የክርስቲያን አገልግሎት

191/246

ምዕራፍ 22—የጸሎት አገልግሎትና የአምልኮ ጊዜ

የውጠታማ ጸሎት ምስጢር

የእግዚአብሔር መንግሥት ዘገምተኛ አካሄድ ወይም ፈጣን መነሳሳት-በሰብዓዊው ወኪል ታማኝ ሆን ወይም አለመሆን ይወሰናል፡፡ ሰብዓዊው ፍጡር ከመለኮት ጋር መተባበር ሳይችል ሲቀር ሥራው መስተጓጎል ይገጥመዋል፡፡ ሰዎች “መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን” ብለው የሚጸልዩትን ጸሎት በሕይወታቸው መተግበር ካልቻሉ ልመናቸው ፍሬ ቢስ ይሆናል፡፡ Testimonies, vol. 6, pp. 437, 438. ChSAmh 291.1

ሚዛኑን የጠበቀ አምልኮአዊ ልምምድ፡- የመላው ሰማይ ዐይኖች በምድር ነዋሪዎች ላይ ተተhለዋል፡፡ መላእክትና የሰማይ አምላክ ክርስቲያን ነን የሚሉ ወገኖችን የአምልኮ ልምምድ በአጽንኦት እየተመለከቱ ይገኛሉ፡፡-Australasian Signs of the Times, June 22, 1903. ChSAmh 291.2

የአምልኮ ጊዜን አስደሳች ማድረግ፡—ሰዎች እንዴት የወንጌል ሥራ መሥራት እንደሚችሉ ትምህርት ለሚያገኙበት ስብሰባ አትኩሮት ይሰጥ፡፡-Appeal to Our Churches, p. 11. ChSAmh 291.3

ጸሎተና የአምልኮ ጊዜ ለነፍሳት የተለየ እርዳታ የምንሰጥበትና እነርሱን የምናበረታታበት ይሁን፡፡ የአንድነት ጊዜያቶችን በተቻለ አስደሳችና ውጤታማ ለማድረግ እያንዳንዱ ሰው የሚሠራው ሥራ አለው፡፡ በአምላካዊው ነገሮች ዕለት ዕለት የአዳዲስ ተሞhሮዎች ባለቤት በመሆን ሳናመነታ ሰዎች በተሰበሰቡበት ስለ ፍቅሩ ለመናገር ስንደፍር ይህ ምርጥ ሆኖ መተግበር ይችላል፡፡ በልብዎ አንዳችም ጽልመት ወይም አለማመን እንዲገባ እስካልፈቀዱ ድረስ ይህ በጉባዔም መሃል ሊታይ አይችልም፡፡ Southern Watchman, March 7, 1905. ChSAmh 292.1

መንፈሳዊ ስብሰባዎቻችን ብርቱና በተጋጋለ ስሜት የተሞሉ፣ የሰማይ መገኘት የሰፈነባቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ ለይስሙላ የሚደረጉ ደረቅ ንግግሮችና ልማዳዊ ጸሎቶች አይኑሩ፡፡ ሁሉም ሰው የየበኩሉን ለመሥራት ተነሳሽነት ያለውና ዝግጁ ይሁን፡፡ በጉባዔ መቅረብ የሚኖርባቸው ነገሮች ከቀረቡ በኋላ ስብሰባው ይቋጭ፡፡ ይህ ሲሆን የሕዝቡ ትኩረት እስከ መጨረሻው የተጠበቀ ከመሆኑ በተጨማሪ አምልኮውም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ይሆናል፡፡ ለእግዚአብሔር የምንሰጠው አገልግሎት አስደሳችና መስህብነት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ ደረቅና የአምልኮ መልክ ብቻ ወዳለው ቁልቁለት የወረደ እንዲሆን መፍቀድ የለብንም፡፡ በየደቂቃው፣ በየሰዓቱና በየቀኑ ለክርስቶስ ስንኖር--ክርስቶስም በእኛ ውስጥ ይኖራል፣ ፍቅሩ በልባችን ይንሰራፋል፣ ጠንካራ የአንድነት ጊዜ ይኖረናል፣ በረሐውን አረንጓዴ እንደሚያለብሰው የፀደይ ወራት ሁሉንም ያነቃቃል፣ ሊጠፉ የተዘጋጁት ከሕይወት ውሃ የመጠጣት ብርቱ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያደርጋል፡፡Testimonies, vol. 5, p. 609. ChSAmh 292.2

