የክርስቲያን አገልግሎት
ማረጋጫ ያላቸው ውጤቶች
የቤተ ክርስቲያን ፈቃደኛ ወንጌላውያን በራሳቸው አነሳሽነት ወደ ፍልሚያው ቦታ በማምራት መሥራት የሚችሉትን ሥራ ለመሥራትቢነሳሱ፤ ነፍሳትን ለየሱስ በማሸነፉ ረገድ እያንዳንዳቸው ምን ያህል ስኬት ማስመዝገብ እንደሚችሉ _ መመልከት ይችላሉ፡፡ ብዙዎች የሰይጣንን ሥልጣንና ማዕረግ እየተዉ በክርስቶስ አርማ ሥር ይሰለፋሉ፡፡ ሕዝባችን እነዚvን ጥቂት የብርሃን ቃላት የያዙ መመሪያዎች መሰረት አድርጎ ምላሽ ቢሰጥ የእግዚአብሔርን አዳኝነት በእርግጥ እናያለን፡፡ ድንቅ መነቃቃቶች ይከተላሉ፡፡ ኃጢአተኞች ይለወጣሉ--አያሌ ነፍሳትም ወደ ቤተ hርስቲያን ይጨመራሉ፡፡Testimonies, vol. 8, p. 246. ChSAmh 256.1
በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አባሎቻችን ለነፍሳት ጥልቅ ፍላጎት ሊኖራቸውይገባል፡፡ የእውነት መርኅዎችን በአዳዲስ ግዛቶች እየተከሉ ራስን መሥዋዕት ያደረገ ጥረት ሲያሳዩ የታላላቅ በረከቶች ባለቤት ይሆናሉ፡፡ ለዚህ ሥራ ወጪ የተደረገው ገንዘብ የከበረ ውጤት ይዞ ከተፍ ይላል፡፡ ከቃሉ ባገኙት ብርሃን ሐሴት ያደረጉት አዳዲስ ነፍሳት፤ የእውነት ብርሃን ወደ ሌሎች የሚደርስበትን መንገድ እነርሱም በተራቸው ይደግፋሉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 49. ChSAmh 256.2
አያሌ ሠራተኞች ለመሄድ ፈቃደኛ በማይሆኑባቸው የከፋ ተቃውሞና ተስፋ አስቆራጭ ሁናቴ በሚስተዋልባቸው ቦታዎች ላይ ራሳቸውን መሥዋዕት ያደረጉ ፈቃደኛ ወንጌላውያን በሚያደርጉት ጥረት እጅግ አስገራሚ ለውጦች ይመዘገባሉ፡፡ እነዚህ አምላካዊውን ሞገስ የተቀበሉ፤ በእግዚአብሔር እንጂ በሰብዓዊው ኃይል የማይተማኑ ነፍሳት ትዕግሥተኞችና አምላካዊውን ዓላማ ለማሳካት ተግተው የሚሠሩ እንደ መሆናቸው ታላላቅ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ በእነዚህ ሠራተኞች ክንውን የሚያገኘው የመልካም ሥራ መጠን ፈጽሞ በዚህ ዓለም መታወቅ አይችልም: : Testimonies, vol. 7 pp. 22, 23. ChSAmh 256.3