የክርስቲያን አገልግሎት
ውጤቶቹ የተረጋገጡ ናቸው
ከልብ የመነጨ የነፍሳት መለወጥ ላይ ገቢራዊ የሚሆኑ አሁን ተለይተው የማይታዩ ተአምራቶች እውን ይሆናሉ፡፡ የዚህ ምድር ታላላቅ ሰዎች የሚገኙት አስደናቂ ሥራ ከሚሠራው አምላካዊ ኃይል ባሻገር አይደለም፡፡ ሠራተኞች ለእርሱ ምቹ ሆነው ከሠሩና የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጀግንነትና በታማኝነት ከተወጡ እግዚአብሔር አርቆ አስተዋዮችንና ተጽእኖ አሳዳሪዎችን በመለወጥ በኃላፊነት ያስቀምጣቸዋል፡፡ ብዙዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካይነት መለኮታዊውን መርኅ ይቀበላሉ፡፡ እውነትን ተቀብለው በመለወጣቸው ከብርሐን ጋር ኅብረት ያላቸው በእግዚአብሔር እጅ የሚገኙ ወኪሎቹ ይሆናሉ፡፡ ችላ በተባለው የሕብረተሰብ ክፍል ለሚገኙ ነፍሶች ልዩ ሸhም የሚሰማቸው ይሆናሉ፡፡ ጊዜና ገንዘብ ለጌታ ሥራ ተቀድሶ ይውላል፡፡ አዲስ ጉልበትና ኃይል ለቤተ hርስቲያን ይጨመራል፡፡--The Acts of the Apostles, p. 140. ChSAmh 282.1
ከፍ ያለው የሕብረተሰብ ከፍል አካል የሆኑ አብዛኞቹ ሰዎች ልባቸው የተጎዳና በከንቱ መታበይ የታወኩ ናቸው፡፡ በውስጣቸው የሌለውን ሰላም ለማግኘት አጥብቀው ይናፍቃሉ፡፡ ደኅንነትን ይራባሉ፤ ይጠማሉም፡፡ የጌታ ሠራተኞች በhርስቶስ ፍቅር በተለሳለሰ ደግነት፤ በግል ቢገናኗቸው አብዛኞቹ እርዳታውን ይቀበላሉ፡፡--Christ’s Object Lessons, p. 231. ChSAmh 282.2
ምድራዊ ጥበብ የሰፈነበት ይህ ዓለም እግዚአብሔርን ስለማያውቅ የዓለም ታዋቂ ሰዎች፣ ምሑራንና ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ፊታቸውን ከብርሐን ያዞራሉ፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር አገልጋዮች እያንዳንዱን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው እውነትን ወደ እነዚህ ሰዎች ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡ ከመካከላቸው አንዳንዶች ስለ አምላካዊው ነገሮች አንዳችም እንደማያውቁ በማመን በመምህሩ የሱስ እግሮች ስር ተቀምጠው ለመማር ይመጣሉ፡፡The Acts of the Apostles, pp. 241-242. ChSAmh 282.3