ረጅም ስብከት በመስበክና በወንጌል ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ብቻ የወጣቶችን ፍላጎት መቀስቀስ እንደሚችሉ አድርገው አያስቡ፡፡ ይልቁንም ሕያው ፍላጎት ሊያነሳሳ የሚችል ዕቅድ ያውጡ፡፡ ወጣቶች በሳምንቱ ውስጥ ለአዳኙ ለማድረግ የሞከሯቸውንና ያገኟቸውን ስኬቶች የሚያበስሩ ዘገባዎች በየሳምንቱ ያቅርቡ፡፡ የወንጌል ስብሰባዎች እንደነዚህ ዓይነቶቹንዘገባዎች የሚያካትቱ ከሆነ ለዛቢስ፣ አሰልቺና ስሜት የማይስቡ በመሆን ፋንታ አስደሳችና ማራኪ ስለሚሆኑ የታዳሚ እጥረት አይገጥማቸውም፡፡ Gospel Workers, pp. 210, 211. ChSAmh 292.3

እምነታችን ክርስቶስን አጥብቆ ሲይዝ አምላካዊው እውነት ለነፍሳችን ደስታ ያመጣል፤ ኃይማኖታዊ አገልግሎታችንም ለዛቢስና አሰልቺ አይሆንም፡፡ አሁን የለዘዘና መንፈስ ዐልባ ሆኖ የሚታየውን መንፈሳዊ ስብሰባችሁን መንፈስ ቅዱስ ሕያውና ጠንካራ ያደርገዋል፡፡ የክርስትና እምነትዎን በተለማዱ ቁጥር በየቀኑ የከበረ ተሞክሮ ባለቤት ይሆናሉ፡፡-Testimonies, vol. 6, p. 437. ChSAmh 293.1

የግል ተሞhሮ ምስክርነት፡እንደ:-ክርስቶስ ተከታይነታችን ከአንደበ ቶቻችን የሚወጡት ቃላት በክርስትና ሕይወት ለሌሎች ድጋፍ የሚሆኑና የሚያበረታቱ ሊሆን ይገባል፡፡ ስለ ከበሩት የሕይወት ምዕራፍ ተሞhሮዎች አብልጠን መናገር ይኖርብናል፡፡--Christ’s Object Lessons, p. 338. ChSAmh 293.2

ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የመፍጠር ትኩስና ሕያው ተሞክሮ ያላቸው አባላት ያስፈልጓታል፡፡ ክርስቶስ የማይታይበት የደረቀና የጎመዘዘ _ ምስክርነትና _ ጸሎት ለሕዝቡ የሚፈይደው ነገር አይኖርም፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ የሚል እያንዳንዱ ሰው በእምነት፣ በብርሐንና በሕይወት የተሞላ ቢሆን ኖሮ እውነትን ለመስማት ለሚጡ እንዴት ያለ ምስክር በሆነ! ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች ለክርስቶስ በተሸነፉ ነበር፡፡— Testimonies, vol. 6, p. 64. ChSAmh 293.3

ስለ አምላካዊው ታማኝነት የምናቀርበው ምስክርነት ክርስቶስ ለዓለም እንዲገለጥ በሰማይ የተመረጠው መንገድ ነው፡፡ ለጥንት የእግዚአብሔር ቅዱሳን የተገለጠውን አምላካዊ ጸጋ እንድንቀበል የተጠራን ቢሆንም የግል ተሞhሮ ምስክርነታችንም ከዚያ የላቀ ውጤት ማምጣት ይችላል፡፡ በውስጣችን የሚሠራውን መለኮታዊ ኃይል ገልጠን ስናሳይ የእግዚአብሔር ምስክሮች እንሆናለን፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ከመላው ሰብዓዊ ፍጡር የተለየ ሕይወትና ተሞክሮ አለው፡፡ የግላዊ ማንነታችንን አሻራ ያልለቀቀ ምስጋና ለእርሱ እናቀርብ ዘንድ የእግዚአብሔር ምኞት ነው፡፡ እንዲህ ያለው ለጸጋው ክብር የሚቀርብ ውዳሴ ክርስቶስን እየመሰለ በሚያድግ ሕይወት ሲደገፍ፤ ለነፍሳት ደኅንነት የሚሠራውን ሥራ ማንም ሊቋቋመው አይችልም፡፡-The Ministry of Healing, p. 100. ChSAmh 293.4

