የክርስቲያን አገልግሎት
ተጨባጭ የወንጌላዊውን ሥራ ማሳያ ዘዴዎች
ሁሉም በወንጌል ጉባዔ አገልግሎት ላይ ተሳታፊ በመሆን ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው እንዴት መሥራት እንደሚኖርባቸው ትምህርት ማግኘት ይችላሉ፡፡- Testimonies, vol. 6, p. 49. ChSAmh 271.2
አንዳንድ የወንጌል ጉባዔዎቻችን አካል የሆኑ ጠንካራ ሠራተኛ ቡድኖች ወደ ከተሞችና መንደሮች ወጥተው በራሪ ጽሑፎችን የማደልና ሰዎችን ወደ ጉባዔ የማደም አገልግሎት እንዲሰጡ ሆነው ተደራጅተዋል፡፡ ይህ ዘዴ ጥቅም ላይ መዋሉን ተከትሎ ከጉባዔው አጋማሽ አንስቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የጉባዔው መደበኛ ተካፋይ ለመሆን ችለዋል፡፡ -Testimonies, vol.P. 36. ChSAmh 271.3
አምላካዊውን እውነት ለመቀበል ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ለሌሎችም ለማካፈል ወደ ጉባዔዎቹ መሄድ እንችላለን፡፡ የክርስቶስ ይቅር ባይ ፍቅር ወራሽ የሆነ እያንዳንዱ ሰው፣ በአምላካዊው መንፈስ ማስተዋል አግኝቶ እውነትን ተቀብሎ የተለወጠ ማንኛወም ሰውለሚገናኘው ነፍስ ሁሉ የከበረውን በረከት የማስተላለፍ ዕዳ እንዳለበት ይሰማዋል፡፡ የተቀባው የወንጌል አገልጋይ ሊደርስባቸው ያልቻለውን ነፍሳት ጌታ ትሑት ልብ ያላቸውን ተጠቅሞ ይገናኛቸዋል፡፡ የሚያድነውን የክርስቶስ ጸጋ የሚገልጹ ቃላቶችን እንዲናገሩ በመንፈስ ቅዱስ ይነካሉ፡፡—Testimonies, vol. 6, p. 43. ChSAmh 271.4
ጌታ ያወጣቸውን እቅዶች ስንከተል “ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች” እንሆናለን፡፡ የፊልድ ፕሬዚደንት፣ አገልጋይ፣ መምህር፣ ተማሪ ወይም ፈቃደኛ ወንጌላዊ ብንሆን ወቅታዊውን እውነት መንገር የምንችልባቸውን ዕድሎች ሳንጠቀም የምንቀር ከሆነ በጌታ ፊት ተጠያቂዎች እንሆናለን፡፡ ይህን እቅድ ገቢራዊ ማድረግ እንድንችል ከተሰጡን መንገዶች አንዱና ቀዳሚው የኅትመት ውጤቶቻችን ናቸው፡፡ በትምህርት ቤቶቻችን፣ በሆስፒታሎቻችን፣ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኖቻችን እንዲሁም በተለይ በዓመታዊው የወንጌል ጉባዔያችን ይህን የከበረ ዘዴ በጥበብ መጠቀም መማር ይኖርብናል፡፡ አባላት ቸር በሆነ አቀራረብ አማኝ ያልሆኑ ሰዎችን እንዴት ማግባባት እንዳለባቸውና ለዚህ ዘመን የተሰጡንን እውነቶች የያዙትን ግልጽና ብርቱ የኅትመት ውጤቶች በሰዎች እጆች ላይ እያኖሩ፤ ነፍሳትን ማሸነፍ የሚችሉባቸውን መንገዶችለሥራው የተመረጡ ሠራተኞች ሕዝባችንን በትዕግሥትና በትጋት ማስተማር ይኖርባቸዋል፡፡ Testimonies, vol. 9, pp. 86, 87. ChSAmh 272.1
በወንጌል ጉባዔያችን ወቅት የሚሠራ ሥራ ሰብዓዊውን ዕቅድ ያማከለ ሳይሆን የክርስቶስን አሠራር ምሳሌ አድርጎ የተከተለ ሊሆን ይገባል፡፡ የቤተ hርስቲያን አባላት ለአገልግሎት መውጣት ይኖርባቸዋል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 120. ChSAmh 272.2