የክርስቲያን አገልግሎት
እዚህ ምን ታደርጋለህ?
እውነተኛና ታማኝ ከሆኑ ወገኖች የማያቋርጥ እንቅስቃሴ እንደሚጠበቅ የሚያውቀው ሰይጣን አምላካዊው ዓላማ በታዛዦች አማካይነት እንዳይተገበር የተቻለውን ጥረት ያደርጋል፡፡ አንዳንዶች ወደ ተሰጣቸው ከፍ ያለና ቅዱስ ተልዕኮ ከመመልከት ተሰናhለው በምድራዊው ሕይወት ደስታ የሚያገኙበትንና የሚረኩበትን ዘዴ ይቀይሳል፡፡ በዓለም ምቾት ውስጥ ተደላድለው እንዲቀመጡ ይገፋፋቸዋል ወይም ለእግዚአብሔር ብርቱ ኃይል መሆን ይችሉ ከነበሩበት ስፍራ ለተሻለ ዓለማዊ ጥቅም ለቅቀው እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡ ሌሎች በሚደርስባቸው ተቃውሞ ወይም ስደት ተስፋ ቆርጠው ከኃላፊነት እንዲሸሹ ያደርጋቸዋል፡፡ ነገር ግን ሰማይ እነዚህን ወገኖች በፍቅርና አዘኔታ ዐይን ያያቸዋል፡፡ የነፍሳት ጠላት ድምጹን ጸጥ፣ ረጭ በማድረግ የተሳካለት እያንዳንዱ የእግዚአብሔር _ ልጅ _ “እዚህ ምን ታደርጋለv?” ተብሎ ይጠየቃል፡፡ እኔ ያዘዝኩህ ወደ ዓለም ሁሉ ሄደv ወንጌልን እንድትሰብክና ሕዝቦችን ለእግዚአብሔር ቀን እንድታዘጋጅ ነው፡፡ ታዲያ እዚህ ምን ታደርጋለህ? ማን እዚህ ላከህ? Prophets and Kings, pp. 171, 172. ChSAmh 252.3
እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል “እዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡ ለአገልግሎት ወደ ሚፈለጉበት ስፍራ በማምራት ብቁ የተጽእኖ አድማሳቸውን ማስፋት የሚችሉ የአምላካዊውን ቃል እውነታ በሚገባ የተማሩ የቤተሰብ አባላት በብዙ ቤተ hርስቲያኖች ይገኛሉ፡፡ Prophets and Kings, p. 172. ChSAmh 253.1