የክርስቲያን አገልግሎት

160/246

ለዘመናዊዎቹ ነህምያዎች የቀረበ ጥሪ

በዛሬዋ ቤተ hርስቲያን መጸለይና መስበክ የሚችሉ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ጸሎታቸውና ስብከታቸው ጥብቅ በሆነና በጉጉት በተሞላ ዓላማ የተደገፈ ነህምያዎች ያስፈልጉናል፡፡ አምላካዊውን እቅድ በማስፈጸሙ ረገድ ዕብራውያኑ አርበኞች የተከተሉት አካሄድ ዛሬም በቤተ hርስቲያን አገልጋዮችና መሪዎች በሥራ ላይ ሊውል ይገባል፡፡ የሚያወጧቸው እቅዶች የአባላትን ፍላጎትና ትብብር ማግኘት እንዲችሉ ሆነው ለቤተ ክርስቲያን ሊያቀርቡ ይገባል፡፡ ሕዝቡ እቅዶችን የሚያስተውልና የሥራው ተካፋይ ሲሆን እያንዳንዱ አባል ለአገልግሎቱ ግስጋሴ የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል፡፡ ጸሎት፣ እምነትና በብልሃት የተሞላ ታታሪነት ስለሚኖረው ብርቱ ውጤት የነህምያን ጥረት የጎበኘው ስኬት ያሳየናል፡፡ ሕያው እምነት ብርቱ ወደ ሆነው በድርጊት የሚገለጽ መነሳሳት በፍጥነት ይሸጋገራል፡፡ በቤተ ክርስቲያን መሪ የሚገለጸው መንፈስ በከፍተኛ መጠን በሕዝቡ ይንጸባረቃል፡፡ ዓለምን በዚህ ዘመን ሊፈትኑ ያሉትን አስፈላጊና የተከበሩ እውነቶች እናምናለን የሚሉ መሪዎች ሕዝቡን ለጌታ ቀን በማዘጋጀቱ ረገድ ጽኑ ቅንአት እያሳዩ አለመሆኑን ተከትሎ ቤተ ክርስቲያን ግዴለሽ፣ ሰነፍና ደስታ ወዳድ ልትሆን እንደምትችል መጠበቅ ይኖርብናል፡፡-- Southern Watchman, March 29, 1904. ChSAmh 245.1