ውዳሴና ምስጋና፡-እግዚአብሔርን በሙላትና ከልብ በመነጨ ቅንነት ማወደስ የጸሎትን ያህል ሊተገበር የሚገባ ተግባር ነው፡፡ እግዚአብሔር በኃጢአት ለወደቀው ሰብዓዊ ዘር ላሳየው አስደናቂ ፍቅር ያለንን አድናቆት ለዓለምና ለመላው የሰማይ ፍጡራን እያሳየን፣ ከአምላካዊው ዘላለማዊ ሙላት ይበልጥ የላቀ በረከት እንጠባበቅ... መንፈስ ቅዱስ በተለይ በኃይል ከፈሰሰ በኋላ አምላካዊውን በጎነት ስንቆጥርና ስለ ልጆቹ የሚሠራውን ድንቅ ሥራ ስንመለከት በጌታ ደስ እንሰኛለንለአገልግሎቱ የሚኖረንም ብቃት በከፍተኛ መጠን ያድጋል፡፡ እነዚህ ተሞhሮዎች የሰይጣንን ኃይል በመጣበት እግሩ በመመለስ የማጉረምረም፣ የምሬት፣ የቁጣና የግልፍተኝነትን መንፈስ ይገስጻሉ፡፡ የምድር ነዋሪዎች ለሰማያዊው ውብ መኖሪያ ብቁ የሚያደርጋቸውን ምርጥ ጸባይ ያበለጽጋሉ፡፡ እንዲህ ያለው ምስክርነት በሌሎች ላይ ጉልህ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡ ነፍሳትን ለክርስቶስ ለማሸነፍ ከዚህ የላቀ ውጤታማ ዘዴ ሊኖር አይችልም፡፡Christ’s Object Lessons, pp. 299, 300. ChSAmh 294.1

ጌታ ስለ መልካምነቱና ስለ ኃያልነቱ እንድንናገር ይመኛል፡፡ ለእርሱ የምናቀርበው ውዳሴና የምስጋና ቃላት ክብሩ ነው፤ “የምስጋና መሥዋዕት የሚሠዋ ያከብረኛል”፡፡ የእስራኤል ሕዝቦች በምድረ በዳ ጉዞአቸው እግዚአብሔርን በተቀደሰ ዜማ ያወድሱ ነበር፡፡ የጌታ ትእዛዛትና ኪዳኖች በዝማሬ ተቀናብረው በተስፋይቱ ምድር ተጓዦች ይዘመሩ ነበር፡፡ እንዲሁም በከነዓን የተቀደሱትን በዓላት ለማክበር በአንድነት ሲገናኙ ግሩምና አስደናቂ የሆኑት የእግዚአብሔር ሥራዎች ይዘከራሉ--ስለ ስሙም ታላቅ የምስጋና መሥዋዕት ያቀርባሉ፡፡ የሕዝቡ ሕይወት የምስጋና ሕይወት ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ምኞት ነው፡፡-Christ’s Object Lessons, pp. 298, 299. ChSAmh 294.2

አደገኛ አቋም፡--አንዳንዶች ምድራዊ ሐብትና ንብረታቸውን እንዳያጡ በመስጋት አብዛኛውን ጊዜያቸውን ለግብርና ወይም ለንግድ ሥራቸው ስለሚያውሉ በአንድነት ተሰባስበው እግዚአብሔርን ለማምለክ ችላ ይላሉ፡፡ ለምድራዊው ይሁን ለሰማያዊውለየትኛው ከፍተኛውን ስፍራ እንደሚሰጡ በሥራቸው ያሳያሉ፡፡ ለመንፈሳዊ ማንነታቸው መሻሻል ሊጠቅሟቸው ይችሉ የነበሩትን ልዩ ኃይማኖታዊ መብቶችና ጥቅሞች ለምድራዊው ሕይወት ቁሶች ሲሉ በከንቱ ስለሚያሳልፏቸው የመለኮታዊውን ፈቃድ ዕውቀት ከማግኘት ይሰናከላሉ፡፡ የክርስትናን ጸባይ ወደ ፍጽምና ከማበልጸግ ስለሚገቱ ከአምላካዊው ቁመትና ስፋት ጋር ገጣሚ አይሆኑም፡፡ ጊዜአዊና ዓለማዊ ፍላጎታቸውን ስለሚያስቀድሙ ለእርሱ አገልግሎት ሊያውሉ ይገባ የነበረውን ጊዜ ይሰርቃሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች በበረከት ፋንታ እርግማን ይቀበላሉ፡፡ Testimonies, vol. 2, p. 654. ChSAmh 295.1

የሚያጽናናው ተስፋ፡--በአንድ ላይ ተሰባስበው ስለ ስሙ ልዩ አጽንኦት የሚሰጡትን ወገኖች እግዚአብሔር ያስታውሳቸዋልከእቶን እሳትም ይታደጋቸዋል፡፡ የከበሩ ዕንቁዎቹ ሆነው በፊቱ ይመላለሳሉ፡፡ Testimonies, vol. 4, p. 107. ChSAmh 295.2