የክርስቲያን አገልግሎት

158/246

የከበረ ዋጋ ያለው ምሳሌ

የነበሯትን ሁለት ሳንቲሞች ወደ ጌታ ግምጃ ቤት ያስገባችው ምስኪን መበለት እያደረገች ስለነበረው ነገር የነበራት ዕውቀት ውሱን ቢሆንም በእርሷ የተስተዋለው ራስን መሥዋዕት አድርጎ የመስጠት ምሳሌ በተለያዩ ዘመናት በየአገሩ በሺ በሚቆጠሩ ልቦች ሲተገበር ኖሮአዋል፡፡ ለእግዚአብሔር ቤት የሚውሉ ስጦታዎች በከፍታ ከሚኖሩም ሆነ በዝቅታ ከሚመላለሱ፣ ከሐብታሞችም ሆነ ከድኾች ወደ አምላካዊው ግምጃ ቤት ጎርፈዋል፡፡ የወንጌል መልእክተኞችን ለመደገፍ፣ ሆስፒታሎችን ለመክፈት፣ የተራቡትን ለመመገብ፣ የታረዙትን ለማልበስ፣ የታመሙትን ለመፈወስም ሆነ ወንጌልን ለድኾች ለመስበክ አስችሎአል፡፡ የዚህች ሴት ለጋስ የስጦታ ተግባር አያሌዎች በረከት እንዲያገኙ መንስኤ ሆኖአል፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 310. ChSAmh 236.1