈሰ ደካሞችና በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጡ በመሆናቸው ወደ ፊት የመገስገስ ተነሳሽነት ይጎድላቸዋል፡፡ አንድ ነገር ለማከናወን ኃይል የሚሆናቸውን አዎንታዊ ትጋትና ጉጉት ማቀጣጠል የሚችል መንፈስና ጉልበት የላቸውም፡፡ የስኬት ባለቤት የሚሆኑ ሁሉ ሃሞተ ኮስታራና በተስፋ የተሞሉ ሊሆኑ የግድ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች የሚሠሩትና የሚያለሙት ለመሥራት ተነሳሽነት ለጎደለው ብቻ ሳይሆን የንቃትና ብርታት ምግባር ባለቤት ለሆነው ጭምር ነው፡፡--Gospel Workers, p. 290. ChSAmh 315.2
ጌታ የክርስቶስን የመስቀል ድልና ስኬት ይዘው ወደ ፊት የሚገሰግሱ ሠራተኞች ይፈልጋል፡፡Review and Herald, May 6, 1890. ChSAmh 315.3
መልእክቱ የሚሰጠው በማያጓጓና በለዘዘ ቃና ሳይሆን ነገር ግን ግልጽ፣ ልብን በሚነካ፣ በሚያነቃቃና በሚያነሳሳ ለዛ ነው፡ Testimonies, vol. 8, p. 16. ChSAmh 316.1
ይህን መልእክት የሚያቀርቡት ሸንጋይ ምላስ ያላቸው ተናጋሪዎች አይደሉም፡፡ እውነት ከነሙሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያው ሊነገር የግድ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማንጻትና ዓለምን ለማስጠንቀቅ በጽኑና የማያቋርጥ ኃይል የሚሠሩ የተግባር ሰዎች ያሰፈልጉናል፡፡— Testimonies, vol. 5, p. 187. ChSAmh 316.2
እግዚአብሔር ለሥራው ሰነፎችን ሳይሆን ነገር ግን ልባሞችን፣ ደጎችን፣ አፍቃሪዎችንና ጽኑ ሠራተኞችን ለመጠቀም _ ይሻል፡፡ Testimonies, vol. 4, p. 411. ChSAmh 316.3